አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ጥር 23–29 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 3፤ ማርቆስ 1፤ ሉቃስ 3፦ “የጌታን መንገድ አዘጋጁ”


“ጥር 23–29 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 3፤ ማርቆስ 1፤ ሉቃስ 3፤ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ጥር 23–29 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 3፤ ማርቆስ 1፤ ሉቃስ 3፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

መጥምቁ ዮሀንስ ኢየሱስን ሲያጠምቅ

ባለቀለም መስታወት መስኮት በናቩ ኢለኖይስ ቤተመቅደስ፣ በቶም ሆልድማን

ጥር 23–29 (እ.አ.አ)

ማቴዎስ 3ማርቆስ 1ሉቃስ 3

“የጌታን መንገድ አዘጋጁ”

ማቴዎስ 3ማርቆስ 1፤ እና ሉቃስ 3ን በማንበብ ጀምሩ። እነዚህን ምዕራፎች ለመረዳት መንፈስ ቅዱስ እንዲያግዛችሁ ጸልዩ፤ እርሱም ለእናንተ የተለየ መረዳትን ይሰጣችኋል። እነዚህን ስሜቶች መዝግቡ እናም ለመተግበር እቅድ አውጡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ኢየሱስ ክርስቶስ እና ወንጌሉ ሊለውጧችሁ ይችላሉ። የአዳኙ መምጣት ስለሚያመጣው ለውጥ የጥንት ነቢይ ኢሳይያስ “አዘቅቱ ሁሉ ይሙላ፣ ተራራው እና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፣ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሁን፥ ሸካራውም መንገድ የቀና ይሁን” በማለት የተነበየውን ሉቃስ ጠቅሷል (ሉቃስ 3፥5፤ በተጨማሪም ኢሳይያስ 40፥4 ተመልከቱ)። ይህ መልዕክት ለሁላችንም ነው፤ ለመቀየር አንችልም ብለው ለማያስቡትም ጭምር። እንደ ተራራ የጸና ነገር ሜዳ መሆን የሚችል ከሆነ፣ ጌታ የጠመመውን መንገዳችንን ማቅናት እንድንችል ሊረዳን ይችላል (ሉቃስ 3፥4–5ን ተመልከቱ)። የመጥምቁ ዮሃንስን የንስሃ እና የለውጥ ግብዣን ስንቀበል፣ እኛም “የእግዚአሔርን ማዳን [ማየት]” እንችል ዘንድ ክርስቶስን ለመቀበል አዕምሯችንን እና ልባችንን እናዘጋጃለን (ሉቃስ 3፥6)።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ማርቆስ ማን ነበር?

ከሌሎች የወንጌል ጸሃፊያን አንጻር ስለ ማርቆስ ጥቂት ነው የምናውቀው። የጳውሎስ፣ የጴጥሮስ እና የተለያዩ ምስዮናውያን የተልዕኮ ተጓዥ ጓደኛ እንደነበር እናውቃለን። ብዙ የመፅሐፍ ቅዱስ ምሁራን ማርቆስ ስለ አዳኙ ህይወት እንዲጽፍ በጴጥሮስ መመሪያ እንደተሰጠው ያምናሉ። የማርቆስ ወንጌል ከሌሎቹ ወንጌላት ቀድሞ የተጻፈ ሊሆንም ይችላል።

በተጨማሪም “ማርቆስ”ን በBible Dictionary (የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት] ውስጥ ተመልከቱ።

ማቴዎስ 3፥1–12ማርቆስ 1፥1–8ሉቃስ 3፥2–18

ንስሃ ሃያል የሆነ የአዕምሮ እና የልብ ለውጥ ነው።

የመጥምቁ ዮሃንስ ተልዕኮ ሰዎች አዳኙን እንዲቀበሉ እና ይበልጥ እርሱን እንዲመስሉ ልባቸውን ለማዘጋጀት ነበር። ይህን ያደረገው እንዴት ነው? “ንስሃ ግቡ” በማለት አወጀ (ማቴዎስ 3፥2)። ስለ ንስሃ ለማስተማር እንደ ፍሬ እና ስንዴ ያሉ ምሳሌዎችን ተጠቅሟል (ሉቃስ 3፥9፣ 17ን ተመልከቱ)።

በመጥምቁ ዮሃንስ አገልግሎት ጽሁፎች ላይ ሌሎች ምን ምሳሌዎችን አገኛችሁ? (ማቴዎስ 3፥1–12ማርቆስ 1፥1–8ሉቃስ 3፥2–18ን ተመልከቱ)። እነዚህንም በቅዱሳት መጻህፋችሁ ላይ ምልክት ማድረግን ወይም ስዕል መሳልን አስቡ። እነዚህ ምስሎች ስለ ንስሃ ትምህርት እና አስፈላጊነት ምን ያስተምራሉ?

