አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
የካቲት 6–12 (እ.አ.አ)። ዮሐንስ 2–4፦ “ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል“


“የካቲት 6–12 (እ.አ.አ)። ዮሐንስ 2–4፦ ‘ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“የካቲት 6–12 (እ.አ.አ)። ዮሐንስ 2–4፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ክርስቶስ ከኒቆዲሞስ ጋር ሲያወራ

የካቲት 6–12 (እ.አ.አ)

ዮሐንስ 2–4

“ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል“

ዮሐንስ 2–4ን ስታነቡ መንፈስ ስለ እናንተ መቀየር ያስተምራችኋል። የሚያሳድርባችሁን ስሜት ማስታወሻ ያዙ። በዚህ ረቂቅ ላይ ከሚገኙ የጥናት ሃሳቦች ተጨማሪ መንፈሳዊ መረዳት ልታገኙ ትችላላችሁ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ቃና በነበረ ሰርግ ክርስቶስ ውሃን ወደ ወይን ቀየረ—ዮሐንስ ይህንን ክስተት “የምልክቶች መጀመሪያ” (ዮሐንስ 2፥11) ብሎ ጠርቶታል። ይህ ከአንድ በላይ በሆነ እይታ ትክክል ነው። ይህ ክርስቶስ ያደረገውን የመጀመርያ ተአምር ሲሆን፣ ይህም ተአምራዊ ጅማሬን ያመለክታል—እንደ አዳኙን እየመሰልን ስንሄድ የልባችንን መቀየር ሂደትን ያመሳስላል። ይህ የእድሜ ልክ ተአምር የሚጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል፣ በእርሱም ለመለወጥ እና የተሻለ ህይወትን ለመኖር በመወሰን ነው። ይህ ተአምር ህይወትን በእጅጉ የሚቀይር ከመሆኑ የተነሳ “ዳግመኛ [መወለድ]” (ዮሐንስ 3፥7) የሚለው በጥሩ ሁኔታ ይገልጸዋል። ነገር ግን ዳግም መወለድ የደቀመዝሙርነት መንገድ ጅማሬ ብቻ ነው። በጉድጓድ አጠገብ ለነበረችው ሳምራዊት ሴት የክርስቶስ ቃላት እንድናስታውስ እንደሚያደርገን፣ በዚህ መንገድ ከቀጠልን በመጨረሻ ወንጌሉ በውስጣችን “ለዘላለም ህይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ” (ዮሐንስ 4፥14) እንደሚሆን ነው።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ዮሐንስ 2፥1–11

የኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራት “[የእርሱን ክብር ይገልጣሉ]”።

ዮሐንስ 2፥1–11 ውስጥ የአዳኙ ውሃን ወደ ወይን መቀየር ስታነቡ፣ በቦታው የነበሩ የተለያዩ ሰዎችን፣ እንዲሁም የማርያም፣ የሐዋርያት እና የሌሎችን እይታ ከግምት ብታስገቡ ተጨማሪ መረዳት ልታገኙ ትችላላችሁ። እዚህ ላይ የተገለጹ ክስተቶች የአይን እማኞች ብትሆኑ ኖሮ፣ ለኢየሱስ የሚኖራችሁ አመለካከት ምን ይሆን ነበር? ይህ ተአምር ስለ እርሱ ምን ያስተምራችኋል?

ዮሐንስ 3፥1–21

ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመግባት ዳግም መወለድ አለብኝ።

ኒቆዲሞስ ወደ ኢየሱስ በድብቅ ሲመጣ፣ ተጠንቅቆ ነበር። በኋላ ግን በህዝብ ፊት ለክርስቶስ ተከላከለ (ዮሐንስ 7፥45–52ን ተመልከቱ) እናም በአዳኙ ቀብር ላይ አማኞችን ተቀላቀለ (ዮሐንስ 19፥38–40ን ተመልከቱ)። በዮሐንስ 3፥1–21 ላይ ኒቆዲሞስ ኢየሱስን እንዲከተል እና ዳግም እንዲወለድ ያነሳሳውን ምን ትምህርት ታገኛላችሁ?

