መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
3. የክህነት መርሆዎች


“3. የክህነት መርሆዎች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ በ[2023 (እ.አ.አ)]።

“3. የክህነት መርሆዎች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ምስል
ቤተሰብ ወደ ቤተመቅደስ ሲሄድ

3.

የክህነት መርሆዎች

3.0

መግቢያ

ክህነት የእግዚአብሔር ስልጣን እና ሃይል ነው። በክህነት አማካኝነት የሰማይ አባት “የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት [የ]ማምጣት” ስራውን ያስፈፅማል (ሙሴ1፥39)። እግዚአብሔር በምድር ላይ ላሉ ወንድ እና ሴት ልጆቹ ይህንን ስራ እንዲያከናውኑ ለመርዳት ስልጣን እና ሃይል ይሰጣል (ምዕራፍ 1)።

3.2

የክህነት በረከቶች

በቃል ኪዳኖች እና በክህነት ስርዓቶች አማካኝነት እግዚአብሔር ታላቅ በረከቶችን ለሁሉም ልጆቹ የሚገኙ አድርጓል። እነዚህ በረከቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ጥምቀት እና አባልነት በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን።

  • የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ።

  • ቅዱስ ቁርባንን መካፈል፡፡

  • በቤተክርስቲያን ጥሪዎች እና ምደባዎች የማገልገል ሥልጣን እና ሃይል

  • የፓትርያርክ በረከቶችን እና የመፈወስ፣ የማፅናናት እና የመምራት ሌሎች የክህነት በረከቶችን መቀበል።

  • በቤተመቅደስ የእግዚአብሔርን የሃይል ስጦታ መቀበል።

  • ከራስ የቤተሰብ አባላት ጋር ለዘለአለም መታተም።

  • የዘለአለም ህይወት ተስፋዎች።

3.3

የመልከ ጼዴቅ ክህነት እና የአሮናዊ ክህነት

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ፣ ክህነት ሁለት ክፍሎች አሉት፦ የመልከ ጸዴቅ ክህነት እና የአሮናዊ ክህነት (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥1ን ይመልከቱ)።

3.3.1

የመልከ ጼዴቅ ክህነት

የመልከ ጼዴቅ ክህነት “እንደ እግዚአብሔር ልጅ ስርዓት ቅዱስ ክህነት“ ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥3)። የእግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች እንደእርሱ ለመሆን የሚያስችላቸው ሃይል ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥19–21132፥19–20 ይመልከቱ)።

በዚህ ሥልጣን አማካኝነት የቤተክርስቲያን መሪዎች ሁሉንም የቤተክርስቲያኗ መንፈሳዊ ስራዎች ይመራሉ እንዲሁም ያስተዳድራሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107 ፡18ን ይመልከቱ)።

የካስማ ፕሬዚዳንቱ በካስማው ውስጥ ከፍተኛ ሊቀ ካህን ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥8፣ 10፤ እንዲሁም ምእራፍ 6ን ይመልከቱ)። ኤጲስ ቆጶሱ በአጥቢያው ውስጥ ከፍተኛ ሊቀ ካህን ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥17፤ እንዲሁም የዚህን መመሪያ መፅሐፍ ምዕራፍ 7ን ይመልከቱ)።

ስለመልከ ጼዴቅ ክህነት ክፍሎች እና ኃላፊነቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 8.1 ይመልከቱ።

3.3.2

የአሮናዊ ክህነት

የአሮናዊ ክህነት “ከመልከ ጼዴቅ ክህነት ጋር የተያያዘ [ነው]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥14ን ይመልከቱ)። የሚከተሉትን ቁልፎች ያካትታል፦

  • የመላዕክት አገልግሎት።

  • የንስሃ ወንጌል።

  • ለኃጢያት ስርየት መጠመቅን ጨምሮ ውጪያዊ ሥርዓቶችን ማከናወን።

(ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፥184፥26–27107፥20 ይመልከቱ)።

ኤጲስ ቆጶሱ የአጥቢያው የአሮናዊ ክህነት ፕሬዚዳንት ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥15 ይመልከቱ)።

