ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
የግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናትዎን ለማሻሻል የሚረዱ ሀሳቦች


የግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናትዎን ለማሻሻል የሚረዱ ሀሳቦች” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) 2020(እ.አ.አ)

“የግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናትዎን ለማሻሻል የሚረዱ ሀሳቦች፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ቅዱሳት መጻህፍትን የሚያጠና ወንድ

የግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናትዎን ለማሻሻል የሚረዱ ሀሳቦች

በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የሚገኘውን የእግዚአብሔር ቃል ጥናትዎን የሚያሳድጉ አንዳንድ ቀላል መንገዶች እንደ ሚከተሉት ናቸው።

ለመነሳሳት ይፀልዩ

ቅዱሳት መጻህፍት የእግዚአብሔር ቃል ናቸው፣ ስለዚህ እነርሱን ለመረዳት ለእርዳታ እርሱን ጠይቁ።

ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነቶችን ይፈልጉ

ቅዱሳት መጻህፍት ሁሉም ነገሮች ስለ ክርስቶስ እንደሚመሰክሩ ያስተምሩናል ( 2 ኔፊ 11፥ 4ሙሴ 6፥63፣ ይመልከቱ)፣ ስለዚህ ስለአዳኝ የሚመሰክሩትን፣ ለእርሱ ያለዎን ፍቅር የሚያሳድጉትን፣ እና እርሱን እንዴት መከተል እንደሚቻል የሚያስተምሩትን ጥቅሶች ላይ ትኩረት ለመስጠት ወይም ምልክት ለማድረግ አስቡባቸው።

የሚያነሳሱ ቃላትን እና ሃረጎችን ይፈልጉ

በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ የተወሰኑ ቃላቶች እና ሀረጎች ለእርስዎ እንደተጻፉ ሆነው ሊሰማችሁ ይችላል። እነርሱ በግላችሁ ተገቢ እንደሆኑ እና አነሳሽ እና አነቃቂ እንደሆኑ ይሰማዎታል። እነዚህንም በቅዱሳት መጻህፍትዎ ላይ ምልክት ማድረግ ወይም በጥናት ደብተር ውስጥ ለመፃፍ አስቡ።

የወንጌል እውነቶችን ይፈልጉ

አንዳንድ ጊዜ የወንጌል እውነቶች (ብዙውን ጊዜ ትምህርት ወይም መርሆዎች ተብለው ይጠራሉ) በቀጥታ ይገለጻሉ፣ እናም አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በምሳሌ ወይም በታሪክ አማካይነት ይገለጻሉ። እራሳችሁን ጠይቁ፣ “እነዚህ ጥቅሶች ምን ዘለዓለማዊ እውነቶችን ያስተምራሉ?”

መንፈስን ስሙ

ከምታነቡት ጋር የማይዛመዱ ቢሆኑም፣ ለሀሳብዎ እና ለስሜትዎ ትኩረት ስጡ። እነዚያ ግንዛቤዎች የሰማይ አባትዎ እንዲማሩ የሚፈልጋቸው ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ።

ቅዱሳት መጻህፍትን ከሕይወትዎ ጋር አመሳስሉ

የምታነቡት ታሪኮች እና ትምህርቶች በሕይወትዎ ውስጥ እንዴት እንደሚሠሩ ልብ በሉ። ለምሳሌ፣ “እኔ ከማነበው ጋር የሚመሳሰሉ ምን ልምዶች አግኝቻለሁ?” ወይም “በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ስላለው የዚህን ሰው ምሳሌ መከተል የምችለው እንዴት ነው?” ብለው መጠየቅ ይችላሉ።

በሚያጠኑበት ጊዜ ጥያቄዎችን ጠይቁ

ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያጠኑ፣ ጥያቄዎች ወደ አዕምሮዎ ሊመጡ ይችላሉ። እነዚህ ጥያቄዎች ከምታነቡት ጋር ወይም በአጠቃላይ ከሕይወትዎ ጋር ሊዛመዱ ይችላሉ። እነዚህን ጥያቄዎች አሰላስሉ እና ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናት ስትቀጥሉ መልሶቹን ፈልጉ።

የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት መርጃን ይጠቀሙ

በምታነቡት አንቀጾች ላይ ግንዛቤ ለማግኘት የግርጌ ማስታዎሻዎቹን፣ የአርዕስት መምሪያን፣ የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ-ቃላትን፣ እና የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ (scriptures.ChurchofJesusChrist.org)፣ እንዲሁም ሌሎች የጥናት እርዳታዎችን ተጠቀሙ።

የቅዱሳት መጻህፍትን አገባብ አመዛዝኑ

የቅዱሳት መጻሕፍት ጽሑፉን አገባብ፣ እንዲሁም የመጣበትን ሁኔታ ወይም ድርጊት፣ በጥልቀት ሲያሰላስሉ ስለዚህ ትርጉም ግንዛቤዎችን ማግኘት ይችላሉ። ለምሳሌ፣ እግዚአብሔር ያነጋግራቸውን ሰዎች ያለፈ ታሪክ እና እምነቶች ማወቁ የቃላቱን ዓላማ በተሻለ ለመረዳት ይረዳዎታል።

ሀሳብዎን እና ስሜትዎን መዝግቡ

በሚያጠኑበት ጊዜ የሚመጡትን ግንዛቤዎች ለመመዝገብ ብዙ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ፣ ትርጉም ያለው ቃል ወይም ሐረግን ምልክት ማድረግ እና ሀሳብዎን በቅዱሳት መጻህፍትዎ ውስጥ እንደ ማስታወሻ መጻፍ ይችላሉ። እንዲሁም የሚቀበሉትን ግንዛቤዎች፣ ስሜቶች፣ እና ሃሳቦች ማስታወሻ ደብተርዎ ላይ መያዝ ይችላሉ።

የኋለኛው ቀን ነቢያትን እና ሐዋርያትን ቃል አጥኑ

በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ስለሚያገኟቸው መርሆዎች የኋለኛው ቀን ነቢያት እና ሐዋርያት ምን እንዳስተማሩ ያንብቡ (ለምሳሌ፣ conference.ChurchofJesusChrist.org እና የቤተክርስቲያን መፅሔቶችን ይመልከቱ)።

ግንዛቤዎችን አጋሩ

ከግል ጥናትዎ ያገኙትን ግንዛቤዎች መወያየት ሌሎች ሰዎችን ለማስተማር ጥሩ የሆነ መንገድ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን ይህም ደግሞ ያነበቧቸውን በተመለከተ ያሎትን ግንዛቤ ለማጠናከር ይረዳል።

በተማሩት ይኑሩ

የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ማነቃቃት ብቻ ሳይሆን አኗኗራችንን እንድንቀይር ሊያደርጉን ይገባል። በሚያነቡበት ጊዜ መንፈስ እንዲያደርጉ የሚገፋፋዎችን አድምጡ፣ ከዚያም በእነዚያ ማነሳሻዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ወስኑ።

ምስል
ቅዱሳት መጻህፍትን የምታጠና ሴት

ሽማግሌ ዴቪድ ኤ ቤድናር እንዳሉት፥ “ቤተክርስቲያኗ እንደ ተቋም እኛ መለኮታዊ ደቀመዛሙርት ለመሆን እና እስከመጨረሻ በጥንካሬ ለመፅናት ማወቅ ወይም ማድረግ የሚያስፈልጉንን ሁሉ እንድታስተምረን ወይን እንድትነግረን መጠበቅ አይገባንም። ይልቁንም፣ የግል ሀላፊነታችን መማር ያለብንን ለመማር፣ መኖር እንዳለብን በምናውቀው መልኩ ለመኖር፣ እናም መምህር እንድንሆን የሚፈልገንን ለመሆን ነው። ቤታችንም ለመማር፣ ለመኖር፣ እና ለመሆን ዋነኛ አመቺ ስፍራ ነው“ (“ማንኛውንም አስፈላጊ ነገር ለማግኘት ተዘጋጁ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.ኤ.አ)፣ 102)።

አትም