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ “ዳግም መወለድ የሚመጣው በእግዚአብሔር መንፈስ በስርዓቶች አማካኝነት ነው” በማለት አስተምሯል (Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith [የቤተክርስቲያኗ ፕሬዝዳንቶች ትምህርቶች፤ ጆሴፍ ስሚዝ] [2007 (እ.አ.አ)]፣ 95)። ጥምቀታችሁ እና መንፈስ ቅዱስን መቀበላችሁ—”ከውሃ እና ከመንፈስ [መወለዳችሁ]” (ዮሐንስ 3፥5)—በእናንተ ዳግም መወለድ ምን አይነት ሚና ይጫወታል? ይህንን የለውጥ ሂደት ለመቀጠል ምን እያደረጋችሁ ነው (አልማ 5፥11–14ን ተመልከቱ)?

በተጨማሪም ሞዛያ 5፥727፥25–26፤ ዴቪድ ኤ. ቤድናር “ዳግም መወለድ አለባችሁ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2007 (እ.አ.አ)፣ 19–22ን ተመልከቱ።

ዮሐንስ 3፥16–17

የሰማይ አባት ለእኔ ያለውን ፍቅር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ያሳያል።

ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ “የመጀመርያው ዘላለማዊ ታላቅ እውነት እግዚአብሔር እኛን በእርሱ ሙሉ ልቡ፣ ሃይሉ እና ብርታቱ እንደሚወደን ነው” በማለት አስተምረዋል (“ነገ ጌታ በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ጋደርጋል፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2016 (እ.አ.አ)፣ 127)። በልጁ ስጦታነት አማካኝነት የእግዚአብሔር ፍቅር እንዴት ተሰምቷችሁ ያውቃል?

የቅዱስ ቁርባን ስርዓት የእግዚአብሔር ፍቅር እና የልጁን ስጦታ ወደኋላ እንድናስብ ጊዜ ይሰጠናል። የትኞቹ የቅዱስ ቁርባን መዝሙሮች ናቸው የእርሱ ፍቅር እንዲሰማችሁ የሚረዷችሁ? ቅዱስ ቁርባን ይበልጥ ትርጉም እንዲኖረው ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ስለ አዳኙ አስተምሮቶች እና አገልግሎት ማንበብ ስትቀጥሉ፣ የምታነቡት ነገር እንዴት የእግዚአብሔርን ፍቅር እንድትረዱ እና እንዲሰማችሁ እንደሚያደርጋችሁ ራሳችሁን ጠይቁ።

ዮሐንስ 4፥24

እግዚአብሔር መንፈስ ነውን?

አንዳንዶች እግዚአብሔር መንፈስ ነው በሚለው የኢየሱስ ንግግር ግራ ሊጋቡ ይችላሉ። የዚህ ጥቅስ የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም “ለእንደዚህ አይነቶቹ ነው እግዚአብሔር መንፈሱን ቃል የገባው” በማለት ጠቃሚ ማብራርያ ይሰጣል (በዮሐንስ 4፥24፣ የግርጌ ማስታወሻ  )። በተጨማሪም የአሁን ጊዜ መገለጦች እግዚአብሔር የስጋ እና አጥንት አካል እንዳለው ያተምራል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 130፥22–23ን ተመልከቱ፤ በተጨማሪም ዘፍጥረት 5፥1–3ዕብራውያን 1፥1–3ን ተመልከቱ)።

ዮሐንስ 4፥5–26

ኢየሱስ ክርስቶስ የህያው ውሃ ምንጩን ይሰጠኛል።

ለሳምራዊቷ ሴት እርሱ ከሚሰጠው ውሃ የሚጠጣ ዳግመኛ አይጠማም ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነው? እንዴት ነው ወንጌል እንደ ህያው ውሃ የሚሆነው?