ስለመልከ ጼዴቅ ክህነት ክፍሎች እና ኃላፊነቶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 10.1.3 ይመልከቱ።

3.4

የክህነት ስልጣን

የክህነት ስልጣን እግዚአብሔርን ለመወከል እና በስሙ ለማድረግ የተሰጠ ፈቃድ ነው። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ፣ ሁሉም የክህነት ስልጣን ስራ የሚከናወነው የክህነት ስልጣን ቁልፍ ባላቸው አመራር ነው።

3.4.1

የክህነት ቁልፎች

የክህነት ቁልፎች የእግዚአብሔርን ልጆች ወክሎ የክህነትን አጠቃቀም የመምራት ስልጣን ነው።

3.4.1.1

የክህነት ቁልፎችን የያዙ

ጌታ በምድር ላይ ካለችው የእግዚአብሔር መንግሥት ጋር የተያያዙ ሁሉንም ቁልፎች ለእያንዳንዱ ሐዋርያ ሰጥቷል። የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት የሆነው በህይወት ያለው ከፍተኛ ሐዋርያ፣ በምድር እነዚያን የክህነት ቁልፎች ሁሉ ለመጠቀም ስልጣን ያለው ብቸኛው ሰው ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81፥1–2107፥64–67፣ 91–92132፥7ን ይመልከቱ)።

የክህነት መረዎች በቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት አመራር ሥር በመሆን ኃላፊነት ባለባቸው ቦታዎች ውስጥ በበላይነት መምራት እንዲችሉ ቁልፎች ተሰጥቷቸዋል። እነዚህ መሪዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • የካስማ እና የአውራጃ ፕሬዚዳንቶች።

  • ኤጲስ ቆጶሳት እና የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቶች።

  • የመልከ ጼዴቅ እና የአሮናዊ የክህነት ቡድን ፕሬዚዳንቶች

  • የቤተመቅደስ ፕሬዚዳንቶች

  • የሚስዮን ፕሬዚዳንቶች እና የሚስዮናዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ፕሬዚዳንቶች

እነዚህ መሪዎች በጥሪዎቻቸው ለአገልግሎት ሲለዩ የክህነት ቁልፎችን ይቀበላሉ።

ለአካባቢ የክህነት መሪዎችአማካሪዎች ወይም ለቤተክርስቲያን ድርጅቶች ፕሬዚዳንቶች ጨምሮ የክህነት ቁልፎች ለሌሎች አይሰጡም። የቤተክርስቲያን ድርጅቶች ፕሬዚዳንቶች የክህነት ቁልፎችን በያዙት አመራር ስር ሆነው በበላይነት ይመራሉ (4.2.4 ይመልከቱ)።

3.4.1.2

ሥርዓት ለጌታ ስራ

የክህነት ቁልፎች የደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራን ሥርዓት ባለው መንገድ እየተፈጸመ እንደሆነ ያረጋግጣሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥11132፥8)። የክህነት ቁልፎችን የያዙ ኃላፊነት ባለባቸው ቦታዎች ውስጥ የጌታን ስራ ይመራሉ። ይህ የበላይ መሪ ባለስልጣን ተቀባይነት የሚኖረው ለመሪው ጥሪ በተሰጡት ልዩ ኃላፊነቶች ላይ ብቻ ነው። የክህነት መሪዎች ከጥሪዎቻቸው ከተሰናበቱ በኋላ እነዚህ ቁልፎች አይኖሯቸውም።

3.4.2

ክህነትን መስጠት እና ሹመት

የክህነት ቁልፎቹን በያዙ አመራር፣ የአሮናዊ ክህነት እና የመልከ ጼዴቅ ክህነት ብቁ ለሆኑ ወንድ የቤተክርስቲያን አባላት ይሰጣሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥14–17ን ይመልከቱ)። ተገቢው የክህነት ስልጣን ከተሰጠው በኋላ በዚያ ክህነት ውስጥ እንደ ዲያቆን ወይም ሽማግሌ በመሳሰሉ የክህነት ክፍሎች ይሾማል። የክህነት ተሸካሚው ክህነቱን የሚጠቀመው በክፍሉ መብት እና ግዴታ መሰረት ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥99ን ይመልከቱ)።

