አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
የካቲት 13–19 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 5፤ ሉቃስ 6፦ “ብፁዓን ናችሁ”


“የካቲት 13–19 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 5፤ ሉቃስ 6፦ ‘ብፁዓን ናችሁ’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“የካቲት 13–19 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 5፤ ሉቃስ 6፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ ተራራ ላይ ሲያስተምር

ኢየሱስ ተራራ ላይ ስብከት እየሰበከ፣ በጉስታቭ ዶሬ

የካቲት 13–19 (እ.አ.አ)

ማቴዎስ 5ሉቃስ 6

“ብፁዓን ናችሁ”

እናንተ ማቴዎስ 5 እና ሉቃስ 6ን ስታነቡ ለሚያድርባችሁን ስሜት ትኩረት ስጡ እናም በጥናት ደብተር ላይ ወይም በሌላ መንገድ ጻፉ። ይህ ረቂቅ በእነዚህ ምዕራፎች ላይ ያሉ መርሆዎችን እንድትለዩ ይረዳችኋል፣ ነገር ግን በጥናታችሁ ለምታገኟቸው ለሌሎች ግኝቶችም ዝግጁ ሁኑ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በዚህን ሰዓት የኢየሱስ አስተምሮቶች በእርሱ ጊዜ የነበሩ ሰዎች መስማት ከለመዱት የተለየ እንደነበር ግልጽ ነበር። ድሆች የእግዚአብሔር መንግሥት ሊወርሱ ይችላሉን? የዋሆች ምድርን ይወርሳሉን? የሚሰቃዩ የተባረኩ ናቸውን? ጸሐፊዎች እና ፈሪሳውያን አንዲህ አይነት ነገር እያስተማሩ አልነበረም። ሆኖም ግን የእግዚአብሔርን ህግ በእውነት የተረዱት በአዳኙ ቃላት ውስጥ እውነትን ያውቁ ነበር። “ዓይን ስለ ዓይን” እና “ጠላትህን ጥላ” አነስትኛ ህጎች ነበሩ (ማቴዎስ 5፥38፣ 43)። ነገር ግን ከፍ ያለውን ህግ (3 ኔፊ 15፥2–10 ተመልከቱ)፣ “የሰማዩ አባታች[ን] ፍጹም እንደ ሆነ [እኛም] ፍጹም” እንድንሆን እንዲረዳን ለማስተማር ኢየሱስ ክርስቶስ መጣ (ማቴዎስ 5፥48)።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ማቴዎስ 5፥1–12ሉቃስ 6፥20–26፣ 46–49

ዘላቂ ደስታ የሚመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ባስተማረው መንገድ በመኖር ነው።

ሁሉም ሰው ደስተኛ ለመሆን ይፈልጋል ነገር ግን ሁሉም ሰው ደስታን ተመሳሳይ ቦታ ላይ አይፈልግም። አንዳንዶች በአለማዊ ሃይል እና ስልጣን ላይ ሌሎች ደግሞ በሃብት ወይም አካላዊ አምሮታቸውን በማርካት ላይ ይፈልጉታል። ኢየሱስ ክርስቶስ የዘላቂ ደስታን መንገድ፣ እንዲሁም በእውነት መባረክ ምን ማለት እንደሆነ ለማስተማር መጣ። ዘላቂ ደስታን ለማግኘት በማቴዎስ 5፥1–12 እና በሉቃስ 6፥20–26 ውስጥ ምን ትማራላችሁ? ከአለም የደስታ እይታ ይህ እንዴት ነው የሚለየው?

እነዚህ ጥቅሶች፣ ከሉቃስ 6፥46–49 ጋር በመጋራት፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ስለመሆን ምን ያስተምራሉ? በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተጠቀሱ ባህርያት እንዲኖራችሁ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ይሰማችኋል?

