አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ጥር 2–8 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 1፤ ሉቃስ 1፦ “እንደ ቃልህ ይሁንልኝ”


“ጥር 2–8 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 1፤ ሉቃስ 1፦ ‘እንደ ቃልህ ይሁንልኝ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ጥር 2–8 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 1፤ ሉቃስ 1፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ማርያም እና ኤልሳቤጥ

ጥር 2–8 (እ.አ.አ)

ማቴዎስ 1ሉቃስ 1

“እንደ ቃልህ ይሁንልኝ”

ማቴዎስ 1 እና ሉቃስ 1ን ስታነቡ እና ስታሰላስሉ፣ የምትቀበሉትን መንፈሳዊ ግንዛቤዎች መዝግቡ። ምን ትምህርታዊ እውነቶች አገኛችሁ? ለእናንተና ለቤተሰባችሁ ትልቅ ዋጋ የሚኖራቸው የትኞቹ መልዕክቶች ናቸው? በዚህ ረቂቅ ላይ ያሉ የመማርያ ሃሳቦች ተጨማሪ መረዳት እንድታገኙ ሊረዷችሁ ይችላሉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ከስጋ ለባሽ እይታ ይህ የማይቻል ነው። ድንግል ወይም ልጅ የመውለድ ጊዜዋ ያለፈባት መካን ሴትም እንደዚያው ልትጸንስ አትችልም። ነገር ግን እግዚአብሔር ለልጁ እና ለመጥምቁ ዮሃንስ መወለድ እቅድ ነበረው፣ ስለዚህ ማርያም እና ኤልሳቤጥ ሁለቱም ምድር ላይ ባልተለመደ መልኩ እናቶች ሆኑ። የማይሆን የሚመስል ነገር ሲገጥመን የእነሱን ተአምራዊ ክስተቶች ማሰብ ሊጠቅመን ይችላል። ድክመቶቻችንን የማሸነፍ ችሎታ አለንን? ምላሽ የማይሰጥ የቤተሰብ አባልን ልብ የመንካት ችሎታ አለንን? ገብርኤል ማርያምን “ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም” ብሎ ሲያስታውሳት በቀላሉ ለእኛ እየተናገረን ሊሆን ይችላል (ሉቃስ 1፥37)። እግዚአብሔር ፈቃዱን ሲያሳውቀን ምላሻችን እንደ ማርያም፣ “እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” መሆን ይችላል (ሉቃስ 1፥38)።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ማቴዎስ እና ሉቃስ እነማን ነበሩ?

ኢየሱስ ከሐዋርያቱ እንደ አንዱ የጠራው ማቴዎስ አይሁዳዊ ቀራጭ ወይም ግብር ሰብሳቢ ነበር (ማቴዎስ 10፥3ን ተመልከቱ፤ በተጨማሪም የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት “ቀራጮች”ን ተመልከቱ)። ማቴዎስ ወንጌሉን የጻፈው ለአይሁድ ባልንጀሮቹ ነበር፤ ስለዚህ በኢየሱስ ህይወት እና አገልግሎት ላይ የተፈጸሙ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ላይ ትኩረት ለመስጠት መረጠ።

ሉቃስ ከሐዋርያው ጵውሎስ ጋር ይጓዝ የነበረ አህዛብ (አይሁድ ያልሆነ) ሃኪም ነበር። ከአዳኙ ሞት በኋላ ወንጌሉን የጻፈው አይሁድ ላልነበሩት አድማጪዎች ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ የአህዛብ እንዲሁም የአይሁዶች አዳኝ እንደሆነ መሰከረ። በአዳኙ ህይወት ትዕይንቶች ውስጥ የአይን እማኞችን ምስክርነት መዝግቧል እናም ከሌሎች ወንጌሎች ጋር ሲነጻጸር ሴቶችን ያካተቱ ታሪኮችን በይበልጥ ይዟል።

በተጨማሪም የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገብ ቃላትን “ወንጌሎች፣” “ማቴዎስ፣” “ሉቃስ” ተመልከቱ።

