ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ተጨማሪ የጥናት ምንጮች


“ተጨማሪ የጥናት ምንጮች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2020 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)] [2020 (እ.አ.አ)]

“ተጨማሪ የጥናት ምንጮች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ቤተሰብ የቤተክርስቲያን መጻህፍትን ሲያነቡ

ተጨማሪ የጥናት ምንጮች

አብዛኛዎቹ እነዚህ የጥናት ምንጮች በወንጌል ቤተ-መጽሐፍት መተግበሪያ አፕልኬሽን ውስጥ እና በChurchofJesusChrist.org ላይ ይገኛሉ።

መዝሙር እና የልጆች መዝሙር መጽሐፍ

የተቀደሰ ሙዚቃ መንፈስን ይጋብዛል እናም ትምህርትን በማይረሳ መንገድ ያስተምራል። ከመዝሙር እና የልጆች መዝሙር መጸሐፍ የወረቀት እትሞች በተጨማሪ በርካታ የመዝሙሮች እና የልጆች መዝሙሮች የድምፅና የቪድዮ ቅጆዎች በ music.ChurchofJesusChrist.org እና በቅዱስ ሙዚቃ አፕሊኬሽን ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት እና የኢንስቲቱት መመሪያ መጽሐፎች

የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት እና የኢንስቲቱት መመሪያ መጽሐፎች በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ለሚገኙት መሰረታዊ መርሆዎች እና ታሪኮች ታሪካዊ መግለጫ እና የመሠረተ ትምህርት አስተያየትን ያቀርባሉ።

የቤተክርስትያን መጽሔቶች

ፍሬንድስ፣ ኒው ኤራ፣ ኢንዛይን፣ እና ሊያሆና መጽሔቶች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የሚያስተምሩትን መሰረታዊ መርሆዎች የሚደግፉ ታሪኮችን እና ተግባሮችን ይዘዋል።

የወንጌል ርዕሶች

ወንጌል ርዕሶች ውስጥ የተለያዩ የወንጌል ርዕሰ ጉዳዮችን፣ እንዲሁም ከእነዚህ ጋር የሚገናኙ የአጠቃላይ ጉባኤ መልእክቶች፣ መጣጥፎች፣ ጥቅሶች፣ እና ቪዲዮዎች አይነት እርዳታ የሚሰጡ የጥናት ምንጮችን ለማግኘት ይችላሉ። እንዲሁም ለትምህርታዊ እና ታሪካዊ ጥያቄዎች ጥልቅ መልስ የሚሰጡ የወንጌል ርዕሶች ጽሁፎች ለማግኘት ይችላሉ።

የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች

ልጆች ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች እንዲማሩ ለመርዳት የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ታሪኮች ስዕሎችን እና ቀላል ቋንቋ ይጠቀማል። እንዲሁም የእነዚህ ታሪኮች ቪዲዮዎችን በወንጌል ቤተ መጻሕፍት አፕሊኬሽን ውስጥ እና በ ወንጌል ማህደረ መረጃ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ በ ChurchofJesusChrist.org ማግኘት ይችላሉ።

የቅዱሳት መጻህፍት ታሪኮች ማቅለሚያ መጽሐፍ፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች

ይህ የጥናት ምንጭ ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ልጆች የሚማሩትን ትምህርት ለማሳደግ የተነደፉ የተግባራዊ ገጾችን ያካትታል።

ቪዲዮ እና ስነ ስእል

የስነ ስዕል ስራ፣ ቪዲዮች፣ እና ሌሎች ማህደረ መረጃዎች ቤተሰቦቻችሁ ከቅዱሳት መጻህፍት ጋር የተዛመዱትን ትምህርቶችን እና ታሪኮችን በአይነ ህሊና እንዲመለከቱ ይረዳሉ ። የቤተክርስቲያኗን የማህደረ መረጃ የጥናት ምንጮችን ክምችት ለማሰስ የወንጌል ማህደረ መረጃ ቤተ መጻሕፍትን በChurchofJesusChrist.org ውስጥ ይጎብኙ። እነዚህ የጥናት ምንጮች በወንጌል ማህደረ መረጃ አፕሊኬሽን ውስጥ ይገኛሉ፣ እና ብዙ ምስሎችም በወንጌል የስነ ስዕል መጽሐፍ ውስጥም ይገኛሉ

ራዕያት በአገባብ

ራዕያት በአገባብ፥ ከትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍሎች በስተጀርባ ያሉት ታሪኮች የሚባለው ፅሁፍ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ስለተካተቱት ራዕዮች በሚመለከት የተፃፉ ድርሰቶች ስብስብን የያዘ ነው። በዚህ የጥናት ምንጭ ውስጥ የቀረበው አገባብ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ያሉ የጌታ ቃላት ለመጀመሪያዎቹ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ምን ትርጉም እንዳላቸው በተሻለ ለመረዳት ይረድዎታል።

ቅዱሳን

ቅዱሳን ብዙ ዕትም ያለው የቤተክርስቲያኗ ታሪክ ትረካ ነው። ጥራዝ 1፣ የእውነት መለኪያው እና ጥራዝ 2፣ ምንም ቅዱስ ያልሆነ እጅ የሚል ርዕስ ያላቸው ፅሁፎች እንደ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ተመሳሳይ የቤተክርስቲያኗን ታሪክ ጊዜ ይሸፍናሉ። እነዚህ ታሪኮች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ ስለተካቱት የሚያጠኗቸው ራዕዮች የአግባብ ግንዛቤዎችን ሊሰጣችሁ ይችላሉ።

የቤተክርስቲያን ታሪክ ርዕሶች

ስለ ሰዎች፣ ቅርሶች፣ ጂኦግራፊ፣ እና ስለ ቤተክርስቲያን ታሪክ ክስተቶች ብዙ ጽሑፎች በChurchofJesusChrist.org/study/history/topics ውስጥ ይገኛሉ።

በአዳኝ መንገድ ማስተማር

ይህ የጥናት ምንጭ ስለክርስቶስ መሰል የማስተማሪያ ዘዴ መርሆችን ለመማር እና ተግባራዊ ለማድረግ ሊረዳዎት ይችላል።