ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ጥር 11–17። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2፤ ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥27–65፥ “እናም የልጆቹንም ልብ ወደ አባቶቻቸው ይመልሳል”


“ጥር 11–17። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2፤ ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥27–65፥ ‘እናም የልጆቹንም ልብ ወደ አባቶቻቸው ይመልሳል’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ጥር 11–17። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2፤ ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥27–65” ኑ ተከተሉኝ—ለግለሰብና ለቤተሰብ፥ ትምህርትና ቃል ኪዳኖች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ሞሮኒ ለጆሴፍ ስሚዝ ሲገለጽለት

በስሜም ጠራኝ በማይክል ማልም

ጥር 11–17

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥27–65

“እናም የልጆቹንም ልብ ወደ አባቶቻቸው ይመልሳል”

በተደጋጋሚ ያነበባችሁት የቅዱስ መጻህፍት ጥቅስ ቢሆንም፣ ቅዱሳት መጻህፍትን ባነበባችሁ ጊዜ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ያስተምራችኋል። ስለዚህም ለአዳዲስ ማስተዋሎችና መነሳሳቶች ተቀባይ ሁኑ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

እግዚአብሔር አብና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ለጆሴፍ ስሚዝ በጥሻው ውስጥ ከተገለጹለት ሶስት አመት ሆኖታል፣ ነገር ግን ጆሴፍ ከዛ ጊዜ ጀምሮ ምንም አይነት ተጨማሪ ራዕይን አልተቀበለም ነበር። በጌታ ፊት ስለነበረው ቦታ ማሰብ ጀመረ። ልክ እንደሁላችንም ስህተትን ሰርቶ ነበር፣ እናም በሰራቸው ነገሮች ጥፋተኝነት ተሰምቶት ነበር። ቢሆንም እግዚአብሔር ለርሱ ሊሰራው የሚገባ ስራ ነበረው። እናም ጆሴፍ እንዲሰራው የተጠራበት ስራ እግዚአብሔር ከእኛ ከሚጠይቀው ጋር የተገናኘ ነው። ጆሴፍ መፅሐፈ ሞርሞንን እውን እንዲሆን አስችሏል፤ እኛስ በዚህ ምን እንድናደርግ ተጠይቀናል? ጆሴፍ የልጆችን ልብ ወደ አባቶች ለመመለስ የሚያስችለውን የክህነት ቁልፍ ይቀበላል፤ እኛስ ልባችንን ወደ አባቶቻችን ለመመለስ ምን እያደረግን ነን? ጆሴፍ በቅርቡ ስለሚፈጸሙ ትንቢቶች ተነግሮታል፤ እነዚህን እውን ለማድረግ የእኛ ክፍል ምንድን ነው? በእግዚአብሔር ስራ ላይ ስንሳተፍ፣ ልክ ነቢዩ እንዳጋጠመው፣ ነቀፋን እና እንዲሁም ስደትን ሊደርስብን እንደሚችል ልንጠብቅ እንችላለን። ነገር ግን ጌታ ልክ ለጆሴፍ እንዳደረገው አይነት፣ በእርሱ እጅ መሳሪያ ሊያደርገን እንደሚችል እምነት ሊኖረንም ይገባል።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥20–48ን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክቶች

ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥27–33

እግዚአብሔር እኔ እንድሰራው የሚፈልገው ስራ አለው።

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥27–33ን ስታነቡ፣ እግዚአብሔር ለጆሴፍ ስሚዝም እንደነበረው፣ ለእናንተም የምሰትሰሩት ስራ አንዳለው አስቡ። ከፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን የተሰጠውን ይህንን ግብዣ አሰላስሉ፥ “ስለእናንተ እና ስላላችሁ ተልዕኮ እግዚአብሔር ምን እንደሚሰማው ለማወቅ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጠይቁ። በትክክለኛው ፍላጎት ተሞልታችሁ ብትጠይቁ፣ ከጊዜ በኋል መንፈሱ ህይወት ቀያሪ የሆነውን እውነታ ሹክ ይላችኋል። … የሰማያዊ አባታችሁ እንዴት እንደሚመለከታችሁ እና ለእርሱ እንድታደርጉለት በእናንተ አመኔታውን ስለጣለበት ነገር በጥቂቱ እንኳን ግንዛቤው ቢኖራችሁ፣ ህይወታችሁ ከበፊቱ የተለየ እንደሚሆን ቃል እገባላችኋለሁ!” (“እውነተኛ ሚለኒያል መሆን ” [አለም አቀፍ መንፈሳዊ መልዕክት ለወጣት አዋቂዎች፣ ጥር 10፣ 2016 (እ.አ.አ)]፣ broadcasts.ChurchofJesusChrist.org)።

