አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
መጋቢት 13–19 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 11–12፤ ሉቃስ 11፦ “እኔ አሳርፋችኋለሁ”


“መጋቢት 13–19 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 11–12፤ ሉቃስ 11፤ ‘እኔ አሳርፋችኋለሁ’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“መጋቢት 13–19 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 11–12፤ ሉቃስ 11፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ኢየሱስ በደመናት መሃል ቆሞ

አትፍሩ፣ በማይክል ማልም

መጋቢት 13–19 (እ.አ.አ)

ማቴዎስ 11–12ሉቃስ 11

“እኔ አሳርፋችኋለሁ”

ፕሬዝዳንት ዳለን ኤች. ኦክስ እንድስተማሩት፦ “የቀደሙ ጊዜያት መገለጦች የሆኑትን ቅዱሳት መጻህፍት፣ አሁን ላይ ላሉ መገለጦች ተቀባይ ሳይሆን መረዳት አይቻልም። … ቅዱሳት መጻህፍትን ማጥናት ሴቶች እና ወንዶች መገልጦችን እንዲቀበሉ ያስችላቸዋል” (“የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት እና መገለጥ፣” ኢንዛይን፣ ጥር 1995 (እ.አ.አ)፣ 7)።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በብዙ መንገድ ፈሪሳውያን እና ጸሀፊዎች ያህዌን ማምለክ ሸክም እንዲሆን አድርገዋል። ዘላለማዊ እውነቶች ላይ የጠበቁ ህጎችን ያጎላሉ። የእረፍት ቀን መሆን የነበረበትን የሰንበት ቀንን ህጎች እንኳን በራሳቸው ከባድ ሸክሞች ነበሩ።

ከዚያም ያህዌ እራሱ በህዝቡ መሃል መጣ። እውነተኛ የሃይማኖት አላማ ሸክም መፍጠር ሳይሆን ማቅለል እንደሆነ አስተማራቸው። እግዚአብሔር ትዕዛዛትን፣ ሰንበትን የማክበርን ጨምሮ፣ የሚሰጠን ሊባርከን እንጂ ሊጨቁነን እንዳልሆነ አስተማረ። አዎን ወደ እግዚአብሔር የሚወስደው መንገድ ቀጥ ያለ እና ጠባብ ነው፣ ነገር ግን ጌታ ብቻችንን መራመድ እንደሌለብን ሊያስታውቅ መጣ። “ወደ እኔ ኑ” ብሎ ለመነ። ለየትኛውም ምክንያት “ሸክማችሁ የከበደ” መስሎ ለሚሰማችሁ የእርሱ ግብዣ በእርሱ አጠገብ እንድንቆም፣ ራሳችንን ከእርሱ ጋር እንድናስር እና ሸክማችንን እንዲጋራን እንድንፈቅድ ነው። የእርሱ ቃልኪዳን “ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ” ነው። ለብቻ ለመሸከም መሞከር ወይም በስጋ ለባሽ መፍትሄ መደገፍ—ከሌሎች አማራጮች ጋር ሲነጻጸር የእርሱ “ቀንበር ልዝብ ሸክሙም ቀላል ነው።” (ማቴዎስ 11፥28–30።)

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ማቴዎስ 11፥28–30

ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ላይ ስደገፍ እረፍት ይሰጠኛል።

ሁላችንም ሸክም እንሸከማለን—አንዳንዱ ከራሳችን ሃጢያቶች እና ስህተቶች የመጣ፣ ሌላው ደግሞ በሌሎች ምርጫ፣ የተቀሩት ደግሞ የማንም ጥፋት ሳይሆኑ የምድር ላይ ኑሮ አካል የሆኑ ናቸው። የችግሮቻችን ምክንያት ምንም ይሁን ምን ኢየሱስ ሸክማችንን መሸከም እንድንችል እና እረፍት እንድናገኝ እንዲረዳን ወደሱ እንድንመጣ ይለምነናል (በተጨማሪም ሞዛያ 24ን ተመልከቱ)። ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር “ቃል ኪዳን መግባት እና መጠበቅ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያስረናል” በማለት አስተምረዋል (“ሸክማቸውን ማቅለል እንዲችሉ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2014 (እ.አ.አ) 88)። ይህንን በአዕምሯችሁ በመያዝ የአዳኙን ቃላት በነዚህ ጥቅሶች ላይ ይበልጥ ለመረዳት እንደሚከተሉት አይነት ጥያቄዎችን አሰላስሉ፤ ቃል ኪዳኖቼ ከአዳኙ ጋር የሚያስሩኝ እንዴት ነው? ወደ ክርስቶስ ለመምጣት ምን ማድረግ አለብኝ? የአዳኙ ቀንበር ልዝብ ሸክሙም ቀላል የሚሆነው እንዴት ነው?