ምስል
ኮለል ያለ ውሃ

የክርስቶስ ወንጌል ነፍሳችንን የሚመግብ ህያው ውሃ ነው።

አዳኙ ለሳምራዊቷ ሴት ከሰጣቸው መልዕክቶች አንዱ የምናመልክበት መንገድ ከምናመልክበት ቦታ ይበልጥ አስፈላጊ እንደሆነ ነው (ዮሐንስ 4፥21–24ን ተመልከቱ)። “ለአብ በመንፈስ እና በእውነት [ለመስገድ]” ምን እያደረጋችሁ ናችሁ? (ዮሐንስ 4፥23)።

በተጨማሪም ለቅዱሳት መጻሀፍት መመርያ፣ “አምልኮ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org፤ ዲን ኤም.ዴቪስ፣ “የአምልኮ በረከቶች፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 93–95 ተመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ዮሐንስ 2–4በዚህ ሳምንት ቤተሰባችሁ እነዚህን ምዕራፎች ሲያነብ አዳኙን መንፈሳዊ እውነቶችን ለማስተማር እንዴት የእለት ተእለት ነገሮችን—መወለድ፣ ንፋስ፣ ውሃ፣ እና ምግብ—እንደተጠቀመ ልዩ ትኩረት ስጡ። መንፈሳዊ እውነቶችን ለማስተማር በቤታችሁ ውስጥ ምን አይነት እቃዎችን መጠቀም ትችላላችሁ?

እነዚህን ምዕራፎች ስታጠኑ ስለእነዚህ ክስተቶች የሚያሳዩ ቪድዮዎች ለማየት አስቡ፦ “ኢየሱስ ውሃን ወደ ወይን ቀየረ፣” “ኢየሱስ ቤተመቅደስን አነጻ፣” “ኢየሱስ ዳግመኛ ስለመወለድ አስተማረ” እና “ኢየሱስ ሳምራዊቷን ሴት አስተማረ” (ChurchofJesusChrist.org)።

ዮሐንስ 2፥13–17ቤታችሁ እንደ ቤተመቅደስ የተቀደሰ ቦታ እንዲሆን ከቤታችሁ ምን አይነት የረከሱ ተጽዕኖዎችን ማስወገድ ይኖርባችኋል? እነዚያን ነገሮች ለማስወገድ ምን ታደርጋላችሁ?

ዮሐንስ 3፥1–6ከቤተሰባችሁ ጋር ስለ እርግዝና እና ልጅ መውለድ ተአምር—ህያው እና የማሰብ ብቃት ያለውን ሰው ስለመፍጠር ሂደት አውሩ። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ከመግባታችን በፊት ዳግም መወለድ እንዳለብን አስተምሯል። ወደ እግዚአብሔር መንግስት ከመግባታችን በፊት ለሚያስፈልገን ለውጥ ዳግም መወለድ ጥሩ ምሳሌ የሆነው ለምንድን ነው? በመንፈስ ዳግም መወለድን እንዴት ነው ልንለማመድ የምንችለው?

ዮሐንስ 3፥16–17የቤተሰባችሁ አባላት እነዚህን ጥቅሶች በገዛ ቃላቸው ለጓደኛ እንደሚያስረዱ አድርገው እዲያብራሩ ጋብዟቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲሰማን እንዴት ረድቶናል?

ዮሐንስ 4፥5–15አዳኙ ወንጌሉን ከህይወት ውሃ ጋር ሲያነጻጽር ምን እያስተማረን ነው? ምናልባት ቤተሰባችሁ የሚፈስ ውሃን መመልከት እና የውሃን ባህርያት መዘርዘር ይችላል። በየቀኑ ውሃ መጠጣት ያለብን ለምንድን ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በምን መንገዶች “ለዘለአለም ህይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ” ነው? (ዮሐንስ 4፥14)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ተመልከቱ።

በሃሳብ የሚቀራረብ መዝሙር፦ “የእግዚአብሔር ፍቅር፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣፣ 97።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ምልክቶችን ፈልጉ። ቅዱሳት መጻህፍት መንፈሳዊ እውነቶችን ለመግለጽ ብዙ ጊዜ እቃዎች፣ ሁኔታዎችን እና ድርጊቶች ይጠቀማሉ። እነዚህ ምልክቶች የትምህርትን ግንዛቤያችሁን ሊያሳድጉ ይችላሉ። ለምሳሌ አዳኙ መለወጥን በዳግም ከመወለድ ጋር አመሳስሏል።

ምስል
ኢየሱስ እና ሳምራዊቷ ሴት በጉድጓድ አጠገብ

የህይወት ውሃ፣ በሲሞን ዱዊ

አትም