አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ጥር 30–የካቲት 5 (እ.አ.አ) ማቴዎስ 4፤ ሉቃስ 4–5፦ “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው”


“ጥር 30–የካቲት 5 (እ.ኤ.አ)። ማቴዎስ 4፤ ሉቃስ 4–5፤ ‘የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—–ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ጥር 30–የካቲት 5 (እ.ኤ.አ)። ማቴዎስ 4፤ ሉቃስ 4–5፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ ምድረበዳ ላይ ቆሞ

ወደ ምድረበዳ፣ በኤቫ ኮሊቫ ቲሞቲ

ጥር 30–የካቲት 5 (እ.አ.አ)

ማቴዎስ 4ሉቃስ 4–5

“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው”

አዳኙ ሰይጣንን ለመቃወም እና ስለ እርሱ መለኮታዊ ተልዕኮ ለመመስከር ቅዱሳት መጻህፍትን ተጠቅሟል (ሉቃስ 4፥1–21ን ተመልከቱ)። ቅዱሳት መጻህፍት እምነታችሁን እና ፈተናን የመቋቋም ውሳኔያችሁን እንዴት መገንባት እንደሚችሉ አሰላስሉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ኢየሱስ ከልጅነቱ ጀምሮ ልዩ የተቀደሰ ተልዕኮ እንደነበረው የሚያውቅ ይመስል ነበር። ነገር ግን የምድር አገልግሎቱን ለመጀመር መዘጋጀት ሲጀምር ጠላት በአዳኙ አዕምሮ ጥርጣሬን ለመትከል ፈለገ። “የእግዚአብሔር ልጅ ሆርክ” አለ ሰይጣን (ሉቃስ 4፥3፣ ትኩረት ተጨምሮበታል)። ነገር ግን አዳኙ በሰማይ አባቱ ጋር ተነጋግሮ ነበር። ቅዱሳት መጻህፍትን እንዲሁም እርሱ ማን እንደነበር ያውቅ ነበር። ለእርሱ “ይህን ሥልጣን ሁሉ ለአንተ እሰጥሃለሁ” (ሉቃስ 4፥6) የሚለው የሰይጣን ስጦታ ባዶ ነበር፣ ምክንያቱም የአዳኙ የእድሜ ልክ ዝግጅት “[የመንፈስን] ሃይል” (ሉቃስ 4፥14) እንዲቀበል አድርጎት ነበርና። ምንም እንኳን ቢፈተን፣ ክፉ ቢገጥመው እና ቢጠላም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰጠው ስራ ፈጽሞ ፍንክች አላለም፦ “ስለዚህ ተልኬአለሁና … የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እሰብክ ዘንድ ይገባኛል” (ሉቃስ 4፥43)።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ማቴዎስ 4፥1–2

ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እንዳገለግለው ያዘጋጀኛል።

ለተልዕኮው ለመዘጋጀት ኢየሱስ “ከእግዚአብሔር ጋር ለመሆን” ወደ ምድረበዳ ሄደ (የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ማቴዎስ 4፥1 [በ ማቴዎስ 4፥1፣ የግርጌ ጽሁፍ  ])። ወደ እግዚአብሔር እንደቀረባችሁ እንዲሰማችሁ የምታደርጉትን ነገር አስቡ። ይህ እርሱ እንድትሰሩ ለሚፈልገው ስራ እንዴት ያዘጋጃችኋል?

ማርቆስ 4፥1–11ሉቃስ 4፥1–13

ኢየሱስ ክርስቶስ ፈተናን በመቋቋም ለእኔ ምሳሌ ሆኖኛል።

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በኃጢያት ሲፈተኑ ጥፋተኝነት ይሰማቸዋል። ነገር ግን “[ያለ ኃጥያት]” (ዕብራውያን 4፥15) የኖረው አዳኙ እንኳን ተፈትኗል። ኢየሱስ ክርስቶስ የሚገጥሙንን ፈተናዎች ያውቃል እንዲሁም እንድናሸንፋቸው ይረዳናል (ዕብራውያን 2፥18አልማ 7፥11–12 ተመልከቱ)።

እናንተ ማቴዎስ 4፥1–11 እና ሉቃስ 4፥1–13ን ስታነቡ፣ ፈተና ሲገጥማችሁ ሊረዳችሁ የሚችል ምን ነገር ተማራችሁ? ሀሳባችሁን እንደዚህ በሰንጠረዥ ማቀናጀት ትችላላችሁ።

ኢየሱስ ክርስቶስ

እኔ

ኢየሱስ ክርስቶስ

ክርስቶስን ለመፈተን ሰይጣን ምን አድርግ አለው?

