ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ)
ሰኔ 14–20። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64–66፥ “ጌታ ልብን እና መልካም ፈቃድ ያለውን አዕምሮ ይሻል”


“ሰኔ 14–20። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64–66፥ ‘ጌታ ልብን እና መልካም ፈቃድ ያለውን አዕምሮ ይሻል፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 2021 (እ.አ.አ) [2020 (እ.አ.አ)]

“ሰኔ 14–20። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64-66፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2021 (እ.አ.አ)

ሜዳ ጸሀይ በምትወጣበት ጊዜ

ዴቪስ ካውንቲ፣ ምዙሪ

ሰኔ 14–20

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64–66

ጌታ ልብን እና መልካም ፈቃድ ያለውን አዕምሮ ይሻል፤

ፕሬዘዳንት ሄንሪ ቢ. አይሪንግ እንዳሉት፣ “አብዛኛውን ጊዜ ወደ ቅዱሳት መጻህፍት የምሄደው ‘እግዚአብሔር ምን እንድሰራ ነው የሚፈልገው?’ ወይም ‘ምን እንዲሰማኝ ይፈልጋል?’ የሚሉ ጥያቄዎችን ይዤ ነው። በማይለወጥ ሁኔታም ከዚህ በፊት አግኝቼው የማላውቀውን አዳዲስ አስተያየቶችን እና ሀሳቦችን አገኛለሁ” (“እግዚአብሔር በቅዱሳት መጻህፍት በኩል እንዴት እንደሚናገረኝ፣” የካቲት 6፣ 2019 (እ.አ.አ)፣ blog.ChurchofJesusChrist.org)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በጣም ሙቅ በሆነው በነሀሴ 1831 (እ.አ.አ) ውስጥ፣ ጌታ እንዳዘዘው በሚዙሪ የነበረውን የፅዮን የመሬት ይዞታ ከገመገሙ በኋላ ብዙ ሽማግሌዎች ወደ ከርትላንድ ለመመለስ እየተጓዙ ነበር። ጉዞው አስደሳች አልነበረም። ተጓዦቹም፣ እንዲሁም ጆሴፍ ስሚዝ፣ ኦሊቨር ካውደሪ፣ ሲድኒ ሪግደን፣ ዕዝራ ቡዝ እና ሌሎችም፣ በሙቀት ቀልጠውና ድካም አዝሏቸው ነበር፣ ከዚያም ውጥረቶች ብዙም ሳይቆይ ወደ ጠብ ተቀየሩ። የፍቅር፣ የአንድነትና የሰላም ከተማ የሆነችውን ፅዮንን መገንባት ረዥም ጊዜ የሚወስድ ሳይመስል አልቀረም።

እንደ እድል ሆኖም በ1831 (እ.አ.አ) ሚዙሪ ውስጥ ወይም ዛሬ በልባችን እና በአጥቢያዎቻችን ውስጥ ፅዮንን ለመገንባት ፍጹም መሆን አይጠይቅብንም። ከዚያ ይልቅ “እናንተ ለሁሉም ሰዎች ይቅርታን ታደርጉ ዘንድ ይጠበቅባችኋል” ብሏል ጌታ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥10)። “ልብን እና መልካም ፈቃድ ያለውን አዕምሮ ይሻል” (ቁጥር 34)። ፅዮን የምትገነባው “በትንንሽ ነገሮች” መሠረትነት “በመልካም [ሥራ … በማይታከቱ]” ሰዎች በመሆኑ ምክንያት እርሱ ትእግስትን እና ትጋትን ይፈልግብናል (ክፍል 33)።

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥133–34136–37ን ይመልከቱ።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥1–11

ሁሉንም ይቅር ማለት ይጠበቅብናል።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥1–11ን ስታነቡ፣ ጌታ ይቅር ስላላችሁ ጊዜ አስቡ። በተጨማሪም ይቅር ልትሉት ስለሚያስፈልጋችሁ ሰው ልታስቡ ትችላላችሁ። የአዳኙ ርህራሄ ለራሳችሁ እና ለሌሎች ያላችሁን ስሜት የሚነካው እንዴት ነው? ጌታ ለምን “ሁሉንም ይቅር እንድንል” ያዘዘን ይመስላችኋል? (ቁጥር 10)። ይቅር ለማለት የምትታገሉ ከሆናችሁ፣ የሚከተሉት መረጃዎች አዳኙ እንዴት ሊረዳ እንደሚችል ምን እንደሚያስተምሩ አስቡ፥ ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ “የመታረቅ አገልግሎት፣” ኢንዛይን ወይም ሊያሆና ህዳር 2018(እ.አ.አ)፣ 77–79፤ የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ ይቅርታ ማድረግ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥31–34

