ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
መጋቢት 15–21 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27–28፥ “ሁሉም ነገሮች በስርዓት … መከናወን አለባቸው”


“መጋቢት 15–21 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖችን 27–28፥ ‘ሁሉም ነገሮች በስርዓት … መከናወን አለባቸው’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“መጋቢት 15–21 (እ.አ.አ)። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27–28፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ

መጋቢት 15–21 (እ.አ.አ)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27–28

“ሁሉም ነገሮች በስርዓት … መከናወን አለባቸው”

ሽማግሌ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን እንዳሉት፣ ቅዱሳት መጻህፍትን ስታጠኑና የሚሰማችሁን ስሜቶች ስትመዘግቡ “ለእግዚአብሔር ቃላት በልባችሁ ቦታ እየሰጣችሁ ነው፣ እርሱም ያነጋግሯችኋል” (“አንተም በተመለስህ ጊዜ፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2004 (እ.አ.አ)፣ 11)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በዳግም መመለስ በሂደት መገለጡን በቀጠለበት ወቅት ለቅዱሳኑ ራእይ እንደ አዲስ ነገር ነበር። የቀደሙት የቤተክርስቲያን አባላት ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለቤተክርስቲያኗ ራእይን እንደሚቀበል ያውቁ ነበር፣ ነገር ግን ሌሎችስ ይችላሉን? ከወርቅ ሰሌዳም ስምንቱ ምስክሮች አንዱ የሆነው ሀይረም ፔጅ ለቤተክርስቲያኗ ራእይ ተቀብያለሁ ብሎ ባመነበት ሰአት እንደዚህ አይነት ጥያቄዎች አንገብጋቢ እየሆኑ መጡ። ብዙ ታማኝ ቅዱሳን ይህ ራእይ ከእግዚአብሔር ነው ብለው አመኑ። ጌታ መልስ በመስጠት ቤተክርስቲያኑ “ሁሉም ነገሮች በስርዓት … መከናወን አለባቸው” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥13) ብሎ አስተማረ፣ ይህም ማለት ለመላ ቤተክርስቲያን “ትእዛዛትን እና ራእዮችን እንዲቀበል” የሚሾመው አንድ ብቻ ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥2)። ቢሆንም፣ ሌሎችም ለሚመለከታቸው የጌታ ስራ ክፍል ራእይን ለመቀበል ይችላሉ። በእርግጥም፣ ለኦሊቨር ካውድሪ ከጌታ የተሰጡት ቃላት ለሁላችንም እንደማስታወሻ ናቸው፥ “የምታከናውነው ነገር ይሰጥሀል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥15)።

በተጨማሪም “ሁሉም ነገሮች በስርአት ይከናወኑ ፣” ራዕያት በአገባብ፣ 50–53ን ይመልከቱ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥1–4

አይኔን ወደ እግዚአብሔር ክብር አድርጌ ቅዱስ ቁርባንን መውሰድ አለብኝ።

ሳሊ ናይት እና ኤማ ስሚዝ በሰኔ 1830 (እ.አ.አ) ነበር የተጠመቁት፣ ነገር ግን የተረጋገጡት ጊዜ በአመጽ ቡድን ተስተጓጎለ። ከሁለት ወር በኋላ ሳሊ እና ባለቤቷ ንዌል ኤማን እና ጆሴፍን ሊጎበኙ መጡ፣ እናም ማረጋገጫቸው በዛን እለት እንዲከናወን እና ቡድኑም ቅዱስ ቁርባን በጋራ እንደሚቋደስ ተወሰነ። ለቅዱስ ቁርባን ወይን ለማምጣት በመሄድ ላይ ሳለ፣ መልአክ ጆሴፍን አስቆመው። መልአኩ ስለ ቅዱስ ቁርባን ምን አስተማረው? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥1–4 ተመልከቱ)።

ቅዱስ ቁርባንን በምን አይነት መልኩ መቋደስ እንዳለባችሁ እነዚህ ጥቅሶች ምን ያስተምሯችኋል? ከምትማሩት ነገር ምን ለማድረግ ፍላጎት እያደረባችሁ ነው?