እንዳንዴ ልክ ጆሴፍ በቁጥሮች 28–29 ውስጥ እንደተሰማው አይነት ስሜት ሊሰማችሁ ይችላል። ድርጊታችሁ እግዚአብሔር እንድትሰሩ ከጠራችሁ አላማ የሚጻረር ቢሆን ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ከጆሴፍ ስሚዝ ምሳሌ ምን ትማራላችሁ?

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥34–65

መፅሐፈ ሞርሞን “የዘለዓለማዊውን ወንጌል ሙሉነት” ይዟል።

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥34–65ን ስታነቡ፣ ስለመፅሐፈ ሞርሞን ከዚህ ቀደም ሰምታችሁ ባታውቁ ኖሮ ከእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ለእናንተ ጎልተው ሊወጡ የሚችሉ ዝርዝሮችን አስቡባቸው። እንደአማኝነታችሁ፣ ለመፅሐፈ ሞርሞን ምስክርነታችሁ የዚህ መዝገብ አስፈላጊነት ምንድን ነው?

ኢሳይያስ 29፥4፣ 11–18 ላይ ያሉትን ትንቢቶች መፅሐፈ ሞርሞን እንዴት እንደሚፈጽመው አስቡበት።

የጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥36–41

የወንጌሉ በዳግም መመለስ ጥንታዊ ትንቢቶችን ወደ ፍጻሜ አምጥቷል።

እንደ ኢሳይያስ 11የሐዋርያት ሥራ 3፥22–23፤ እናኢዮኤል 2፥28–32 ያሉ የተለያዩ ትንቢቶችን ሞሮኒ ለጆሴፍ ከብሉይ ኪዳን እና ከአዲስ ኪዳን ላይ ጠቅሷል። ለጆሴፍ እነዚህን ትንቢቶች ማወቁ ለምን አስፈላጊ ነበሩ? ለእናንተስ እነዚህን ማወቁ ለምን አስፈላጊ ናቸው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2

ኤሊያስ በዳግም የመለሰው ምንድን ነው?

ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ. ኢይሪንግ እንዳሉት፣ “ጌታ ኤሊያስን ለመላክ ለምን ቃል እንደገባ ማወቁ ጠቃሚ ነው። ኤሊያስ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ታላቅ ኃይል ያለው ታላቅ ነቢይ ነበር። እግዚአብሔር ለልጆቹ ከሚሰጠው ሃይል ታላቁን ሃይልም ይዟል፥ የማጣመርን ሃይል፣ በምድር የተጣመረውን በሰማይ የሚያጣምር ሃይል ይዟል” (“በአንድነት የተጣመሩ ልቦች፣” ኤንዛይን ወይንም ሊያሆና፣ ግንቦት 2005 (እ.አ.አ)፣ 78)።

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥13–16 ፤ ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “ይህ ቤት ለእኔ ስም ይሰራ፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና ግንቦት 2020 (እ.አ.አ)፣ 84–87።

ምስል
የፓልማይራ ኒው ዮርክ ቤተመቅደስ በመጸው

የፓልማይራ ኒውዮርክ ቤተመቅደስ። በኤሊያስ አማካይነት በዳግም በተመለሰው ሃይል ቤተሰቦች በቤተመቅደስ ውስጥ ይጣመራሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2