ስታነቡ ሌሎች ምን አይነት ጥያቄዎች ወደ አዕምሯችሁ ይመጣሉ? ጻፏቸው፣ እናም መልሶችን በዚህ ሳምንት በቅዱሳት መጻህፍት እና በነቢያት ቃላት ላይ ፈልጉ። ለአንዳንድ ጥያቄዎቻችሁ መልስ ከላይ በተጠቀሰው በሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር መልዕክት ላይ ልታገኙ ትችላላችሁ።

በተጨማሪም ጆን ኤ.መክኩን “ወደ ክርስቶስ ኑ—እንደ ኋላኛው ቀን ቅዱሳን መኖር፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020፣ 36–38፤ ላውረንስ ኢ.ቾርብሪገ፣ “መንገዱ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2008 (እ.አ.አ)፣ 34–36 ተመልከቱ።

ምስል
ደቀመዛሙርት በስንዴ እርሻ ውስጥ ሲራመዱ ሰዎች እየተመለከቱ

ደቀመዛሙርት በሰንበት ስንዴ እየበሉ፣ በጄምስ ቲሶት

ማቴዎስ 12፥1–13

“በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዶአል”

የፈሪሳውያን አስተምሮት ከክርስቶስ በብዙ መንገዶች የተለዩ ናቸው፤ በተለይም ሰንበትን የሚያከብሩበት መንገድ። ማቴዎስ 12፥1–13ን ስታነቡ ለሰንበት ያላችሁ አመለካከት እና ተግባራችሁ ከአዳኙ አስተምሮቶች ጋር እንዴት መስመር ላይ እንደሆኑ ማሰብ ትችላላችሁ። ይህን ለማድረግ እንደሚከተሉት አይነት ጥቅሶችን ማሰላሰል ትችላላችሁ፦

  • “ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን.እወድዳለሁ” (ቁጥር 7ሆሴዕ 6፥6ን ተመልከቱ)።

  • “የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና” (ከቁጥር 8)።

  • “በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዶአል”(verse 12)።

እነዚህ አስተምሮቶች ስለ ሰንበት ባላችሁ አመለካከት ላይ እንዴት ተፅዕኖ ያሳድራሉ?

በተጨማሪም ማርቆስ 2፥233፥5፤ የወንጌል ርዕሶች “የሰንበት ቀን፣” topics.ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ።

ማቴዎስ 12፥34–37ሉቃስ11፥33–44

ንግግሬ እና ተግባሬ በልቤ ውስጥ ያለውን ያሳያል።

አዳኙ ፈሪሳውያንን ይወቅስ ከነበረበት ምክንያቶች ዋነኛው፥ ሃሳባቸው ንጹህ ሳይሆን ጻድቅ ለመምሰል መሞከራቸው ነበር። በማቴዎስ 12፥34–37 እና ሉቃስ 11፥33–44 ላይ ጌታ ለፈሪሳውያን የሰጠውን ማስጠንቀቅያ ስታነቡ በልባችን እና በተግባራችን መካከል ያለውን ግንኙነት አሰላስሉ። “ከልቡ መልካም መዝገብ” የሚለው ሃረግ ለእናንተ ምን ማለት ነው? (ማቴዎስ 12፥35)። ቃላችን ሊያጸድቀን ወይም ሊያስኮንነን የሚችለው እንዴት ነው? (ማቴዎስ 12፥37)። የአይናችሁ “ጤናማ” መሆን ለእናንተ ምን ማለት ነው? (ሉቃስ 11፥34)። በአዳኙ ሃይል እናንተ እንዴት “ብሩህ” (ሉቃስ 11፥36) መሆን እንደምትችሉ አሰላስሉ።

በተጨማሪም አልማ 12፥12–14ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥67–68ን ተመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ማቴዎስ 11፥28–30የቤተሰብ አባላት በእነዚህ ቁጥሮች የአዳኙን አስተምሮቶች በምናባቸው መሳል እንዲችሉ ከባድ የሆነን ነገር መጀመርያ ብቻቸውን፣ ከዚያም ደግሞ በእርዳታ እንዲጎትቱ በማድረግ መርዳት ትችላላችሁ። አንዳንድ የምንሸከማቸው ሸክሞች ምንድናቸው? የክርስቶስን ቀንበር በላያችን መሸከም ምን ማለት ነው? በዚህ ጽሁፍ መጨረሻ ላይ ያሉ ምስሎች ቀንበር ምን እንደሆነ ሊያስረዳችሁ ይችላል።

ማቴዎስ 12፥10–13ኢየሱስ በሰንበት አንድን ሰው ስለመፈወሱ ስታነቡ በአዳኙ አማካኝነት እንዴት “ደህና [እንደሚሆን]” ቤተሰባችሁ መነጋገር ይችላል። ሰንበት ለእኛ የፈውስ ቀን እንዴት ሊሆነን ይችላል?

በእነዚህ ጥቅሶች ላይ ካሉ የአዳኙ ምሳሌዎች በመነሳሳት ቤተሰባችሁ “በሰንበት መልካም [ለመሥራት]” የተለያዩ መንገዶችን ዝርዝር ማውጣት ይችላል (ቁጥር 12)። ሌሎችን የማገልገል እድሎችን ማካተታችሁን አረጋግጡ። ዝርዝራችሁን መያዝ ለሚመጡ ሰንበቶች ተመልሳችሁ እንድትመለከቱ ሊረዳችሁ ይችላል።

ሉቃስ 11፥33–36“ብሩህ” መሆን ምን ማለት እንደሆነ ቤተሰባችሁን እንዴት ማስተማር እንዳለባችሁ አሰላስሉ (ቁጥሮች 34፣ 36)። ቁሳቁስን በመጠቀም ማስተማር ሊረዳ ይችላል? ወደ ህይወታችን፣ ወደ ቤታችን እና ወደ አለም የአዳኙን ብርሃን ማምጫ መንገዶችን መወያየት ትችላላችሁ። ለሃሳብ “ብርሃንም በጨለማ ይበራል” የሚለውን ቪድዮ መመልከት ትችላላችሁ ChurchofJesusChrist.org

ሉቃስ 11፥37–44ምናልባት ቤተሰባችሁ እነዚህን ጥቅሶች እቃን በአንድነት እያጠበ ሊወያይበት ይችላል። እንደ ጎድጓዳ ሰሃን እና ኩባያዎች የመሳሰሉ እቃዎች ውጭያዊ ክፍል ብቻ ማጠብ ለምን ጥሩ ሃሳብ እንዳልሆነ ማውራት ትችላላችሁ። ከዚያም ጻድቅ መሆን በውጭ ለሚታየው ምግባራችን ብቻ ሳይሆን በውስጣዊ ሃሳባችን እና ስሜቶች ጭምር እንደሆነ ይህን ታሪክ ማገናኘት ትችላላችሁ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልን ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “የእግዚአብሔር ህጎች እንዴት ገር ናቸው፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 125።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ፅኑ ሁኑ። አንዳንድ ቀን የቅዱሳት መጻህፍትን ጥናት ይበልጥ ከባድ ሊሆንባችሁ ወይም እንዳሰባችሁት ብዙ ተጸዕኖ የሚፈጥር ላይመስላችሁ ይችላል። ተስፋ አትቁረጡ። ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናርእንዳስተማሩት፣ “ትንሽ የሚመስሉ ነገሮችን በጽናት መፈጸማችን ትልቅ የሆነ መንፈሳዊ ውጤት ሊያመጣ ይችላል” (“ቤት ውስጥ ይበልጥ ትጉ እና አሳቢ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2009 (እ.አ.አ) 20)።

ምስል
ሁለት በሬዎች በአንድነት ተጠምደው

“ቀንበሬንም በላያችሁ ተሸከሙ፣ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝ፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ” (ማቴዎስ 11፥29)። ፎቶ © iStockphoto.com/wbritten

አትም