ስለክህነት አሰጣጥ እና ሹመት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ 8.1.1 እና 18.10ን ይመልከቱ።

3.4.3

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ለማገልገል የክህነት ስልጣንን በውክልና ለሌላ ሰው መስጠት

3.4.3.1

ለአገልግሎት መለየት

ወንዶች እና ሴቶች የክህነት ቁልፎችን በያዙ አመራር አማካኝነት ለአገልግሎት በሚለዩበት ጊዜ፣ በዚያ ጥሪ ውስጥ እንዲሰሩ ከእግዚአብሔር ሥልጣን ይሰጣቸዋል። የክህነት መሪዎች ከጥሪያቸው ሲሰናበቱ፣ ከዚህ ጋር የተያያዘ ሥልጣን አይኖራቸውም።

ለማገልገል የተለዩ የቤተክርስቲያኗ አባላት ሁሉ በጥሪያቸው ውስጥ ለመስራት መለኮታዊ ስልጣንና ኃላፊነት ይሰጣቸዋል። ለምሳሌ፦

  • በአጥቢያ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት ሆና በኤጲስ ቆጶስ የተጠራች እና ለአገልግሎት የተለየች አንዲት ሴት በአጥቢያው የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስራ እንድትመራ ስልጣን ይሰጣታል።

ጥሪ የተሰጣቸው እና የተለዩ እያንዳንዳቸው በበላይነት በሚቆጣጠሯቸው አመራር ስር በመሆን ነው የሚያገለግሉት (3.4.1.2ን ይመልከቱ)።

3.4.3.2

የስራ ምደባ

በበላይነት የሚመሩ የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ሥልጣናቸውን በስራ ምደባ አማካኝነት ለሌላ ሰው በውክልና ሊሰጡ ይችላሉ። ወንዶች እና ሴቶች እነዚህን የስራ ምደባዎች በሚቀበሉበት ጊዜ እንዲሰሩ ከእግዚአብሔር ሥልጣን ይሰጣቸዋል። ለምሳሌ፦

  • የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን ዋና አካባቢዎችን ለማስተዳደር ለተመደቡት እና የካስማ ጉባኤዎችን በበላይነት ለሚመሩት ለሰባዎች ሥልጣናቸውን በውክልና ይሰጣሉ።

  • እንደ አገልጋይ ወንድሞች እና አገልጋይ እህቶች እንዲያገለግሉ ለቤተክርስቲያኗ አባላት ሥልጣን በውክልና ይሰጣል።

በሥራ ምደባው በውክልና የተሰጠው ሥልጣን በተወሰኑት ኃላፊነቶች ላይ እና በሥራ ምደባው የቆይታ ጊዜ የተወሰነ ነው።

3.4.4

የክህነት ሥልጣንን በፅድቅ መጠቀም

ይህ ሥልጣን በፅድቅ ብቻ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥36ን ይመልከቱ)። ጥቅም ላይ የሚውለው በማሳመን፣ በትዕግስት፣ በደግነት፣ በትህትና፣ በፍቅር እና በርህራሄ ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፥41–42 ይመልከቱ)።

የክህነት ሥልጣንን የሚጠቀሙ ፍላጎታቸውን በሌሎች ላይ በሐይል አይጭኑም። ራስ ወዳድ ለሆነ ዓላማ አይጠቀሙበትም።

3.5

የክህነት ሀይል

የክህነት ሀይል እግዚአብሔር ልጆቹን የሚባርክበት የእርሱ ኃይል ነው። ከእርሱ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳኖች ሲጠብቁ፣ የእግዚአብሔር የክህነት ሃይል ለሁሉም የቤተክርስቲያኗ አባላት—ሴት እና ወንድ—ያለማቋረጥ ይመጣል። አባላት የክህነት ስርዓቶችን ሲቀበሉ እነዚህን ቃል ኪዳኖች ይገባሉ። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥19–20 ይመልከቱ።)