ኤሊያስ የእኔን ልብ ወደ አባቶቼ ለመመለስ ነው የመጣው።

በዚህ ክፍል ውስጥ የሚገኙት “ተክል”፣ “ልብ” እና “መመለስ” የሚሉት ቃላት ስለኤሊያስ ተልዕኮ እና በዳግም ስለመለሳቸው የክህነት ቁል በረከቶች ምን ያስተምሯችኋል? ልባችሁ ወደ አባቶቻችሁ ሲመለስ በምን አይነት መልኩ ተሰምቷችኋል? እነዚህ አይነት ስሜቶችን በተደጋጋሚ እንዲሰሟችሁ የሚያስችሏችሁን መንገዶች አስቡባቸው። ምናልባትም የቤተሰብ አባል የሆነን ሰው ስለ ቀደምት አባቶቻችሁ ታሪክ እንዲያካፍላችሁ ጠይቁ፤ በተሻለም ይህንን መመዝገብ ትችላላችሁ። ምናልባትም የወንጌል ስርአቶችን ያልፈጸመላቸው የሞተ ቀደመ አያትን በማግኘት የእርሳቸውን ስራ በቤተመቅደስ ውስጥ ለመፈጸም ትችላላችሁ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና የቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥28–29ጆሴፍ ስሚዝ ስለ ስህተቶቹ ምን አይነት ስሜት ተሰማው? ስለተሰማውስ ስሜቶች ምን አይነት ምላሽን ሰጠ? ስህተትን ስንሰራ ምን ማድረግ አንዳለብን ከእርሱ ምን እንማራለን?

ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥33–54ጆሴፍ ስሚዝ—ታሪክ 1፥33–42 ላይ ያለውን ግማሹን ወይም ሙሉውን የሞሮኒን መልዕክት አንድ የቤተሰቡ አባል ጮክ ብሎ አራት ጊዜ እንዲያነበው መጠየቅ ትችላላችሁ (ምክንያቱም ሞሮኒ ይህንን መልዕክት አራት ጊዜ ደግሞታልና)። በእያንዳንዱ ንባብ መሀከል፣ ሌሎቹን የቤተሰብ አባላት የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶችን ሳይመለከቱ ከዚህ መልዕክት ምን እንደሚያስታውሱ እንዲያካፍሉ ጠይቁ። ጌታ ጠቃሚ መልዕክቶችን ለምን የሚደጋግም ይመስላችኋል? ጌታ በመደጋገም የሚያስተምርበት ሌሎች መንገዶች ምንድን ናቸው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2፥2ልጆቻችሁ “ለአባቶች የተገባውን የተስፋ ቃል” መረዳት እንዲችሉ፣ በጋራ አብርሐም 2፥9–11ን ማንበብ ወይንም “የክርስቶስ ልዩ ምስክሮች—ፕሬዚደንት ራስል ኤም. ኔልሰን” (ChurchofJesusChrist.org) የሚለውን ቪድዮ መመልከት ትችላላችሁ። እግዚአብሔር ከአብርሐም ጋር የገባው ቃል ኪዳን አካል የሆኑትን በረከቶች ለዩ። እነዚህን የተስፋ ቃላት በልባችን “መትከል” የምንችለው እንዴት ነው?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2፥2–3የቤተሰብ አባሎችን ልብ ወደ አባቶቻቸው (ቅድመ አያቶቻቸው) እንዲመለስ ለመርዳት፣ ስለቅድመ አያት እንዲማሩና የተማሩትንም ከተቀረው የቤተሰብ አባላት ጋር እንዲያካፍሉ ለመጋበዝ ትችላላችሁ። ጌታ ስለ ቤተሰብ አባላቶቻችን እንድንማርና ለእነርሱም የቤተመቅደስ ስርአቶችን እንድንፈጽም ለምን ይፈልጋል? በቤተሰብ ታሪክ እናም በቤተመቅደስ ስራ ስንሳተፍ በምን አይነት መልኩ ነው የምንባረከው? (ዴል ጂ. ሬንለንድ “የቤተሰብ ታሪክ እና የቤተመቅደስ ስራ፥ መጣመርና መፈወስ፣” ኤንዛይን ወይንም ሊያሆና፣ ግንቦት፣ 2018 (እ.አ.አ)፣ 46–49 ይመልከቱ)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “የቤተሰብ ታሪክ—እየተገበርኩት ነው፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 94።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት መርጃን ይጠቀሙ። እንደ ግርጌ ማጣቀሻ፣ የእርዕስት መመሪያ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ እና ChurchofJesusChrist.org ውስጥ ያሉት መተግበሪያዎች በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ስላሉ ሰዎች፣ ድርጊቶች፣ እና ሃረጎች ይበልጥ እንድትገነዘቡ ይረዷችኋል።

ምስል
ሞሮኒ የወርቅ ሰሌዳዎችን ለጆሴፍ ስሚዝ ሲሰጠው

ጆሴፍ ሰሌዳዎችን ተቀበለ በጌሪ ኢ. ስሚዝ

አትም