እግዚአብሔር ልቤን እና መልካም ፈቃድ ያለውን አዕምሮዬን ይሻል።

“መልካም ስራ” ልታከናውኑ በምትሞክሩበት ጊዜ “ድካም” ተሰምቷችሁ ያውቃልን? ጌታ ለእናንተ ያለውን መልዕክት በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥31–34 ውስጥ ፈልጉ። “ልባችሁን እና መልካም ፈቃድ ያለውን አዕምሯችሁን” ለእግዚአብሔር መስጠት ማለት ምን ማለት ነው?(ክፍል 34)

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥41–43

ፅዮን “ለህዝብ ምልክት” ሆና ትቆማለቸ።

ምልክት ማለት “ሰዎች እንደ አንድ ነገር ማስረጃ ወይም ማረጋገጫ የሚመለከቱት ድርጊት ወይም አጋጣሚ” ነው (የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ “ምልክት፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org)። ፅዮን—ወይም የጌታ ቤተክርስቲያን—እንደ ምልክት የሆነችላችሁ እንዴት ነው? ህዝቡን ለመባረክ እንደ ምልክት ወደላይ የሚያዙ እነዚህን ሌሎች ምሳሌዎችን አስቡ፥ ዘሕልቁ 21፥6–9ማቴዎስ 5፥14–16አልማ 46፥11–20። እነዚህ ጥቅሶች በምትኖሩበት ቦታ ቤተክርስቲያኗ እንደ ምልክት እንድትሆን እንዴት መርዳት እንደምትችሉ ምን ያስተምሯችኋል? ጌታ ፅዮንን የገለጸባቸውን ሌሎች መንገዶች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥41–43 ውስጥ ፈልጉ።

ሻምበል ሞሮኒ

ሻምበል ሞሮኒ የነፃነት አርማን ይዞ፣ በጌሪ ኢ. ስሚዝ

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 65

“የጌታን መንገድ አዘጋጁ።”

ማቴዎስ መጥምቁ ዮሃንስን “የጌታን መንገድ አዘጋጁ” እያለ የሚጮህ ድምጽ ብሎ ገለጸው (ማቴዎስ 3፥3፤ በተጨማሪም ኢሳይያስ 40፥3ን ይመልከቱ)። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 65 ውስጥ፣ ጌታ ተመሳሳይ ቃላት በመጠቀም የኋለኛውን ቀን ስራውን ገለጸ። መጥምቁ ዮሃንስ ባደረገው (ማቴዎስ 3፥1–12ን ይመልከቱ) እና ጌታ ዛሬ እንድናደርግ በሚፈልገው ነገር መካከል ምን ተመሳሳይነት ታያላችሁ? በውስጡ የያዛቸው ትንቢቶች እንዲፈጸሙ ለመርዳት የሚያነሳሳችሁ በዚህ ራዕይ ውስጥ ምን ታገኛላችሁ? “በአህዛብ መካከል [የእግዚአብሔር] ድንቅ ስራዎቹን እንዲታወቁ [ለማድረግ]” የምትችሉበትን መንገድ አሰላስሉ (ቁጥር 4)።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 66

ጌታ የልቤን ሃሳቦች ያውቃል።

በቤተክርስቲያኗን አባል ከሆነ በአጭር ጊዜ በኋላ፣ ውልያም መክለለን እግዚአብሔር ለእሱ ያለውን ፈቃድ እንዲገለፅለት ጆሴፍ ስሚዝን ጠየቀው። ጆሴፍ አላወቃቸውም ነበር፣ ነገር ግን ውልያም እግዚአብሔር በነቢዩ አማካኝነት እንዲመልስለት ተስፋ ያደረገባቸው አምስት የግል ጥያቄዎች ነበሩት። የውልያም ጥያቄዎች ምን እንደሆኑ አናውቅም፣ ነገር ግን አሁን በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 66 ውስጥ ለእርሱ የተሰጡት ራዕዮቹ ሁሉንም ጥያቄዎችን ለውልያም “በሙሉ እና በሚያረካው መልኩ” መለስ እንደሰጡ እናውቃለን (“አምስቱ የውልያም መክለለን ጥያቄዎች፣” ራዕይ በአገባብ፣ 138)።

ክፍል 66ን ስታነቡ፣ ጌታ ስለ ውልያም መክለለን እና ስላሳሰበውና በልቡ ስለያዘው አላማው ምን እንደሚያውቅ አስቡ። ጌታ እንደሚያውቃችሁ የገለጸው እንዴት ነዉ? የፓትርያርክ በረከቶችን ተቀብላችሁ ከሆነ፣ ይህንን ማጥናቱን አስቡበት። ይህንን ስታደርጉም፣ እግዚአብሔር ለእናንተ ስላለው አላማ መንፈስ ቅዱስ ምን እንድትገነዘቡ ረዳችሁ?

