አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ጥር 16–22 (እ.አ.አ)። ዮሐንስ 1፦ መሲሁን አግኝተነዋል


“ጥር 16–22 (እ.አ.አ)። ዮሐንስ 1፦ መሲሁን አግኝተነዋል፣” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ጥር 16–22 (እ.አ.አ)። ዮሐንስ 1፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
አንዲት ሴት በባቡር ጣብያ ወንጌልን እያካፈለች

ጥር 16–22 (እ.አ.አ)

ዮሐንስ 1

መሲሁን አግኝተነዋል

እናንተ ዮሐንስ 1ን ስታነቡ እና ስታሰላስሉ ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ። ለእናንተና ለቤተሰባችሁ ጠቃሚ የሆነ ምን መልዕክት አገኛችሁ? በቤተክርስትያን ክፍሎቻችሁ ምን ማካፈል ትችላላችሁ?

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረ አገልግሎቱ ወቅት በህይወት ብትኖሩ የናዝሬቱን ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደነበር ማወቅ ትችሉ እንደሆን አስባችሁ ታውቃላችሁን? ለአመታት እንደ እንድርያስ፣ ጴጥሮስ፣ ፊሊጶስ እና ናትናኤል ያሉ ታማኝ እስራኤላውያን ቃል ለተገባለት መሲህ መምጣት ጠብቀዋል እንዲሁም ጸልየዋል። ከእርሱ ጋር ሲያገኙም፣ ሲፈልጉት የነበረው እርሱ እንደነበር እንዴት አወቁ? በተመሳሳይ መንገድ ሁላችንም አዳኙን እንደምናውቅውው—የእርሱን “መጥታችሁ እዩ” ግብዣን በመቀበል ነው (ዮሐንስ 1፥39)። በቅዱሳት መጻህፍት ስለ እርሱ እናነባለን። የእርሱን ትምህርት እንሰማለን። የእርሱን አኗኗር እንመለከታለን። የእርሱ መንፈስ ይሰማናል። እንደ ናትናኤልም በጉዞአችንም፣ አዳኙ እንደሚያውቀን እና እንደሚወደን እናም “የሚበልጥ ነገር” እንድናገኝ እንደሚያዘጋጀን እናውቃለን (ዮሐንስ1፥50)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ዮሐንስ ማን ነበር?

ዮሐንስ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዝሙር የነበረ፣ ኋላ ላይ ከኢየሱስ ክርስቶስ ቀዳሚ ተከታዮች እንዲሁም ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት መካከል አንዱ ነበር። እርሱ የዮሐንስ ወንጌል፣ ብዙ ደብዳቤዎች እና የራዕይ መፅሐፍ ጸሃፊ ነበር። በዚህ ወንጌል እሱ ራሱን “ኢየሱስ ይወደው የነበረ” እና “ሌላው ደቀመዝሙር” በማለት ይገልጻል (ዮሐንስ 13፥2320፥3)። ዮሐንስ ወንጌልን ለመስበክ የነበረው ጉጉት እጅግ ከፍተኛ ስለነበር ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ ለማምጣት እስከ አዳኙ ዳግም ምጻት ድረስ በምድር ላይ ለመቆየት ጠየቀ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 7፥1–6ን ተመልከቱ)።

በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት “ዮሐንስ፣” “የዮሐንስ ወንጌል”ን ተመልከቱ።

ዮሐንስ 1፥1–5

ኢየሱስ ክርስቶስ “በመጀመርያው … በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።”

ዮሐንስ ወንጌሉን “በመጀመርያ … ቃልም [ኢየሱስ ክርስቶስ] በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ” በማለት ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት የሰራውን ስራ ገልጿል። ከቁጥር 1–5 ስለ አዳኙ እና ስራው ምን ተማራችሁ? ጠቃሚ የሆኑ ማብራርያዎችን በጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዮሐንስ 1፥1–5 (በመፅሐፍ ቅዱስ አባሪ) ማግኘት ትችላላችሁ። የአዳኙን ህይወት ጥናት ስትጀምሩ፣ የቅድመ ምድራዊ ስራውን ማወቅ ለምን ይጠቅማል?

በተጨማሪም የወንጌል ርዕሶች፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አዳኝ ተመረጠ፣” topics.ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

ዮሐንስ 1፥1–18

ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ “እውነተኛ ብርሃን” ነው።

“ስለ ብርሃን ሊመሰክር” እንደመጣ (ዮሐንስ 1፥8–9) በገለጸው በመጥምቁ ዮሐንስ ምስክርነት ምክንያት ዮሐንስ አዳኙን ለማግኘት ተነሳስቶ ነበር ። ዮሐንስ እራሱ ስለ ክርስቶስ ህይወት እና ስለ አዳኙ ተልዕኮ ታላቅ ምስክርነትን ሰጥቷል።

ምናልባት ዮሐንስ በመክፈቻ የክርስቶስ ምስክርነቱ ላይ ያካተተውን እውነቶች ዝርዝር ማውጣት አስደሳች ሊሆን ይችላል (ቁጥሮች 1–18፤ በተጭማሪም ጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዮሐንስ 1፥1–19 [በመፅሐፍ ቅዱስ አባሪ] ተመልከቱ)። ዮሐንስ ወንጌሉን በእነዚህ እውነቶች መጀመር የፈለገው ለምን ይመስላችኋል? ለኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ምስክርነት ለመጻፍ አስቡ—ምን ማካፈል ትፈልጋላችሁ? አዳኙን እንድታውቁት እና እንድትከተሉት የረዷችሁ ልምዶች ምንድናቸው? ምስክርነታችሁን በመስማት ሊጠቀም የሚችለው ማን ነው?

