አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ጥር 9–15 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 2፤ ሉቃስ 2፦ ልንሰግድለት መጥተናል


“ጥር 9–15 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 2፤ ሉቃስ 2፦ ልንሰግድለት መጥተናል፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ጥር 9–15 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 2፤ ሉቃስ 2፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ሰብአ ሰገል በግመል ላይ ሲጓዙ

እናምልከው፣ በዴና ማሪዮ ዉድ

ጥር 9–15 (እ.አ.አ)

ማቴዎስ 2ሉቃስ 2

ልንሰግድለት መጥተናል

ማቴዎስ 2 እና ሉቃስ 2ን ስታነቡ ለምትቀበሉት ማንኛውም መንፈሳዊ መረዳት ትኩረት ስጡ። በዚህ የመማርያ ረቂቅ ውስጥ ያሉ የመማርያ ሃሳቦች በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ያሉትን አንዳንድ አስፈላጊ መርሆዎች ለመለየት ይረዷችኋል።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ከመወለዱ ቀን ጀምሮ ኢየሱስ የተለመደ አይነት ልጅ እንዳልነበር ግልጽ ነበር። የኢየሱስን ህጻንነት ጊዜ የሚታወስ ያደረገው በሰማይ የነበረው አዲስ ኮከብ ወይም በደስታ የተሞላው የመልአክ አዋጅ ብቻ አልነበረም። ከተለያዩ ሃገራት፣ የስራ ዘርፍ እና የኋላ ታሪክ የነበራቸው ታማኝ የነበሩ የተለያዩ ሰዎች፣ ወዲያው ወደ እርሱ መሳባቸውም ጭምር ነበር። እርሱ “ኑ፣ ተከተሉኝ” የሚለውን ግብዣ ከማስተላለፉ በፊት እነርሱ መጡ (ሉቃስ 18፥22)። በእርግጥ ወደ እርሱ የመጡት ሁሉም ሰዎች አልነበሩም። ልብ ያላሉት ብዙዎች ነበሩ፣ እንዲሁም በቅናት የተሞላ ገዢ ህይወቱን ሊያጠፋ ፈለጎ ነበር። ነገር ግን ትሁት፣ ንጹህ፣ ታማኝ የጽድቅ ፈላጊዎች ማን እንደሆነ አወቁት—ቃል የተገባላቸው መሲህ። የእነርሱ ታማኝነት የእኛን ያነሳሳል፥ ምክንያቱም ለእረኞች የመጣው “ታላቅ ደስታ የምስራች” እንዲሁም “ለህዝብ ሁሉ የሚሆን” ነበር፣ እናም በዚያች ቀን “መድሃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ” ለሁላችንም ተወለደ (ሉቃስ 2፥10–11ን ተመልከቱ)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ሉቃስ 2፥1–7

ኢየሱስ ክርስቶስ አነስተኛ በሆነ ሁኔታ ነበር የተወለደው።

ምንም እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስ “አለም ሳይፈጠር” ከእግዚአብሔር አብ ጋር ክብር ቢኖረውም (ዮሃንስ 17፥5)፣ ተራ በሆነ ሁኔታ ለመወለድ እና በመካከላችን በምድር ለመኖር ፈቃደኛ ሆነ። እናንተ ሉቃስ 2፥1–7ን ስታነቡ፣ ስለመወለዱ የሚናገረው ይህ ታሪክ ስለ እርሱ ምን እንደሚያስተምር አሰላስሉ። ከዚህ በፊት ልብ ያላላችሁትን ማብራርያዎች ወይም መረዳቶች ከዚህ ታሪክ ለማግኘት ሞክሩ። ለእነዚህ ነገሮች ትኩረት መስጠት ለእርሱ ያላችሁን ስሜት እንዴት ይቀይራል?

በተጨማሪም “ህጻኑ ኢየሱስ” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ።

ማቴዎስ 2፥1–12ሉቃስ 2፥8–38

ስለክርስቶስ መወለድ ብዙ ምስክሮች አሉ።

የክርስቶስ ልደት እና ህጻንነት ወቅት ከተለያዩ የህይወት ክፍል በመጡ ምስክሮች እና አምላኪዎች የተሞላ ነበር። ታሪካቸውን ስትዳስሱ፣ ስለአምልኮ እና ስለ ክርስቶስ መመስከርያ መንገዶች ምን ትማራላችሁ?