ማቴዎስ 1፥18–25ሉቃስ 1፥26–35

ኢየሱስ ክርስቶስ ከሟች እናት እና ከማይሞት አባት ተወለደ።

ማቴዎስ 1፥18–25 እና ሉቃስ 1፥26–35 ውስጥ፣ ማቴዎስ እና ሉቃስ የኢየሱስን መወለድ ተአምር እንዴት እንደገለጹ አስተውሉ። የእነርሱ ገለጻዎች በአዳኙ ላይ ያላችሁን እምነት እንዴት ያጠናክራሉ? ኢየሱስ የእግዚአብሔር እንዲሁም የማርያም ልጅ መሆኑን ማወቁ ለእናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን እዲህ ገልጸዋል፣ “የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ “ለሞት በማይገዛ ዘለአለማዊ ግለሰብ የግል መሥዋዕትነት ያስፈልገዋል። ሆኖም መሞት እና ሰውነቱን ዳግም ማስነሳት ነበረበት። አዳኙ ብቻ ነበር ይህንን ሊያከናውን የሚችለው። ከእናቱ የመሞትን ሃይል ወረሰ። ከአባቱ በሞት ላይ ሃይልን አገኘ” (“[Constancy amid Change] በለውጥ መሃል ቋሚነት፣” ኤንዛይን፣ ህዳር 1993 (እ.አ.አ)፣ 34)።

ሉቃስ 1፥5–25፣ 57–80

የእግዚአብሔር በረከቶች በእርሱ ጊዜ ይመጣሉ።

ራሳችሁን በረከት ለማግኘት እየጠበቃችሁ ካገኛችሁ ወይም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን እየሰማ እንዳልሆነ ከተሰማችሁ፣ የኤልሳቤጥ እና የዘካርያስ ታሪክ እግዚአብሔር እንዳልረሳችሁ ማስታወሻ ሊሆናችሁ ይችላል። ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ እንዲህ ቃል ገብተዋል፦ “ስለዚህ አብረን ስንሰራ እና ለአንዳንዶቹ ጸሎቶቻችን መልስ ስንጠብቅ፣ እነርሱ እንደሚሰሙ እና ምናልባት በወቅቱ ወይም በፈለግነው መንገድ ባይሆንም እንደሚመለሱ የእኔን ሐዋርያዊ ቃል እሰጣችኋለሁ። ነገር ግን እነርሱ ሁል ጊዜ መልስ የሚሰጡበት ሁሉን አዋቂ እና ለዘለአለም ርህሩህ የሆነው ወላጅ በወቅቱ በሚሰጥበት መልስ ነው” (“ጌታን መጠበቅ፣” ሊያሆና፣ ጥቅምት 2020 (እ.አ.አ)፣ 115–16)። ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ ታማኝ ሆነው የቆዩት እንዴት ነው? (ሉቃስ 1፥5–25፣ 57–80ን ተመልከቱ)። ራሳችሁን በረከት እየጠበቃችሁ ታገኛላችሁን? በምትጠብቁበት ወቅት ጌታ ከእናንተ ምን እንደሚጠብቅ ይሰማችኋል?

ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ ከህጻኑ ዮሐንስ ጋር

በታማኝነት ከጠበቁ በኋላ ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ በወንድ ልጅ ተባረኩ።

ማቴዎስ 1፥18–25ሉቃስ 1፥26–38

ታማኝ የሆነ በፈቃደኝነት በእግዚአብሔር ፈቃድ ይገዛል።

እንደ ማርያም አንዳንድ ጊዜ ለህይወታችን የእግዚአብሔር እቅድ እኛ ካቀድነው የተለየ ሆኖ ልናገኘው እንችላለን። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለመቀበል ከማርያም ምን ትማራላችሁ? በሚከተሉት ሰንጠረዦች የመልአኩ እና የማርያም ንግግሮችን (ሉቃስ 1፥26–38ን ተመልከቱ)፣ በንግግራቸው ከምታገኗቸው መልዕክቶች ጋር ጻፉ።