በተጨማሪም የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ “ብጹእ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org፤ “የተራራው ላይ ስብከት፦ ብጽእና” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org

2:12

ማቴዎስ 5፥13

“እናንተ የምድር ጨው ናችሁ።”

ጨው ለረጅም ጊዜያት ለማቆየት፣ ለማጣፈጥ እና ለማንጻት ጥቅም ላይ ውሏል። ለእስራኤላውያን ጨው ሃይማኖታዊ ትርጉምም ነበረው። በሙሴ ህግ ውስጥ ከጥንታዊ የእንስሳት መስዋዕት ጋር ይገናኛል (ሌዋውያን 2፥13ዘሁልቁ 18፥19ን ተመልከቱ)። ጨው ጣዕሙን ካጣ አያገለግልም ወይም “ለምንም አይጠቅምም” (ማቴዎስ 5፥13)። ይህ የሚፈጠረው ከሌሎች ንጥረነገሮች ጋር ሲቀላቀል ወይም ሲበከል ነው።

ማቴዎስ 5፥13ን ስታሰላስሉ ይህን ነገር በአዕምሯችሁ ያዙ። እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙርነት ጣዕማችሁን የምትጠብቁት እንዴት ነው? እንደ ምድር ጨው የማቆየት እና የማንጻት ስራችሁን የምትፈጽሙት እንዴት ነው?

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 103፥9–10ን ተመልከቱ።

ጨው

“እናንተ የምድር ጨው ናችሁ”(ማቴዎስ 5፥13)።

ማቴዎስ 5፥17–48ሉቃስ 6፥27–35

የክርስቶስ ህግ የሙሴን ህግ ተካ።

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ጽድቃቸው የሙሴን ህግ በመጠበቃቸው ይኮሩ ከነበሩ ጸሐፊዎች እና ፈሪሳውያን ጽድቅ መብለጥ እንዳለበት (ማቴዎስ 5፥20ን ተመልከቱ) ሲነግራቸው ደቀመዛሙርቱ ሳይገረሙ አልቀረም።

ማቴዎስ 5፥21–48 እና ሉቃስ 6፥27–35ን ስታነቡ በሙሴ ህግ ይፈለጉ የነበሩ ባህርያትን (“… እንደ ተባለ ሰምታችኋል”) እና ኢየሱስ እነዚህን ለማስተካከል ያስተማረው ምልክት ለማድረግ አስቡ። የአዳኙ መንገድ ከፍ ያለ ህግ የሆነው ለምን ይመስላችኋል?

ለምሳሌ በማቴዎስ 5፥27–28 በአስተሳሰባችን ላይ ስላለን ሃላፊነት ኢየሱስ ምን አስተማረ? በአዕምሯችሁ እና በልባችሁ የሚመጡ ሃሳቦችን እና ስሜቶችን ይበልጥ መቆጣጠር የምትችሉት እንዴት ነው?(ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥45ን ተመልከቱ)።

በተጨማሪም “የተራራው ላይ ስብከት፤ ከፍ ያለው ህግ” (ቪድዮ)፣ ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

2:28

ማቴዎስ 5፥48

የሰማይ አባት ፍጹም እንድሆን በእውነት ይጠብቃልን?

ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳስተማሩት፦

ፍጹም የሚለው ቃል teleios [ቴሌዮስ] ከሚል የግሪክ ቃል የተተረጎመ ሲሆን ትርጓሜውም ‘ሙሉ’ ማለት ነው። … የዚህ ግስ ሰዋሰው ለውጥ teleiono [ተሌኦኖ] ሲሆን ትርጓሜውም ‘የራቀን መጨረሻ መድረስ፣ በሙላት ማደግ፣ ማሟላት ወይም መፈጸም’ ማለት ነው። እባካችሁ ቃሉ ‘ከስህተት ነጻ’ ማለት እንዳልሆነ አስተውሉ፤ የሚያመለክተው ‘የሩቅ ግብ መምታትን ነው።’ …

“… ጌታ እንዳስተማረው፣ ‘የእግዚአብሔርን ፊት … ትመለከቱ ዘንድ አትችሉም፤ ስለዚህ ፍጹም እስክትሆኑ ድረስ በትዕግስት ፅኑ’ [ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 67፥13]።