የክርስቶስ ምስክር

ስለ ክርስቶስ አምልኮ እና መመስከር ምን እማራለሁ?

የክርስቶስ ምስክር

እረኞች (ሉቃስ 2፥8–20)

ስለ ክርስቶስ አምልኮ እና መመስከር ምን እማራለሁ?

የክርስቶስ ምስክር

ስምኦን (ሉቃስ 2፥25–35)

ስለ ክርስቶስ አምልኮ እና መመስከር ምን እማራለሁ?

የክርስቶስ ምስክር

ሐና (ሉቃስ 2፥36–38)

ስለ ክርስቶስ አምልኮ እና መመስከር ምን እማራለሁ?

የክርስቶስ ምስክር

ሰብአ ሰገል (ማቴዎስ 2፥1–12)

ስለ ክርስቶስ አምልኮ እና መመስከር ምን እማራለሁ?

በተጨማሪም 1 ኔፊ11፥13–233 ኔፊ 1፥5–21፤ “እረኞች ስለክርስቶስ መወለድ ተማሩ” (ቪዲዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ።

ማቴዎስ 2፥13–23

ቤተሰባቸውን ለመጠበቅ ወላጆች መገለጥን ሊቀበሉ ይችላሉ።

ዮሴፍ ያለ ሰማያት እርዳታ ኢየሱስን በልጅነቱ እንዲጠብቅ የተጠየቀውን ማድረግ አይችልም ነበር። እንደ ሰብአ ሰገልም፣ አደጋ እንዳለ የማስጠንቀቅያ መገለጥን ተቀበለ። እናንተ ስለ ዮሴፍ ልምድ ማቴዎስ 2፥13–23ን ስታነቡ፣ ዛሬ ስለሚያጋጥሙን አካላዊ እና መንፈሳዊ አደጋዎች አስቡ። እናንተን እና የምትወዷቸውን ለመጠበቅ የእግዚአብሔር ምሬት የተሰማችሁ ጊዜን አሰላስሉ። ይህን ተሞክሮ ለሌሎች ለማካፈል ሞክሩ። እንዲህ አይነት ምሪት ወደፊት ለመቀበል ምን ማድረግ አለባችሁ?

በተጨማሪም ዮሴፍ የእግዚአብሔር ልጅን የመንከባከብ ሃላፊነት ሲሰጠው የተሰማውን ለመገመት፣ “የመጀመርያው ገና መንፈስ” የተሰኘውን ቪድዮ መመልከት ትችላላችሁ (ChurchofJesusChrist.org)።

ሉቃስ 2፥40–52

ኢየሱስ በልጅነቱ እንኳን ትኩረቱ የአባቱን ፈቃድ መፈጸም ላይ ነበር።

እንደ ታዳጊ ወንድ፣ አዳኙ ወንጌልን በሃይል ሲያስተምር በቤተመቅደስ የነበሩ አስተማሪዎች እንኳን “በማስተዋሉ እና በመልሱ” (ሉቃስ 2፥47) ተደንቀው ነበር። ከእነዚህ ጥቅሶች ስለአዳኙ ልጅነት ምን ትማራላችሁ? እናንተ የምታውቋቸው ወጣት ልጆች “[በአባታቸው] ቤት ይሆኑ ዘንድ” የሚሞክሩት እንዴት ነው? (ሉቃስ 2፥49)። ወጣቶች እና ህጻናት የጠለቀ የወንጌል መረዳት እንዲኖራችሁ የረዷችሁ እንዴት ነው? በሉቃስ 2፥40–52 እና በ የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ማቴዎስ 3፥24–26 (በመጽሐፍ ቅዱስ መግለጫ) ላይ ካለው የኢየሱስ ምሳሌነት ተጨማሪ ምን ትማራላችሁ?

ምስል
ኢየሱስ እንደ ታዳጊ ወንድ በቤተመቅደስ ውስጥ ካሉ አስተማሪዎች ጋር

“በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን?” (ሉቃስ 2፥49)።

የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ምንድነው?

