ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
መለወጥ ግባችን ነው


“መለወጥ ግባችን ነው፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2020 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

“መለወጥ ግባችን ነው፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ቅዱሳት መጻህፍትን የምታጠና ሴት

መለወጥ ግባችን ነው

የሁሉም የወንጌል ትምህርት እና ማስተማሪያ አላማ በኢየሱስ ክርስቶስ በጥልቅ እንድንለወጥ እና እርሱን እንድንመስል እኛን ለመርዳት ነው። በዚህ ምክንያት፣ ወንጌልን በምናጠናበት ጊዜ፣ እኛ አዲስ መረጃን ብቻ የምንፈልግ አይደለንም፤ “አዲስ ፍጡር” ለመሆን እንፈልጋለን (2 ቆሮንቶስ 5፥17)። ይህም ልባችንን፣ አመለካከታችንን፣ ድርጊቶቻችንን፣ እና ተፈጥሮአችንን ለመለወጥ ይረዳ ዘንድ በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ መታመን ማለት ነው።

ነገር ግን እምነታችንን የሚያጠናክር እና ወደ ተዓምራታዊ ለውጥ የሚመራው የወንጌል ትምህርት በሙሉ በአንድ ጊዜ አይከሰትም። ከመማሪያ ክፍል በላይ ወደ ግለሰብ ልብ እና ቤት ይሰፋል። ወንጌልን ለመረዳት እና ለመኖር የማይቋረጥ፣ የእለት ጥረታችንን ይጠይቃል። ነገር ግን የሰማይ አባት እኛ ብቻችንን እንድናደርገው አይጠብቅም—በምንለወጥበት እኛን ለመርዳት መንፈስ ቅዱስን ይልካል።

መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ይመራናል እናም ስለዚያ እውነት ይመሰክራል (ይመልከቱ፥ ዮሐንስ 16፥13)። እርሱ አዕምሮአችንን ያብራራል፣ ግንዛቤያችንን ያፋጥናል፣ እናም የእውነት ሁሉ ምንጭ በሆነው በእግዚአብሔር ራዕይ ልባችንን ይነካል። መንፈስ ቅዱስ ልባችንን ያነጻል። በእውነት የመኖር ፍላጎት በውስጣችን ያነቃቃል፣ እና ይህን የምናደርግበትን መንገዶች በጸጥታ ይነግረናል። በእውነትም፣ “መንፈስ ቅዱስ… ሁሉንም ያስተምረናል” (ዮሐንስ 14፥26)።

በእነዚህ ምክንያቶች፣ በወንጌል ለመኖር፣ ለመማር፣ እና ለማስተማር በምናደርገው ጥረት፣ በመጀመሪያ እና ከሁሉም በላይ የመንፈስን ጓደኝነት መፈለግ አለብን። ይህ ግብ ምርጫዎቻችንን መምራት እና ሀሳባችንን እና ድርጊቶቻችንን መምራት ይገባዋል። የመንፈስን ተጽዕኖ የሚጋብዘውን ማንኛውንም ነገር መፈለግ እና የእሱን ተጽዕኖ ከማያሳድሩ ነገሮች መራቅ አለብን—እኛ ለመንፈስ ቅዱስ መገኘት ብቁዎች ለመሆነ ከቻልን፣ እንዲሁ ከሰማያዊ አባት እና ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረን ለመኖር ብቁ ለመሆን እንደምንችል እናውቃለንና።

አትም