መልአኩ ለማርያም የተናገረው ቃል

ለእኔ የትሰጠ መልዕክት

መልአኩ ለማርያም የተናገረው ቃል

“ጌታ ከአንቺ ጋር ነው”(ቁጥር 28)።

ለእኔ የትሰጠ መልዕክት

ጌታ የእኔን ሁኔታ እና ትግሎች ያውቃል።

መልአኩ ለማርያም የተናገረው ቃል

ለእኔ የትሰጠ መልዕክት

መልአኩ ለማርያም የተናገረው ቃል

ለእኔ የትሰጠ መልዕክት

የማርያም ምላሽ

ለእኔ የትሰጠ መልዕክት

የማርያም ምላሽ

“ይህ እንዴት ይሆናል?” (ከቁጥር 34)።

ለእኔ የትሰጠ መልዕክት

የእግዚአብሔርን ፈቃድ ይበልጥ ለመረዳት ጥያቄዎችን መጠየቅ ተገቢ ነው።

የማርያም ምላሽ

ለእኔ የትሰጠ መልዕክት

የማርያም ምላሽ

ለእኔ የትሰጠ መልዕክት

ማቴዎስ 1፥18–25፣ ስለ ዮሴፍ የጽድቅ ምሳሌ ስታነቡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስለመቀበል ምን ትማራላችሁ? ከዘካርያስ እና ከኤልሳቤጥ ልምድ ተጨማሪ ምን ግንዛቤዎች ተምራችኋል? (ሉቃስ 1ን ተመልከቱ)።

በተጨማሪም ሉቃስ 22፥42ን ተመልከቱ፤ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት “ገብርኤል።”

ሉቃስ 1፥46–55

ማርያም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ተልዕኮ መስክራለች።

ሉቃስ 1፥46–55 ውስጥ የነበሩት የማርያም ቃላት ስለአዳኙ ተልዕኮ ገፅታዎች ቀድመው ተንብየዋል። ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከማርያም ንግግር ምን ተምራችኋል? እነዚህን ቁጥሮች ከ1 ሳሙኤል 2፥1–10 እና ከኢየሱስ ብፁዕና ማቴዎስ 5፥3–12 ጋር ማነጻጸር ትችላላችሁ። ጥቅሶቹን ስታሰላስሉ መንፈስ ምን ያስተምራችኋል?

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ማቴዎስ 1፥1–17ቤተሰባችሁ ስለ ኢየሱስ የዘር ግንድ ሲያነብ ስለራሳችሁ ቤተሰብ ታሪክ ልትወያዩ እንዲሁም ስለ ቅድመ አያቶቻችሁ አንዳንድ ታሪኮችን ልታካፍሉ ትችላላችሁ። የቤተሰብ ታሪካችሁን ማወቃችሁ ቤተሰባችሁን እንዴት ይባርካል? ለተጨማሪ የቤተሰብ ታሪክ ተግባራት FamilySearch.org/discovery ን ተመልከቱ።

ማቴዎስ 1፥20ሉቃስ 1፥11–13፣ 30በዚህ ጥቅስ ላይ የነበሩ ሰዎች ፈርተው የነበረው ለምን ይመስላችኋል? ምን እንድንፈራ ያደርገናል? እግዚአብሔር “አትፍሩ” ብሎ የሚጋብዘን እንዴት ነው?

ሉቃስ 1፥37“ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና” በሚለው ቤተሰባችሁ እምነትን መገንባት እንዲችል፣ ሉቃስ 1ን በአንድነት መመርመር እና እግዚአብሔር የማይቻል የሚመስሉ ነገሮችን ያስቻለበትን መፈለግ ትችላላችሁ። የማይቻል የሚመስሉ ነገሮችን እግዚአብሔር ያስቻለበትን ከቅዱሳት መጻህፍት ወይም ከራሳችን ልምድ ሌሎች ታሪኮችን ምን ማካፈል እንችላለን? የወንጌል ስዕል መጽሐፍ ውስጥ መመልከት ሃሳብ ሊሰጥ ይችላል።

ሉቃስ 1፥46–55አዳኙ ለእኛ ያደረጋቸው አንዳንድ “ታላቅ [ስራዎች]” ምንድን ናቸው? “[ጌታን ማክበር]” ለነፍሳችን ምን ማለት ሊሆን ይችላል?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀርብ መዝሙር “እርሱ ልጁን ላከ፣” የህጻናት መዝሙር መጽሐፍ፣ 34–35።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ቅዱሳት መጻህፍትን ከህይወታችሁ ጋር አመሳስሉ የቅዱሳት መጻህፍትን ጥቅስ ካነበባችሁ በኋላ የቤተሰብ አባላት በህይወታቸው እንዲኖሩት ጋብዟቸው (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር]፣ 21ን ተመልከቱ)። ለምሳሌ የቤተሰብ አባላት በማቴዎስ 1 እና ሉቃስ 1 ላይ ለጌታ ጥሪ ምላሽ ስለመስጠት የተማሩትን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ?

ገብርኤል ለማርያም ሲገለጥ

ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፣ በዋልተር ሬን