“ብዙ ግልጽ እና የከበሩ” እውነቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ በምዕተ አመታት ውስጥ ጠፍተው ስለነበር (1 ኔፊ 13፥28፤ በተጨማሪም ሙሴ 1፥41ን ተመልከቱ) ጌታ ጆሴፍ ስሚዝ በመንፈስ የተመራ የመጽሐፍ ቅዱስ ክለሳ እንዲያደርግ አዝዞት ነበር፣ ይህም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ይባላል። በነቢዩ የተደረጉ ብዙ ክለሳዎች በኋለኛው ቀን ቅዱሳን ቅዱሳት መጻህፍት እትም መግለጫዎች ውስጥ ይገኛሉ። የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ማቴዎስ 24፣ እንዲሁም ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ በመባል የሚያወቀው፣ በታላቅ ዋጋ እንቁ ውስጥ ይገኛል። ለበለጠ መረጃ “የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም (ጆ.ስ.ት)”ን በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት እና የወንጌል ርዕሶች ጽሁፍ “መጽሐፍ ቅዱስ፣ ስህተት አልባ” (topics.ChurchofJesusChrist.org) ተመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ሉቃስ 2የቤተሰባችሁ አባላት በሉቃስ 2 ላይ የተገለጸን አንድ ሰው እንዲመርጡ፣ ያ ሰው ከአዳኙ ጋር ስለነበረው ግንኙነቶች ጥቂት ጥቅሶችን እንዲያነቡ፣ እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት እንዲጨምር የረዳቸውን የተማሩትን የሆነ ነገር እንዲያካፍሉ ጋብዙ። “የማርያም መዝሙር” ወይም “የክርሥቶስ ልደት መዝሙር” በአንድነት ዘምሩ (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 44–45፣ 52–53)። ከእነዚህ መዝሙሮች ስለአዳኙ መወለድ ምን እንማራለን?

የጥበብ ስራ ስለ ክርስቶስ ልደት ውይይታችሁን እንዴት ሊረዳ እንደሚችል አስቡ። (ለምሳሌ የወንጌል ጥበብ መጽሃፍ ወይም history.ChurchofJesusChrist.org/exhibit/birth–of–Christን ተመልከቱ።)

የማቴዎስ 2፥1–12አዳኙን ስለመፈለግ እና ማግኘት ከሰብአ ሰገል ተምሳሌትነት ምን እንማራለን?

ሉቃስ 2፥41–49“[በአባት] ቤት መሆን” ምንድነው? (ሉቃስ 2፥49ሙሴ 1፥39General Handbook: Serving in The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints [ጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል]1.2ChurchofJesusChrist.org ተመልከቱ)። በሉቃስ 2፥41–49 ካለው ታሪክ ውስጥ [በአባት] ቤቱ ስለመሆን ምን እንማራለን? ቤተሰባችሁ በአብ ስራ ሊሳተፉ የሚችሉበትን መንገዶች ለመጻፍ አስቡ እናም በማሰሮ ላይ አኑሩት። በሚቀጥለው ሳምንት ቤተሰባችሁ በሰማይ አባት ስራ ላይ ለመርዳት መንገድ ሲፈልግ፣ ከማሰሮው ላይ ሀሳቦችን መምረጥ ይችላሉ። ተሞክሯችሁን የምታካፍሉበትን ጊዜ አቅዱ።

ሉቃስ 2፥52ኢየሱስ በህይወቱ እንዴት እንዳደገ ከሉቃስ 2፥52 ምን እንማራለን? “በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት” ለማደግ በግል እና እንደ ቤተሰብ ልናስቀምጥ የምንችላቸው ግቦች ምንድን ናቸው?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልን ተመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “ከዋክብት እያበሩ ነበር፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 37።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት መርጃን ይጠቀሙ። ቅዱሳት መጻህፍትን ስታነቡ ተጨማሪ መረዳትን ለማግኘት፣ የርዕስ መመርያየመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትየቅዱሳት መጻህፍት መመርያ፣ እና በChurchofJesusChrist.org የሚገኙ ሌሎች ለጥናት የሚረዱ ምንጮችን ይጠቀሙ።

ምስል
ማርያም፣ ዮሴፍ እና ህፃኑ ኢየሱስ

የአለም አዳኝ ዝቅተኛ በሆነ መንገድ ወደ ምድር መጣ።

አትም