ምስል
የቅዱስ ቁርባን ዳቦ እና ኩባያ

ቅዱስ ቁርባን የአዳኙን መስዋዕትነት ያስታውሰናል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥15–18

የእግዚአብሔር የጦር እቃ ልብስ ክፉን እንድከላከል ይረዳኛል።

ፕሬዚደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዲህ አሉ፥ “በመንፈሳዊነት እራሳችንን ለማላበስ ማድረግ ያለብን አንድ ትልቅና አስደናቂ ነገር የለም። እውነተኛ መንፈሳዊ ሃይል በጥቃቅን ተግባሮች ባንድ ላይ ተሸምኖ በመንፈሳዊ ንጻት ከክፉ የሚጠብቅና የሚከላከል አይነት ልብስ ነው” (“በጌታ ጠንክሩ፣” ኤንዛይን፣ ሐምሌ 2004 (እ.አ.አ)፣ 8)።

እናንተ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥15–18 ስታነቡ፣ ከዚህ ስር እንዳለው አይነት ዝርዝር መስራት ትችላላችሁ። እያንዳንዱን የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ ልብስ ክፍሎች ለመልበስ ምን እያደረጋችሁ ናችሁ?

የጦር እቃ ልብስ ክፍል

የተሸፈነ የሰውነት ክፍል

ይህ የሰውነት አካል ምን እንደሚወክል

የጽድቅ ጥሩር

ልብ

የእኛ ፍላጎት እና ዝንባሌ

የደህንነት የራስ ቁር

ጭንቅላት ወይም አዕምሮ

በተጨማሪም ኤፌሶን 6፥11–182 ኔፊ 1፥23

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28

በሕይወት ያለው ነቢይ በቤተክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሔር አፍ ነው።

ማንም ሰው ለመላው ቤተክርስቲያን ትእዛዛትን እና ራእይ መቀበል የሚችል ቢሆን ምን ሊደርስ እንደሚችል አስቡት። ሀይረም ፔጅ እንዲህ አይነት ራእይ ተቀብያለሁ ብሎ ሲናገር በቤተክርስቲያን አባላት መካከል ግራ መጋባትን ፈጥሮ ነበር። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28 ውስጥ፣ ጌታ በቤተክርስቲያኑ ስላለው ስለራእይ ሂደት ገለጸ። በዚህ ክፍል ውስጥ የቤተክርስቲያን ፕሬዚደንት ስላለው ግልጽ የሆነ ሃላፊነት ምን ትማራላችሁ? በቁጥር 3 ውስጥ ለኦሊቨር ካውድሪ ከተሰጠው የጌታ ቃል ምን ትማራላችሁ? ከዚህ ክፍል ውስጥ እግዚአብሔር እንዴት ሊመራችሁ እንደሚችል ምን ትማራላችሁ?

በተጨማሪም ዳለን ኤች. ኦክስ “የሁለት መስመር ግንኙነቶች፣” ኤንዛይን ወይም ሊያሆና፣ ህዳር 2010 (እ.አ.አ)፣ 83–86።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥8–9

የኦሊቨር ካውድሪ ወደ ላማናውያን የነበረው ተልዕኮ ለምን አስፈላጊ ነበር?