እኔ

ሰይጣን ምን እንዳደርግ ሊፈትነኝ ይፈልጋል?

ኢየሱስ ክርስቶስ

ፈተናን ለመቋቋም ክርስቶስ እንዴት ተዘጋጀ?

እኔ

ፈተናን ለመቋቋም እንዴት መዘጋጀት እችላለሁ?

ኢየሱስ ክርስቶስ

እኔ

ከጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ማቴዎስ 4 ተጨማሪ ምን መረዳት አገኛችሁ? (ማቴዎስ 4 የግርጌ ጽሁፎችን ሙሉ ተመልከቱ)።

በተጨማሪም 1 ቆሮንቶስ 10፥13አልማ 13፥28ሙሴ 1፥10–22፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “ፈተናን ተመልከቱ፣” topics.ChurchofJesusChrist.org

ሉቃስ 4፥16–32

ኢየሱስ ክርስቶስ የተተነበየለት መሲህ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር የተላከው ለምንድነው ተብላችሁ ብትጠየቁ ምን ብላችሁ ትመልሳላችሁ? ኢሳይያስ ስለ መሲሁ ከተነበየው ትንቢቶች መካከል አንዱን በመጥቀስ አዳኙ ስለ እርሱ ተልዕኮ አብራርቷል (ሉቃስ 4፥18–19ኢሳይያስ 61፥1–2ን ተመልከቱ)። እነዚህን ጥቅሶች ስታነቡ ስለ እርሱ ተልዕኮ ምን ትማራላችሁ?

አዳኙ በእርሱ ስራ ላይ እንድትሳተፉ የሚጋብዛችሁ አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው?

ኢየሱስ በምኩራብ ውስጥ ቆሞ

ምንም እንኳን አይሁዶች የኢሳይያስ ትንቢት እንዲፈጸም ምዕተ–አመታትን ቢጠብቁም “ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ” ብሎ ሲናገር ብዙዎቹ ኢየሱስ መሲሁ እንደነበር አልተቀበሉም (ሉቃስ 4፥21)። ሉቃስ 4፥20–30 (በተጨማሪም ማርቆስ 6፥1–6ን ተመልከቱ) ስታነቡ ራሳችሁን ናዝሬት በነበሩ ሰዎች ቦታ ለማስቀመጥ ሞክሩ። ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛችሁ በሙላት እንዳትቀበሉ የሚከለክላችሁ ነገር አለ?

በተጨማሪም ሞዛያ 3፥5–12ን፤ “ክርስቶስ እርሱ መሲሁ እንደሆነ ተናገረ” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

3:24

ማቴዎስ 4፥18–22ሉቃስ 5፥1–11

በጌታ ስተማመን መለኮታዊ ብቃቴ ላይ እንድደርስ ይረዳኛል።

ኤዝራ ታፍት ቤንሰን እንዳስተማሩት፣ “ህይወታቸውን ለእግዚአብሔር አሳልፈው የሰጡ ሴቶች እና ወንዶች እነርሱ ከሚችሉ እጅግ የላቀ ነገር እርሱ በህይወታቸው ሊያደርግ እንደሚችል ያውቃሉ” (Teachings of Presidents of the Church: Ezra Taft Benson [የቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንቶች ትምህርቶች፤ ኤዝራ ታፍት ቤንሰን] [2014 (እ.አ.አ)]፣ 42)። አሁን ለስምኦን ጴጥሮስ እና መሰል አሳ አጥማጆች ይህ እንዴት እንደሆነ አስተውሉ። ክርስቶስ እነርሱ በራሳቸው ካዩት የበለጠ ነገር አየ። እነርሱን “የሰዎች አጥማጆች” ሊያደርጋቸው ፈለገ (ማቴዎስ 4፥19፤ በተጨማሪም ሉቃስ 5፥10ን ተመልከቱ)።