ዮሐንስ 1፥11–13

ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ሴት እና ወንድ ልጆች “የመሆን ኃይል” ይሰጠናል።

ምንም እንኳን ሁላችንም የመንፈስ ሴት እና ወንድ ልጆቹ ብንሆንም፣ ኃጢያት ስንሰራ ከእርሱ እንርቃለን ወይም እንለያለን። በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕት አማካኝነት ወደ እርሱ እንድንመለስ ያደርገናል። ዮሐንስ 1፥11–13 የእግዚአብሔር ሴት እና ወንድ ልጆች ስለመሆን የሚያስተምረውን አሰላስሉ። በተጨማሪም ይህንን ስጦታ እንዴት እንደምንቀበል እነዚህ ጥቅሶች የሚያስተምሩትን አስቡ ሮሜ 8፥14–18ሞዛያ 5፥7–9ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 25፥1። የእግዚአብሔር ሴት እና ወንድ ልጆች “የመሆን ኃይል” ማግኘት ለናንተ ምን ማለት ነው?

ዮሐንስ 1፥18

አብ ስለ ወልድ ይመሰክራል።

ዮሐንስ 1፥18 ማንም እግዚአብሔርን እንዳላየ ይናገራል። ሆኖም ግን የጆሴፍ ስሚዝ የዚህ ቁጥር ትርጉም እንዲህ ግልጽ ያደርጋል፣ “ስለ ልጁ ከመሰከረ ውጪ መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድስ ስንኳ የለም፣ ዮሐንስ 1፥18፣ የግርጌ ማስታወሻ  )። እግዚአብሔር አብ ስለልጁ የመሰከረበትን ጊዜያት ለመቃኘት አስቡ ማቴዎስ 3፥1717፥53 ኔፊ 11፥6–7የጆሴፍ ስሚዝ ታሪክ 1፥17

እነዚህን ምዕራፎች ማግኘት በረከት ለምን ይመስላችኋል? ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ አባቱ ግንኙነት ምን ያስተምራሉ?

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ምስል
ሴት ልጅ ቅዱሳት መጻሐፍትን እያነበበች

ቅዱሳት መጻህፍትን ስናጠና ለህይወታችን የሚሆኑ የሚያነሳሱ ነገሮችን ልናገኝ እንችላለን።

ዮሐንስ 1፥4–10በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ቤተሰባችሁ ስለ ብርሃን ያነበበውን በአይነ ህሊና እንዲያይ እንዴት መርዳት ትችላላችሁ? ቤተሰባችሁ በጨለማ ክፍል ውስጥ መብራት ተራ በተራ እንዲያበራ እና አዳኙ የህይወታቸው ብርሃን እንዴት እንደሆነ እንዲያካፍሉ ማድረግ ትችላላችሁ። ከዚያም ዮሐንስ 1፥4–10ን ስታነቡ፣ የቤተሰብ አባላት ዮሐንስ የአለም ብርሃን ስለሆነው ክርስቶስ ስላለው ምስክርነት ተጨማሪ መረዳት ሊኖራቸው ይችላል።

ዮሐንስ 1፥ 35–36መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን “የእግዚአብሔር በግ” ብሎ የጠራው ለምን ይመስላችኋል? ከሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ መልዕክት ርዕስ “እነሆ የእግዚአብሔር በግ” ወይም ከሽማግሌ ጋሬት ደብሊው. ጎንግ መልዕክት “መልካም እረኛ፣ የእግዚአብሔር በግ” ምን እንማራለን? (ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 44–46፣ 97–101)

ዮሐንስ 1፥35–46የዮሐንስ ምስክርነት ውጤቶች ምንድን ናቸው? በእነዚህ ጥቅሶች ከተገለጹት ሰዎች ወንጌልን ስለማካፈል ቤተሰባችሁ ምን ለመማር ይችላሉ? በተጨማሪም “ሌሎች ‘መጥተው እንዲያዩ’ መጋበዝ” የሚለውን ቪዲዮ ተመልከቱ (ChurchofJesusChrist.org)።

ዮሐንስ 1፥45–51ናትናኤል ስለ አዳኙ ምስክርነትን እንዲያገኝ የረዳው ምንድነው? የቤተሰብ አባላት ምስክርነታቸውን እንዴት እንዳገኙ እንዲናገሩ ጋብዟቸው።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልን ተመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “እግዚአብሔር ብርሃኔ ነው፣” መዝሙር፣፣ ቁጥር 89።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

በተግባራዊ ምሳሌያዊ ነገሮች ትምህርቶችን አጋሩ። በምታነቧቸው ቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ ያሉ መርሆችን ለመረዳት የሚያግዟቸውን ነገሮች እንዲፈልጉ የቤተሰብ አባላትን ጋብዟቸው። ለምሳሌ ሻማ የክርስቶስ ብርሃንን እንዲወክል መጠቀም ይችላሉ ( ዮሐንስ 1፥4ን ይመልከቱ)።

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ ምድርን እየፈጠረ

ያህዌ ምድርን ፈጠረ፣ በዋልተር ሬን

አትም