እውነተኛ ንስሃ “የአዕምሮ መለወጥ፣ እንዲሁም ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ራስ እና ስለ አለም አዲስ እይታ ማግኘት ማለት ነው። … [ይህም] ልብን እና የግል ፈቃድን ለእግዚአብሔር መለወጥ [ማለት ነው]” (Bible Dictionary [የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት]፣ “ንስሃ”)። በሉቃስ 3፥7–14 ላይ ዮሃንስ ሰዎች ክርስቶስን ለመቀበል እንዲዘጋጁ ምን አይነት ለውጥ እንዲያመጡ ጋብዟል? እነዚህ ምክሮች ለእናንተ ሊሆኑ የሚችሉት እንዴት ነው? በእውነት ንስሃ መግባታችሁን እንዴት ማሳየት ትችላላችሁ? ( ሉቃስ 3፥8ን ተመልከቱ)።

በተጨማሪም ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “የተሻለ ማድረግ እና የተሻለ መሆን እንችላለን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት2019 (እ.አ.አ)፣ 67–69፤ ዳለን ኤች. ኦክስ “በንስሃ መንጻት፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 91–94 ተመልከቱ።

ማቴዎስ 3፥7ሉቃስ 3፥7

ፈሪሳውያን እና ሰዱቃውያን እነማን ነበሩ?

ፈሪሳውያን የሙሴን ህጎች እና ስርዓቶች አጥብቀው በማክበራቸው የሚኮሩ የአይሁድ እምነት አባላት ናቸው። ሰዱቃውያን ደግሞ ትልቅ ሃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ያላቸው ባለጠጋ የአይሁድ ማህበረሰብ ክፍል ናቸው፤ በትንሳኤ ትምህርት አያምኑም። ሁለቱም ቡድኖች ከቀዳሚው የእግዚአብሔር ህጎች አላማ አፈንግጠው ነበር።

በተጨማሪም ማቴዎስ 23፥23–28ን ተመልከቱ፤ Bible Dictionary [የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት] “ፈሪሳውያን፣” “ሰዱቃውያን።”

ማቴዎስ 3፥11፣ 13–17ማርቆስ 1፥9–11ሉቃስ 3፥15–16፣ 21–22

ኢየሱስ ክርስቶስ “ጽድቅን ሁሉ [ለመፈጸም]“ ተጠመቀ።

እናንተ በተጠመቃችሁ ጊዜ የአዳኙን ምሳሌ ተከትላችኋል። ስለ አዳኙ ጥምቀት ከተጻፉ ጽሁፎች የተማራችሁትን በራሳችሁ ጥምቀት ከተከሰቱ ነገሮች ጋር አነጻጽሩ።

የአዳኙ ጥምቀት

የእኔ ጥምቀት

የአዳኙ ጥምቀት

ኢየሱስን ማን አጠመቀው እናም ምን አይነት ስልጣን ነበረው?

የእኔ ጥምቀት

እናንተን ማን አጠመቃችሁ? ምን አይነት ስልጣን ነበረው?

የአዳኙ ጥምቀት

ኢየሱስ የተጠመቀው የት ነበር?

የእኔ ጥምቀት

እናንተ የት ነበር የተጠመቃችሁት?

የአዳኙ ጥምቀት

ኢየሱስ እንዴት ነበር የተጠመቀው?

የእኔ ጥምቀት

እናንተ እንዴት ነበር የተጠመቃችሁት?

የአዳኙ ጥምቀት

ኢየሱስ ለምን ነበር የተጠመቀው?

የእኔ ጥምቀት

እናንተ ለምን ተጠመቃችሁ?

የአዳኙ ጥምቀት

የሰማይ አባት በኢየሱስ ደስ እንደሚለው ያሳየው እንዴት ነው?