“አሁን ላይ ፍጹም የመሆን ቅን ጥረታችን እጅግ ከባድ እና ማብቅያ የሌለው ከመሰለን ተስፋ መቁረጥ የለብንም። ፍጹምነት ያላለቀ ሂደት ነው። በሙላት ሊመጣ የሚችለው ከትንሳኤ በኋላ እና በጌታ አማካኝነት ብቻ ነው። እርሱን የሚወዱትን እና ትዕዛዛቱን የሚጠብቁትን ሁሉ ይጠብቃል” (“ፍጹምነት ያላለቀ ሂደት፣” ኢንዛይን፣ ህዳር 1995 (እ.አ.አ) 86፣ 88)።

በተጨማሪም 2 ጴጥሮስ 1፥3–11ሞሮኒ10፥32–33ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76፥69፤ ጀፍሪ አር. ሆላንድ “ፍጹማን ሁኑ—በስተመጨረሻ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2017 (እ.አ.አ)፣ 40–42ን ተመልከቱ።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ማቴዎስ 5፥1–9ማቴዎስ 5፥1–9 ካሉት አስተምሮቶች የትኞቹ መርሆች ናቸው ቤታችሁ የደስታ ቦታ እንዲሆን የሚረዷችሁ? ለቤተሰባችሁ እጅግ አስፈላጊ ከሚመስሉት ውስጥ አንድ ወይም ሁለት መምረጥ ትችላላችሁ። ለምሳሌ አስታራቂ እንድንሆን የሚረዱን ምን አስተምሮቶች እናገኛለን? (ማቴዎስ 5፥21–25፣ 38–44ን ተመልከቱ)። ምን አይነት ግብ ማስቀመጥ እንችላለን? እንዴት ነው የምንከታተለው?

ማቴዎስ 5፥13በአንድነት በጨው የጣፈጠ እና ያለ ጨው የተሰራ ተመሳሳይ ምግብ ተመገቡ። ምን አይነት ልዩነት እናስተውላለን? “የምድር ጨው” መሆን ምን ማለት ነው? እንዴት ነው ይህን ልናደርግ የምንችለው?

ማቴዎስ 5፥14–16“የዓለም ብርሃን” መሆን ምን ማለት እንደሆነ ቤተሰባችሁ እንዲረዳ ቤታችሁ ውስጥ፣ በሰፈራችሁ እና በአለም ያሉ አንዳንድ የብርሃን ምንጮችን መፈለግ ትችላላችሁ። ብርሃንን ስትደብቁ የሚፈጠረውን ማሳየት ሊረዳ ይችላል። ኢየሱስ “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ” ሲል ምን ማለቱ ነበር? (ማቴዎስ 5፥14)። ለቤተሰባችን እንደ ብርሃን የነበረው ማነው? ለሌሎች ብርሃን መሆን የምንችለው እንዴት ነው? (3 ኔፊ 18፥16፣ 24–25ን ተመልከቱ)።

ማቴዎስ 5፥43–45ቤተሰባችሁ በእነዚህ ጥቅሶች የአዳኙ ቃላት ሲያነብ ማንን መውደድ፣ መባረክ እና ለማን መጸለይ እንደሚገባ እንደሚሰማችሁ ለመነጋገር ትችላላችሁ። ለእነርሱ ያለንን ፍቅር እንዴት ነው መጨመር የምንችለው?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልን ይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “አብሩ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 144።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ንቁ አስተዋይ ሁኑ። “በልጆቻችሁ ህይወት ውስጥ እየሆነ ባለው ነገር ላይ ትኩረት ስታደርጉ እጅግ በጣም ጥሩ የማስተማር እድሎችን ታገኛላችሁ። … የሚሰጡት አስተያየት ወይም የሚጠይቁት ጥያቄዎች ወደ ማስተማርያ ጊዜ ሊመሩ ይችላሉ (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር]፣ 16)።

ሻማ

“እናንተ የአለም ብርሀን ናችሁ” (ማቴዎስ 5፥14)።