በተጨማሪም ቅዱሳን፣ 1፥138–40፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “የፓትርያርክ በረከቶች፣” topics.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክቶች

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥8–10የቤተሰብ ግንኘነቶች ይቅርታ ማድረግን ለመማር ብዙ አጋጣሚዎችን ያቀርባሉ። ምናልባት የቤተሰብ አባላት እርስ በርስ ይቅር መባባላቸው ቤተሰቡን እንዴት እንደባረከ ሊነጋገሩ ይችሉ ይሆናል። አዳኙ እርስ በርሳችን ይቅር እንድንባባል የረዳን እንዴት ነው? ሌሎችን ይቅር በማንልበት ጊዜ እንዴት ነው “[የምንሰቃየው]” (ቁጥር 8)?

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥33ሰማያዊ አባት የእርሱን “ታላቅ ስራ” እንድታመጡ ቤተሰባችሁ ምን እንዲያደርግ ይፈልጋል? ወደ ቤተመቅደስ መሄድ፣ ወንጌልን ከጎረቤት ጋር መካፈል ወይም አለመግባባትን መፍታት ይሆናል። ምናልባት እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል እንደ ድንጋዮች ወይም ቁልፎች ወይም የሚገጣጠሙ እንቆቅልሾችን የመሳሰሉ ትንንሽ ነገሮችን ሊሰበስብ፣ ከዚያም የእግዚአብሔርን ታላቅ ስራ “መሰረት [ለመገንባት]” በየቀኑ ልናደርጋቸው የምንችላቸውን “ትናንሽ ነገሮችን” ለመወከል ሊጠቀምባቸው ይችላል። እንደቤተሰብ ልትሰሩባቸው የምትችሏቸውን ከእነዚህ ትንንሽ ነገሮች አንዱን ምረጡ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 66፥3የንስሃን አስፈላጊነት የምታስተምሩት እንዴት ነው? በከፊል ንጹህ በሆነ ሳህን ላይ ምግብ ልታቀርቡ እና ጌታ ለውልያም መክለለን የሰጠውን “በሁሉም ባይሆን፣ ንጹህ ነህ” የሚለውን ቃል ልታነቡ ትችላላችሁ። ከዚያም ሳህኑን ልታጸዱት እና ኢየሱስ ክርሰቶስ በመንፈሳዊ ንጹህ እንድንሆን እንዴት መንገዱን እንደከፈተ እየተወያያችሁ ምግቡን ልትካፈሉት ትችላላችሁ።

ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 66፥10ቤተሰባችሁ “ብኩንነትን አትሻ” ወይም በብዙ ስራዎች ሸክም አይብዛብህ የሚለውን የጌታን ምክር ለመከተል የሚትችሉት እንዴት ነው? ስለማርያም እና ማርታ ታሪክ (ሉቃስ 10፥38–42 ይመልከቱ) ለመነጋገር፣ እና ቤተሰባችሁ ዘለአለማዊ እሴት በሌላቸው ነገሮች እንዳይባክን እንዴት ሊጠበቅ እንደሚችል ልትነጋገሩ ትችላላችሁ።

ልጆችን ለማስተማር ሌሎች ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “እርዳኝ፣ ውድ አባቴ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 99።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

የምትገኙ እና ተደራሽ ሁኑ። አንዳንድ አመቺ የማስተማሪያ ጊዜዎች በቤተሰብ አባላት ልብ ውስጥ ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ሲጸነሱ ይጀምራሉ። የቤተሰብ አባላትን ለመስማት ፍላጎት እንዳላችሁ በአንደበታችሁ እና በተግባራችሁ አማካኝነት አሳውቁላቸው። (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 16ን ይመልከቱ።)

አንድ ሴት በኢየሱስ አጠገብ ተንበርክካ

ይቅር የተባለች በግሬግ ኬ. ኦልሰን። በፍቃድ ጥቅም ላይ የዋለ። http፥//www.GregOlsen.com