የእኔ ጥምቀት

እናንተ ስትጠመቁ የሰማይ አባት በእናንተ ደስ እንደተሰኘ እንዴት አሳየ? ከዚያን ጊዜ በኋላ የእርሱን ማረጋገጫ እንዴት አሳየ?

በተጨማሪም 2 ኔፊ 31ሞዛያ 18፥8–11ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥37፣ 68–74፤ “የኢየሱስ ጥምቀት” (ቪዲዮ)፣ ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

2:54

ማቴዎስ 3፥16–17ማርቆስ 1፥9–11ሉቃስ 3፥21–22

የአምላክ አባላት ሶስት የተለያዩ ፍጥሮች ናቸው።

የአምላክ አባላት ሶስት የተለያዩ ፍጥሮች ስለመሆናቸው መፅሐፍ ቅዱስ ብዙ ማስረጃዎችን ይዟል። የአዳኙ ጥምቀት አንዱ ምሳሌ ነው። እነዚህን ምዕራፎች ስታነቡ፣ ስለ አምላክ የምትማሩትን አሰላስሉ። እነዚህ ትምህርቶች ለእናንተ አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው?

በተጨማሪም ዘፍጥረት 1፥26ማቴዎስ 17፥1–5ዮሐንስ 17፥1–3የሐዋርያት ስራ 7፥55–56ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥22ን ተመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ማቴዎስ 3መጥምቁ ዮሐንስ የአሮናዊ የክህነት ስልጣን ነበረው። ከዮሐንስ ምሳሌነት ስለአሮናዊ ክህነት አገልግሎት ምን መማር እንችላለን? በአሮናዊ ክህነት አማካኝነት ምን በረከቶችን ልንቀበል እንችላለን? ቤተሰባችሁ ውስጥ ወጣት ወንድ ካለ አሮናዊ ክህነትን በመጠቀም እንዴት ሌሎችን ለመባረክ እንደሚችል መረዳት እንዲችል ልትረዱት ትችላላችሁ። (በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፥120፥46–60ን ተመልከቱ)።

ወጣት ወንድ ሌላ ሰውን እያጠመቀ

እኛ ስንጠመቅ ኃጢያቶቻችን ይታጠባሉ።

ማቴዎስ 3፥11–17ማርቆስ 1፥9–11ሉቃስ 3፥21–22 የቤተሰባችሁ አባላት አንድ ሰው ሲጠመቅ ወይም የቤተክርስትያን አባል ሆኖ ሲረጋገጥ አይተው ያውቃሉ? የቤተሰባችሁ አባላት ምን ተሰማቸው? ምናልባት ስለ ጥምቀት እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ መቀበል ምሳሌነት ልታስተምሯቸው ትችላላችሁ። መጠመቅ እና መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንዴት እንደ አዲስ እንደ መወለድ የሚሆው? በጥምቀት ጊዜ ሰውነታችን ሙሉ በሙሉ ውሃ ውስጥ እንዲጠልቅ የሚደረገው ለምንድን ነው? በጥምቀት ጊዜ ነጭ የምንለብሰው ለምንድነው? የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ “በእሳት መጠመቅ” ተብሎ የተገለጸው ለምንድን ነው? (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥41፤ በተጨማሪም Bible Dictionary [የመፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት]፣ “ጥምቀት፣” “መንፈስ ቅዱስ”ን ተመልከቱ)።

ማቴዎስ 3፥17ማርቆስ 1፥11ሉቃስ 3፥22 እግዚአብሔር በእኛ ተደስቶ እንደነበር የተሰማን መቼ ነበር? እንደ ቤተሰብ እግዚአብሔርን ለማስደሰት ምን ማድረግ እንችላለን?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልን ተመልከቱ።

በሃሳብ ተቀራራቢ መዝሙር፦ “ጥምቀት፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ ቁጥር 100–101።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ጌታን ለእርዳታ ጠይቁ። ቅዱሳት መጻህፍት የተሰጡት በመገለጥ ነው፣ እናም እነርሱን ለመረዳት ግላዊ መገለጥ ያስፈልገናል። ጌታ እንዲህ ሲል ቃል ገብቷል፣ “ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል” (ማቴዎስ 7፥7)።

መጥምቁ ዮሀንስ ኢየሱስን ሲያጠምቅ

መጥምቁ ዮሀንስ ኢየሱስን ሲጠምቅ፣ በግሬግ ኬ. ኦልሰን