ማቴዎስ 4፥18–22 እና ሉቃስ 5፥1–11ን ስታነቡ፣ ኢየሱስ እንድትሆኑ እየረዳችሁ ያለውን ነገር አሰላስሉ። እንድትከተሉት ሲጋብዛችሁ እንዴት ነበር የተሰማችሁ? እርሱን ለመከተል ሁሉን ነገር እንደምትተዉ እንዴት ማሳየት ትችላላችሁ? (ሉቃስ 5፥11ን ተመልከቱ)።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ማቴዎስ 4፥1–2ሉቃስ 4፥1–2ከእነዚህ ጥቅሶች ስለ ጾም ሃይል ምን መረዳቶችን ልናገኝ እንችላለን? ቤተሰባችሁ ስለጾም እንዲማር እንዲረዳ በወንጌል ርዕሶች “ጾም እና የጾም በኩራት” መጠቀም ትችላችህ (topics.ChurchofJesusChrist.org)። የቤተሰብ አባላት ከጾም ጋር ያላቸውን ተሞክሮ ሊያካፍሉ ይችላሉ። ምናልባት በጸሎት በአንድነት ለአንድ የተለየ አላማ ለመጾም እቅድ ልታወጡ ትችላላችሁ።

ማቴዎስ 4፥3–4ሉቃስ 4፥3–4ሰይጣን ክርስቶስ ድንጋይን ወደ ዳቦ እንዲቀይር ሲጠይቅ “የእግዚአብሔር ልጅ ሆርክ” በማለት የክርስቶስን መለኮታዊ ማንነት ፈተነ (ማቴዎስ 4፥3፣ ትኩረት ተጨምሮበታል)። ሰይጣን የእኛን እና የአዳኙን መለኮታዊ ማንነት እንድንጠራጠር ለማድረግ የሚሞክረው ለምድን ነው? ይህን ለማድረግ የሚሞከረው እንዴት ነው? (በተጨማሪም ሙሴ 1፥10–23ን ተመልከቱ።)

የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ማቴዎስ 4፥11ኢየሱስ በአካል እና በመንፈስ ከተፈተነ በኋላ፣ ሃሳቡ እስር ቤት ወደነበረው መጥምቁ ዮሐንስ ዞረ “አሁን መጥምቁ ዮሐንስ አልፎ እንደተሰጠ አወቀ እናም መላእክትን ላከ፣ እነሆ መላእክትን ቀርበው ያገለግሉት [ዮሐንስን] ነበር” (የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ማቴዎስ 4፥11 [በማቴዎስ 4፥11፣ የግርጌ ጽሁፍ  )። የክርስቶስ ስለሌሎች የሚያስብበትን ምሳሌ ስንከተል እንዴት ነው የምንባረከው?

ሉቃስ 4፥16–21ልቡ የተሰበረን ወይም “ነጻ [መውጣት]” ያለበትን ሰው ታውቃላችሁን? (ሉቃስ 4፥18)። ሌሎች የአዳኙን ፈውስ እና ቤዛነት እንዲቀበሉ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው ? በተጨማሪም የቤተመቅደስ ስርዓቶችን መፈጸም “ለታሰሩት መፈታት” እንዴት እንደሚያመጣ መወያየት ትችላላችሁ (ሉቃስ 4፥18)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ተመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “ኑ፣ ተከተሉኝ፣” መዝሙሮች፣ ቁ. 116።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ኑሩ። “(እንደ ወላጅ እና አስተማሪ) ምናልባት ልታደርጉት የምትችሉት በጣም አስፈላጊው ነገር … በሙሉ ልባችሁ ወንጌልን መኖር ነው። የመንፈስ ቅዱስን ወዳጅነት ለማግኘት ብቁ ለመሆን ዋነኛው መንገድ ይህ ነው። በትጋት መሞከር—እንዲሁም ስትሰናከሉ በአዳኙ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ይቅርታን መለመን እንጂ ፍጹም መሆን አይጠበቅባችሁም” (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር]፣ 13)።

ኢየሱስ ሐዋርያት የሰዎች አጥማጆች እንዲሆኑ ሲጠራቸው

ክርስቶስ ሐዋርያት ያዕቆብን እና ዮሐንስን እየጠራ፣ ኤድዋርድ አርሚቴጅ (1817–96)/Sheffield Galleries and Museums Trust, UK/© Museums Sheffield/The Bridgeman Art Library International