አባላት ሊቀበሏቸው የሚችሏቸው የክህነት ሃይል በረከቶች እነዚህን ያካትታሉ፦

  • ለህይወታቸው መመሪያ።

  • የቤተሰብ አባላትን እና ሌሎችን እንዴት ማገልገል እንደሚቻል ለማወቅ የሚረዳ መነሳሳት።

  • በፈተናዎች ለመፅናት እና ለማሸነፍ የሚረዳ ጥንካሬ።

  • ችሎታዎቻቸውን ለማጉላት የሚረዱ የመንፈስ ስጦታዎች።

  • የተሾሙለትን፣ ለአገልግሎት የተለዩለትን ወይም እንዲሠሩ የተሰጣቸውን ሥራ እንዴት እንደሚያከናውኑ ለማወቅ የሚረዳ ራዕይ።

  • ይበልጥ እንደ ሰማይ አባት እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመሆን እርዳታ እና ጥንካሬ።

3.5.1

ቃል ኪዳኖች

ቃል ኪዳን በእግዚአብሔር እና በልጆቹ መካከል ያለ የተቀደሰ ስምምነት ነው። እግዚአብሔር የቃል ኪዳኖቹን ሁኔታዎች ይሰጣል ከዚያም ልጆቹ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ለመታዘዝ ይስማማሉ። ቃል ኪዳኑን ሲፈፅሙ እግዚአብሔር ልጆቹን እንደሚባርክ ቃል ገብቷል።

ቃል ኪዳኖቻቸውን በመጠበቅ እስከመጨረሻው የሚጸኑ ሁሉ የዘለአለም ህይወትን ያገኛሉ (2 ኔፊ 31፥17–20ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14፥7ን ይመልከቱ)።

ግለሰቦች የወንጌል ሥርዓቶችን ሲቀበሉ ቃል ኪዳኖችን እንዲገቡ ወላጆች፣ የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ሌሎች ይረዳሉ። እርሱ ወይም እርሷ የሚገቧቸውን ቃል ኪዳኖች እንደተረዷቸው ያረጋግጣሉ። ግለሰቡ/ቧ ቃል ኪዳን ከገባ/ች በኋላ እንዲጠብቀው/እንድትጠብቀው ይረዳሉ። (Mosiah 18፥8–11፣ 23–26 ይመልከቱ)።

3.5.2

ስርዓቶች

ሥርዓት በክህነት ስልጣን የሚከናወን የተቀደሰ ተግባር ነው።

በብዙ ሥርዓቶች ግለሰቦች ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ይገባሉ፡፡ ምሳሌዎቹ እነዚህን ያካትታሉ፣ ጥምቀት፣ ቅዱስ ቁርባን፣ የቤተ መቅደስ የመንፈስ ሥጦታ እና የጋብቻ እትመት።

የደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥርዓቶች ለዘለዓለም ህይወት አስፈላጊ ናቸው። ለተጨማሪ መረጃ 18.1ን ይመልከቱ።

3.6

ክህነት እና ቤት

ቃል ኪዳናቸውን የሚጠብቁ ሁሉም የቤተክርስቲያኗ አባላት—ሴቶች፣ወንዶች እና ልጆች—በቤታቸው ውስጥ እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ለማጠንከር በእግዚአብሔር የክህነት ኃይል ተባርከዋል (3.5ን ይመልከቱ)። ይህ ኃይል አባላት በግል እና በቤተሰቦቻቸው ህይወት ውስጥ የእግዚአብሔርን የደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ሲሰሩ ይረዳል (2.2ን ይመልከቱ)።

የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ የሆኑ ሰዎች መመሪያን፣ ፈውስን እና ማፅናኛን ለመስጠት ለቤተሰብ አባላት የክህነት በረከቶችን መስጠት ይችላሉ። አስፈላጊ ሲሆን የቤተክርስቲያን አባላት እነዚህን በረከቶች ከሩቅ የቤተሰብ አባላት፣ ከአገልጋይ ወንድሞች ወይም ከአካባቢ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሊጠይቁም ይችላሉ።

አትም