አንደኛው የመሐፈ ሞርሞን አላማ “ላማናውያን ወደ አባቶቻቸው እውቀት ይመጡ ዘንድ፣ እናም የጌታን የተስፋ ቃል ያውቁ ዘንድ” ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3፥20)። ይህ ደግሞ ጌታ ለተለያዩ የመፅሐፈ ሞርሞን ነቢያት ከገባው ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው (ለምሳሌ 1 ኔፊ 13፥34–41ኢኖስ 1፥11–18ሔለማን 15፥12–13 ይመልከቱ)። ቀደምት የቤተክርስቲያን አባላት የአሜሪካ ህንዶችን የመፅሐፈ ሞርሞን ህዝቦች ዝርያ ናቸው ብለው ይቆጥሩ ነበር። (የቤተክርስቲያኗ የዚህ ቀናት አስተያየትም ላማናዊያን “ከአሜሪካን ህንዶች የዘር ሃረግ መሃከል” እንደሆኑ ነው [የመፅሐፈ ሞርሞን መግቢያ]።)

ስለኦሊቨር ካውድሪን በቅርብ ለነበሩት የአሜሪካ ህንዶች ጎሳ ስለነበረው ተልዕኮ በተጨማሪ ለማንበብ “ተልዕኮ ወደ ላማናውያንን ” (ራዕያት በአገባብ፣ 45–49) ይመልከቱ። ይህ ተልዕኮ ስለጌታ እና ስለስራው ምን ያስተምራችኋል?

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምሀርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥1–2ቅዱስ ቁርባንን ስንካፈል የአዳኙን መስዋእትነት እንዴት አድርገን በተሻለ መልኩ ለማስታወስ እንችላለን?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥5–14ከእነዚህ ጥቅሶች ስለነቢያት ምን እናውቃለን? ስለእነርሱ መረጃ ለማግኘት የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያን መፈተሽ ትችላላችሁ (scriptures.ChurchofJesusChrist.org)። እነርሱ በያዙት ቁልፍ ምን አይነት በረከቶች ለእኛ ተከፍተውልናል? ስለእነዚህ ቁልፎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ማቴዎስ 16፥16–19ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥11–16ን ይመልከቱ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥15–18ምናልባትም ቤተሰባችሁ ተጨማሪ ልብሶችን እንደ ኮፍያ፣ ሰደርያ፣ ሽርጥ፣ ወይም ጫማ በመደራረብ እና የእግዚአብሔር የጦር እቃን መልበስን በማስመሰል ጦርነት ላይ እንዳሉ መተወን ሊያስደስታቸው ይችላል። የጦር እቃ እንዴት ነው በጦር ሜዳ እኛን ለመከላከል የሚረዳው? የእናንተ ቤተሰብ የሚጋፈጥበትን መጥፎ ተጽዕኖ እና መንፈሳዊ የጦር እቃን ለመልበስ ምን ማድረግ እንደምትችሉ ተወያዩበት። “Put on the Whole Armor of God [የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ሁሉ ልበሱ]” የሚለውን ቪድዮ ማሳየትን አስቡበት (ChurchofJesusChrist.org)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥2–7ስለ ነቢይ ጥሪ ከእነዚህ ጥቅሶች ምን እንማራለን? ምናልባትም የቤተሰብ አባላት ከህያው ነቢያችን ከዚህ በፊት የተላለፉ መልእክቶችን መርምረው ምክራቸው ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንከተል እንዴት እንደሚረዱን ሊያካፍሉ ይችላሉ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 28፥11ለሌሎች እርማትን ለመስጠት ስንፈልግ፣ ለምንድነው ይህን “በአንተ እና በእርሱ መሀከል” ብቻ ማድረጉ ጠቃሚ የሚሆነው።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ኑ፣ የነብያትን ድምጽ ስሙ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 21።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የኋለኛው ቀን ነቢያትን እና ሐዋሪያትን ቃል አጥኑ። በቅዱሳት መጻህፍት ላይ ስለምታገኟቸው መርሆዎች የኋለኛው ቀን ነቢያት እና ሐዋሪያት ምን እንዳስተማሩ አንብቡ። የአጠቃላይ ጉባኤ አርእስቶችን ማውጫ ከconference.ChurchofJesusChrist.org ወይም ከወንጌል ቤተመጽሀፍት መተግበሪያ ላይ ለማየት ሞክሩ።

አትም