አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
የካቲት 27–መጋቢት 5 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 8፤ ማርቆስ 2–4፤ ሉቃስ 7፦ “እምነትሽ አድኖሻል”


“የካቲት 28–መጋቢት 5 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 8፤ ማርቆስ 2–4፤ ሉቃስ 7፦ ‘እምነትሽ አድኖሻል፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“የካቲት 28–መጋቢት 5 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 8፤ ማርቆስ 2–4፤ ሉቃስ 7፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ኢየሱስ አንድን ሰው ከመኝታው እያስነሳው

የካቲት 27–መጋቢት 5 (እ.አ.አ)

ማቴዎስ 8ማርቆስ 2–4ሉቃስ 7

“እምነትሽ አድኖሻል”

የቅዱሳት መጻህፍት ጥናታችሁ በችኮላ እንዳይሆን ተጠንቀቁ። ምንም እንኳን ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ባትችሉ በጸሎት መንፈስ ለማሰላሰል ጊዜ ውሰዱ። እነዚህ የጥሞና ጊዜያት ብዙ ጊዜ ወደ ግላዊ መገለጥ ይመራሉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በአዲስ ኪዳን ግልጽ ከሆኑ መልዕክቶች መካከል አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈዋሽ እንደሆነ ነው። የታመሙትን እና የተጎዱትን ስለፈወሰበት የተጻፉ ምዕራፎች ብዙ ናቸው—በትኩሳት ከታመመችው ሴት እስከ የመበለቲቱን ወንድ ልጅ ከሞት እስከማስነሳት። በአካላዊ ፈውስ ላይ ትኩረት የተሰጠው ለምድን ነው? በእነዚህ ተአምራቶች ውስጥ ለእኛ ምን አይነት መልዕክት አለ? በእርግጥ አንድ ግልጽ የሆነ መልዕክት አለ፤ ይህም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በሁሉ ላይ፣ እንዲሁም አካላዊ ህመማችንን እና ጉድለቶቻችንን ጨምሮ ሃይል እንዳለው ነው። ነገር ግን ለማያምኑ ጸሀፊዎች በተናገረው ቃላት ላይ፤ “ለሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ሊያስተሰርይ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ” (ማርቆስ 2፥10) የሚል ሌላ ትርጉም ይገኛል። ስለዚህ ስለ አይነ ስውር ወይም ስለ ለምጻም መፈወስ ስትሰሙ ከአዳኙ ልታገኙ ስለምትችሉት—አካላዊ እና መንፈሳዊ ፈውስ—ልታስቡ እና “እምነ[ታችሁ] [አድኗችኋል]” ሲላችሁ ልትሰሙት ትላላችሁ (ሉቃስ 7፥50)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ማቴዎስ 8ማርቆስ 2–3ሉቃስ 7

አዳኙ የአካል ጎዶሎነትን እና በሽታን መፈወስ ይችላል።

በእነዚህ ጥቂት ምዕራፎች ውስጥ አዳኙ ያደረገው ብዙ ተአምራቶች ተጽፈዋል። ስለእነዚህ ፈውሶች ስታጠኑ ለእናንተ የሚሆን መልዕክት ፈልጉ። ይህ ታሪክ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ስላለ እምነት ምን ያስተምራል ብላችሁ ራሳችሁን ትጠይቁ ይሆናል። ታሪኩ ስለአዳኙ ምን ያስተምራል? እግዚአብሔር ከዚህ ተአምር ምን እንድማር ይፈልጋል? እነኚህ አንዳንድ ምሳሌዎች ናቸው፣ ነገር ግን ብዙ ተጨማሪ ምሳሌዎች አሉ፦

በተጨማሪም ዴቪድ ኤ ቤድናር፣ “የጌታን ፈቃድ እና ጊዜ መቀበል፣” ሊያሆና፣ ነሃሴ 2016 (እ.አ.አ)፣ 17–23፤ ኒል ኤል. አንደርሰን፣ “የቆሰለ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 83–86 ተመልከቱ።

ማርቆስ 2፥15–17ሉቃስ 7፥36–50

ኢየሱስ ክርስቶስ ሃጥያተኞችን ለመንቀፍ ሳይሆን ለመፈወስ ነው የመጣው።

በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ኢየሱስ ከጸሀፊዎች እና ከፈሪሳውያን ጋር ስላለው ግንኙነት ስታነቡ ራሳችሁን በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ታገኙ እንደሆነ አስቡ። ለምሳሌ ሃሳባችሁ እና ስራችሁ እንደ ፈሪሳዊው ስምኦን ናቸውን? ኢየሱስ ሃጢያተኞችን የሚያይበትን መንገድ እና እንደ ስምኦን ያሉ ፈሪሳውያንን የሚያዩበትን መንገድ ልዩነት እንዴት ልትገልጹ ትችላላችሁ? በሃጥያት የተጨነቁ ከአዳኙ ጋር ሲሆኑ ሊሰማቸው የሚችለውን ስሜት አስቡ። እነሱ ከእናንተ ጋር ሲሆኑ ምን ይሰማቸዋል?

በተጨማሪም እናንተ በሉቃስ 7፥36–50 ላይ እንደተገለጸቸ ሴት እንዴት እንደሆናችሁ አሰላስሉ። አዳኙ ያሳያትን አይነት ፍቅር እና ምህረት መቼ ነው የገጠማችሁ? ከእርሷ የእምነት፣ የፍቅር እና ትህትና ተምሳሌትነት ምን ትማራላችሁ?

በተጨማሪም ዮሐንስ 3፥17ሉቃስ 9፥51–56፤ ዲተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “የጸጋ ስጦታ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ) 107–10 ን ተመልከቱ።

ማቴዎስ 8፥18–22ማርቆስ 3፥31–35

የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር መሆን ማለት እርሱን በህይወቴ አስቀድመዋለሁ ማለት ነው።

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ኢየሱስ የእርሱ ደቀመዝሙር መሆን አንዳንዴ ለእኛ ዋጋ ያለውን ነገር መስዋዕት ማድረግ ማለት ቢሆንም እንኳን፥ በህይወታችን እርሱን ማስቀደምን እንደሚጠይቅ አስተምሯል። እነዚህን ጥቅሶች ስታነቡ የራሳችሁን ደቀመዝሙርነት አሰላስሉ። ደቀመዛሙርት እርሱን ለማስቀደም ፈቃደኞች መሆን ያለባቸው ለምንድነው? ኢየሱስን ለማስቀደም ምን መተው ሊኖርባችሁ ይችላል? (በተጨማሪም ሉቃስ 9፥57–62ን ተመልከቱ።)

ማቴዎስ 8፥23–27ማርቆስ 4፥35–41

በህይወት ማእበል ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም የማምጣት ሃይል አለው።

የኢየሱስ ደቀመዛሙርት በባህር ማዕበል ላይ እንደተሰማቸው ተሰምቷችሁ ያውቃልን—ውሃው መርከቢቷን ሲሞላ መመልከት እና “መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን?” ማለትስ?

ማርቆስ 4፥35–41 ውስጥ፣ አራት ጥያቄዎችን ታገኛላችሁ። እያንዳንዳቸውን ዘርዝሩ እናም የህይወት ፈተናዎች በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዴት መጋፈጥ እንደሚቻል የሚያስተምረውን አሰላስሉ። ለህይወታችን ማዕበል አዳኙ ሰላም እንዴት ያመጣል?

በተጨማሪም ሊሳ ኤል. ሃርክነስ “ዝም በል፥ ጸጥ በል፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2020 (እ.አ.አ)፣ 80–82 ተመልከቱ።

ምስል
ኢየሱስ መርከብ ላይ ማዕበሉን እያሰከነ

ከፍርሃት ወደ እምነት፣ በሃዋርድ ላዮን

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ማቴዎስ 8ማርቆስ 2–4ሉቃስ 7በእነዚህ ምዕራፎች ላይ የተጠቀሱ ተአምራትን ለመዘርዘር አስቡ። የእነዚህን ስዕል ለመሳል ወይም ስዕል ለማግኘት ሞክሩ (የወንጌል የስነ ስዕል መጽሐፍን ወይም ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ)። እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ከተአምራቶች ውስጥ አንዱን ስዕል በመጠቀም መናገር እና የሚማሩትን ማካፈል ይችላሉ። በአሁን ጊዜ ያያችሁትን ወይም ያነበባችሁትን የአንዳንድ ተአምራት ምሳሌዎችን ማካፈል ትችላላችሁ።

በተጨማሪም “የናይን መበለት” እና “ማዕበሉን ጸጥ ማሰኘት” የሚሉ ቪዲዮዎች ተመልከቱ (ChurchofJesusChrist.org)።

ማርቆስ 8፥5–13ሉቃስ 7፥1–10ስለ መቶ አለቃው እምነት ኢየሱስን ያስደነቀው ነገር ምንድነው? በኢየሱስ ክርስቶስ ተመሳሳይ እምነት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ማርቆስ 2፥1–12ምዕራፍ 23፤ መራመድ የማይችለው ሰው” (በአዲስ ኪዳን ታሪኮች፣ 57–58፣ ወይም በChurchofJesusChrist.org የሚገኝ ተመሳሳይ ቪድዮ) ማርቆስ 2፥1–12 ላይ እንድትወያዩ ሊረዳችሁ ይችላል። (“ኢየሱስ ሃጥያትን ይቅር አለ እና በደዌ የተመታን ሰው ፈወሰ” የሚለውን ቪዲዮ በChurchofJesusChrist.org ላይ ተመልከቱ)። መራመድ እንደማይችለው ሰው ጓደኞች መሆን የምንችለው እንዴት ነው? እንደዚህ አይነት ጓደኛ የሆናን ማነው?

ማርቆስ 4፥35–41እነዚህ ጥቅሶች የቤተሰብ አባላት ፍርሃት ሲሰማቸው ሊረዷቸው ይችላሉ? ምናልባት ቁጥር 39ን ማንበብ እና አዳኙ ሰላም እንዲሰማቸው የረዳቸውን ልምድ ሊያካፍሉ ይችላሉ።

አንድ ሰው ማርቆስ 4፥35–38ን ሲያነብ፣ ህጻናት ማዕበል ባለበት መርከብ ውስጥ እንደሆኑ አድርገው መተወን ያስደስታቸው ይሆናል። ከዚያም አንድ ሰው ቁጥር 39፣ ሲያነብ ጸጥ ባለ ባህር ውስጥ እንዳሉ ማስመሰል ይችላሉ። በተጨማሪም በአዳኙ ሰላም ስለማግኘት እንደ “መምህር፥ አውሎ ነፋሱ እያስጨነቀ ነው” (መዝሙሮች፣ ቁጥር 105ን) አይነት መዝሙር በአንድነት ልትዘምሩ ትችላላችሁ። በመዝሙሩ ላይ የትኞቹ ሃረጎች ናቸው ኢየሱስ ስለሚሰጠው ሰላም የሚያስተምሩን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልን ይመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “መምህር፥ አውሎ ነፋሱ እያስጨነቀ ነውመዝሙሮች፣ ቁጥር 105።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

የምትገኙ እና ተደራሽ ሁኑ። አንዳንድ አመቺ የማስተማሪያ ጊዜዎች በቤተሰብ አባላት ልብ ውስጥ ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ሲጸነሱ ይጀምራሉ። የቤተሰብ አባላትን ለመስማት ፍላጎት እንዳላችሁ በአንደበታችሁ እና በተግባራችሁ አማካኝነት አሳውቁላቸው። (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር]፣ 16ን ይመልከቱ።)

ምስል
ኢየሱስ ታሞ አልጋ ላይ ሆኖ በጣራ ወደታች ካወረዱት ሰው ጋር

ክርስቶስ እና በደዌ የተመታው ሰው፣ በጄ. ከርክ ሪቻርድስ

አትም