ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
በኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች መጠቀም


“በኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች መጠቀም” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 ( እ.አ.አ)]

“በኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች መጠቀም” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ) መጠቀም

ይህ ጽሁፍ ለማን ነው?

ይህ ጽሁፍ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ላሉ እያንዳንዱ ግለሰብ እና ቤተሰብ ነው። በግልዎም ሆነ ከቤተሰብዎ ጋር፣ ወንጌልን እንዲማሩ ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ከዚህ በፊት ወንጌልን ዘወትር የማያጠኑ ከሆነ፣ ይህ ጽሁፍ እንዲጀምሩ ይረዳድዎታል። ቀድሞውኑ በወንጌል ጥናት ጥሩ ልማድ ካለዎት፣ ይህ ጽሁፍ የበለጠ ትርጉም ያለው ተሞክሮ እንዲኖርዎት ይረዳል።

ይህንን ጽሁፍ እንዴት መጠቀም ይኖርብኛል?

ይህንን ጽሁፍ ለእርስዎ በሚረዳ መንገድ ሁሉ ተጠቀሙበት። ለግል እና ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እንደ መመሪያ ወይም እንደ እርዳታ ያግዝዎታል። ለቤተሰብ የቤት ምሽትም ይህን ለመጠቀም ይችላሉ። ይዘቶቹ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ የሚገኙትን ጠቃሚ መርሆዎች ያደምቃል፣ የግለሰቦችን እና ቤተሰቦችን የጥናት ሀሳቦችን እና እንቅስቃሴዎችን ይጠቁማል፣ እንዲሁም ግንዛቤአችሁን የምትመዘግቡባቸው ቦታዎችን ያቀርባል።

ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች እርስዎ ከሚሠሩት ሌሎች መልካም ነገሮች ጋር የሚወዳደር ወይም የሚተካ አይደለም። የራስዎን የእግዚአብሔር ቃል ጥናት እንዴት ማድረግ እንደሚያስፈልጎት ለመወሰን የመንፈስ ቅዱስን መመሪያ ይከተሉ።

ይህ ጽሁፍ በቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚሆነው ጋር የሚዛመደው እንዴት ነው?

በዚህ መገልገያ ውስጥ ያሉት ይዘቶች በሳምንት የንባብ መርሃግብር መሠረት የተደራጁ ናቸው። ኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል እና ኑ፣ ተከተሉኝ—ለሰንበት ትምህርት ተመሳሳይ መርሃግብርን ይከተላሉ። በቤት ውስጥ በወንጌል ለመማር እና ለመኖር ያደረጋችሁትን ጥረቶች ለመደገፍ፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያሉ አስተማሪዎ በቤትዎ ውስጥ ስላጠኑት የቅዱሳት መጻህፍት ምንባቦች ልምድዎን፣ ሀሳብዎን እና ጥያቄዎን ለማጋራት እድሎችን ይሰጥዎታል።

የሰንበት ትምህርት በወር ሁለት ጊዜ ብቻ ስለሚቀርብ፣ የሰንበት ትምህርት መምህራን ሳምንታዊ መርሃግብሩን ለመከታተል ይዘቶቹን ለመዝለል ወይም ለማዋሃድ መምረጥ ይችላሉ። በካስማ ስብሰባ ወይም በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ መደበኛ የቤተክርስቲያን ስብሰባዎች በማይካሄዱባቸው ሳምንቶችም፣ ይህ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። በእነዚህ ሳምንታት ውስጥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን በቤትዎ ውስጥ ማጥናት እንዲቀጥሉ ይጋብዛሉ።

መርሃግብሩን መከተል አለብኝን?

መርሃግብሩ በአመቱ መጨረሻ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን አንብበው እንዲጨርሱ ይረዳዎታል። በተጨማሪም፣ እንደ ሌሎች ተመሳሳይ መርሃግብርን መከተል በቤት፣ በቤተክርስቲያን፣ እና በሁሉም ቦታዎች ትርጉም ያለው ልምዶችን ያስከትላል። ነገር ግን መርሃግብሩን በመከተል እንደተያዙ ወይም እያንዳንዱን ጥቅስ ለማንበብ እንደተገደዱ አይሰማዎት፤ መርሃግብሩ በእራሳችሁ ፍጥነት እንድትከተሉ የሚያግዛችሁ መመሪያ ነው። አስፈላጊው ነገር በግል እና በቤተሰብ ውስጥ ወንጌልን መማራችሁ ነው።

ጥንዶች ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያጠኑ