“የካቲት 20–26 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 6–7፦ ‘እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበር፣’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]
“የካቲት 20–26 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 6–7፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)
የካቲት 20–26 (እ.አ.አ)
ማቴዎስ 6–7
“እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበር”
ጥያቄ በአዕምሯችን በመያዝ እንዲሁም የሰማይ አባት እንድናውቅ የሚፈልገውን ለመረዳት በእውነት በመፈለግ ቅዱሳት መጻህፍትን ስናነብ መንፈስ ቅዱስ እንዲያነሳሳን እንጋብዛለን። ማቴዎስ 6–7ን ስታነቡ ለሚያሳድርባችሁ ስሜት ትኩረት ስጡ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
የተራራው ላይ ስብከት በክርስትና ይበልጥ ከሚታወቁ ንግግሮች መሃል አንዱ ነው። አዳኙ ኮረብታ ላይ ያለች ከተማ፣ የምድር አበቦች፣ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩሎችን በመሳሰሉ ብዙ ምሳሌዎች አስተምሯል። ነገር ግን የተራራው ላይ ስብከት ውብ ከሆነ ንግግር በላይ ነው። አዳኙ ለደቀመዛሙርቱ ያስተማረው ትምህርት ሃይል ህይወታችንን ሊቀይር ይችላል በተለይም ከኖርንባቸው። የዛኔ የእርሱ ቃላት ቃላት ብቻ አይሆኑም፤ ለህይወት ጠንካራ መሰረት ይሆናሉ፣ ልክ እንደ ብልሁ ሰው ቤት የአለምን ነፋሳት እና ጎርፍ መቋቋም ይችላል (ማቴዎስ 7፥24–25ን ተመልከቱ)።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
የአዳኙን አስተምሮቶች መኖር እንደ እርሱ እንድሆን ይረዳኛል።
የተራራው ላይ ስብከት ብዙ የወንጌል መርሆዎችን ይዟል። እነዚህን ጥቅሶች ስታነቡ ጌታ ምን እንድትማሩ እንደሚፈልግ ጠይቁት።
አንድ የምታገኙት መርህ የእግዚአብሔርን ነገሮች ከአለማዊ ነገሮች ቅድሚያ ልንሰጣቸው እንደሚገባ ነው። ማቴዎስ 6–7 ላይ ካሉ ከአዳኙ ትምህርቶች የትኞቹ ናቸው በሰማያዊ ነገሮች ላይ እንድታተኩሩ የሚረዷችሁ? ሌሎች ምን ሃሳቦችን ወይም መረዳቶች ታገኛላችሁ? ምን ለማድረግ ተነሳሽነት ይሰማችኋል? ያሳደረባችሁን ስሜት ለመመዝገብ አስቡ። ለምሳሌ፦
እኔ ሰው ስለ እኔ ከሚያስበው ይልቅ እግዚአብሔር ስለሚያስበው ይበልጥ መጨነቅ እፈልጋለሁ። | |
በማቴዎስ 6–7 ላይ ሌላው መርህ ጸሎት ነው። ጸሎታችሁን ለመገምገም ትንሽ ጊዜ ውሰዱ። በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የምታደርጉት ጥረት እንዴት እንደሆነ ይሰማችኋል? በማቴዎስ 6–7 ካሉ አስተምሮቶች ጸሎታችሁን እንድታሻሽሉ የሚያነሳሳችሁ የትኛው ነው? የሚቀበሉትን ስሜቶች መዝግቡ። ለምሳሌ፦
ስጸልይ የሰማይ አባትን ስም ማክበር እፈልጋለሁ። | |
ጸሎት ሳደርግ የጌታ ፈቃድ እንዲሆን ፍላጎቴን መግለጽ እችላለሁ። | |
ለእናንተ የሚሆኑ ሌሎች የሚደጋገሙ መርሆዎችን ወይም መልዕክቶችን ለማግኘት የተራራው ላይ ስብከትን ደግማችሁ ለማንበብ ልታስቡ ትችላላችሁ። የምታገኙትን በጥናት ደብተራችሁ ከሃሳባችሁ እና ካሳደረባችሁ ስሜት ጋር ጻፉ።
ጸሎት ላይ “በከንቱ [መድገም]” ምን ማለት ነው?
ብዙ ጊዜ ሰዎች “በከንቱ [መድገም]” ማለት ተመሳሳይ ቃል መደጋገም እንደሆነ ይረዳሉ። ነገር ግን ከንቱ የሚለው ቃል ዋጋ የሌለው ነገርን ሊገልጽ ይችላል። “በከንቱ [መድገም]” በእውነት እና ከልብ በሆነ ስሜት አለመጸለይ ማለት ሊሆን ይችላል (አልማ 31፥12–23ን ተመልከቱ)።
እኔ በጽድቅ መፍረድ እችላለሁ።
በማቴዎስ 7፥1 ውስጥ አዳኙ ፈጽሞ መፍረድ እንደሌለብን እየተናገረ ያለ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን በሌሎች ቅዱሳት መጻህፍት (በዚህ መዕራፍ ላይ ያሉ ሌሎች ቁጥሮችን ጨምሮ) እንዴት መፍረድ እንዳለብን ትዕዛዝ ይሰጠናል። ያ ግራ የሚያጋባ ከመሰለ የዚህ ቁጥር የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ሊረዳችሁ ይችላል፤ “እንዳይፈረድባችሁ በክፋት አትፍረዱ፤ ነገር ግን በጽድቅ ፍረዱ” (በማቴዎስ 7፥1፣ የግርጌ ማስታውሻ ሀ )። በማቴዎስ 7፥1–5 ውስጥ እና በተቀረው መዕራፍ ላይ “በጽድቅ [መፍረድን]” ማወቅ እንድትችሉ የሚረዳችሁን ምን ታገኛላችሁ?
በተጨማሪም የወንጌል መመርያ፣ “ሌሎች ላይ መፍረድ፣” topics.ChurchofJesusChrist.org፤ ልን ጂ. ሮቢንስ፣ “ጻድቁ ዳኛ፣” Liahona፣ ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 96–98 ተመልከቱ።
ፈቃዱን በመፈጸም ኢየሱስ ክርስቶስን አውቀዋለሁ።
በማቴዎስ 7፥23 ላይ “ከቶ አላወቅኋችሁም” የሚለው ሃረግ በጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም “ከቶ አላወቃችሁኝም” ተብሎ ተቀይሯል (ማቴዎስ 7፥23፣ የግርጌ ማስታወሻ ሀ )። ጌታ በቁጥሮች 21–22 ፈቃዱን ስለማድረግ ያስተማረውን ይበልጥ ለመረዳት ይህ ለውጥ እንዴት ይረዳችኋል? ጌታን ምን ያህል እንደምታውቁት ይሰማችኋል? እርሱን ይበልጥ ለማወቅ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
በተጨማሪም ዴቪድ ኤ. ቤድናር፣ “ብታውቁኝ ኖሮ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ) ተመልከቱ።
የአዳኙን ትምህርቶች መታዘዝ ለህይወቴ ጠንካራ መሰረት ይፈጥራል።
ወንጌልን መኖር ጠላታችንን ከህይወታችን አያስወግድም። በማቴዎስ 7፥24–27 በአዳኙ ምሳሌ ውስጥ የነበሩት ሁለቱም ቤቶች ማዕበል መጥቶባቸዋል። ነገር ግን አንዱ ቤት መቋቋም ቻለ። የአዳኙን አስተምሮት መኖር ጠንካራ መሰረት የፈጠረላችሁ እንዴት ነው? “[ቤታችሁን] በዓለት ላይ” መገንባት መቀጠል እንድትችሉ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ይሰማችኋል? (ቁጥር 24ን ተመልከቱ)።
በተጨማሪም ሔላማን 5፥12ን ተመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ማቴዎስ 6–7።ከማቴዎስ 6–7 መማርያ አንዱ መንገድ እንደ ቤተሰብ “የተራራ ላይ ስብከት፤ የጌታ ጸሎት” እና “የተራራ ላይ ስብከት፤ በሰማይ መዝገብ” (ChurchofJesusChrist.org) የሚሉ ርዕሶች ያላቸውን ቪድዮ በመመልከት ነው። የቤተሰብ አባላት በቅዱሳት መጻህፍታቸው መከታተል እናም መወያየት የሚፈልጉት ነገር ሲኖር ቪድዮውን ማቆም ይችላሉ። ይህ ተግባር ለብዙ ቀናት ሊቀጥል ይችላል።
2:194:33 -
ማቴዎስ 6፥5–13።አዳኙ ከጸለየው መንገድ ስለ ጸሎት ምን ልንማር እንችላለን? የእርሱን ጸሎት የግል እና የቤተሰብ ጸሎታችንን ለማሻሻል እንደ ምሳሌ እንዴት መጠቀም እንችላለን? (በተጨማሪም ሉቃስ 11፥1–13ን ይመልከቱ።) ትንሽ ልጆች ካሏችሁ፣ በአንድነት ጸሎትን መለማመድ ትችላላችሁ።
-
ማቴዎስ 6፥33።“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት … ፈልጉ” ምን ማለት ነው? ይህንን በግል እና እንደቤተሰብ እንዴት እየፈጸማችሁ ነው?
-
ማቴዎስ 7፥1–5።በዚህ ጥቅስ ላይ ያሉትን በምዕናብ ለማየት ቤተሰባችሁ ሲጥሩ፣ (ትንሽ የእንጨት ስባሬ) እና ምሰሶ (ትልቅ እንጨት) ማግኘት ይችላሉ። ሁለቱን በማነጻጸር ሌሎች ላይ ስለመፍረድ ምን ያስተምረናል? ይህንን ርዕስ ይበልጥ ለማብራራት በ“ሌሎች ላይ መፍረድ” (የወንጌል ርዕሶች topics.ChurchofJesusChrist.org) የሚገኙ አንዳንድ መርጃዎችን መጠቀም ትችላላችሁ።
-
ማቴዎስ 7፥24–27።ቤተሰባችሁ የአዳኙን የልባም ሰው እና የሰነፉ ሰው ምሳሌ ይበልጥ እንዲረዳ፣ ውሃ በአሸዋ ከዚያም በድንጋይ ላይ እንዲያፈስ ማድረግ ትችላላችሁ። መንፈሳዊ መሰረታችንን አለት ላይ እንዴት መገንባት እንችላለን?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልን ይመልከቱ።
በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “ልባሙ ሰው እና ሰነፉ ሰው፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 281።