መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
1.የእግዚአብሔር እቅድ እና በደህንነት እና በዘለዓለማዊ ሕይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራ ውስጥ ያላችሁ ሚና


“1. የእግዚአብሔር እቅድ እና በደህንነት እና በዘለዓለማዊ ሕይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራ ውስጥ ያላችሁ ሚና፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ 2023(እ.አ.አ)።

“1. የደህንነት እና በዘለዓለማዊ ሕይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራ ፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ሰዎች ቤት ሲገነቡ

“1.

የእግዚአብሔር እቅድ እና በደህንነት እና በዘለዓለማዊ ሕይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራ ውስጥ ያላችሁ ሚና

1.0

መግቢያ

በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንድታገለግሉ ተጠርታችኋል። ለአገልግሎታችሁ እናመሰግናለን። በታማኝነት ስታገለግሉ ደስታን ታገኛላችሁ፣ ለብዙዎችም መባረክ ምክንያት ትሆናላችሁ።

ይህ የመመሪያ መፅሀፍ እንደ ክርስቶስ አይነት አገልግሎት መርህ እንድትማሩ እና የሚጠበቅባችሁን ኃላፊነት እንድትረዱ ይረዳችኋል። በቤተክርስትያን ውስጥ ያላችሁን አገልግሎት ከእግዚአብሔር እና ከልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ስራ ጋር አንድ ስታደርጉ እጅግ ውጤታማ ትሆናላችሁ።

1.1

የእግዚአብሔር የደስታ እቅድ

የሰማይ አባት የደስታን እቅድ እንድንካፈል እና በረከቱን በደስታ እንድንቀበል አስችሎናል። ስራው እና ክብሩ “የሰውን ህያውነት እና ዘለአለማዊ ህይወት ለማምጣት” ነው (ሙሴ1፥39)።

ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር እቅድ ዋና ክፍል ነው። የሰማዩ አባታችን ለእኛ ባለው የማያልቅ ፍቅር ምክንያት በኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ከኃጢያት እና ሞት ነጻ ሊያወጣን ልጁን ላከልን (ዮሃንስ 3፥16ን ይመልከቱ)። በእርሱ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ የተወለድን በሙሉ ከሞት እንደምንነሳ እና የዘላለማዊ ህይወትን እንደምናገኝ አረጋግጦልናል። የእርሱ የኃጢያት ክፍያ ከኃጢያት እንድንነጻ እና ልባችን እንዲለወጥ፣ በዚህም የዘለዓለማዊ ህይወት የደስታ ሙላትን እንድንቀበል አስችሎናል።

የዘለዓለማዊ ህይወትን ለመቀበል “ወደ ክርስቶስ [መምጣት]፣ እናም በእርሱም ፍፁማን [መሆን]” አለብን (ሞሮኒ 10፥32)።

1.2

የደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራ

ወደ ክርስቶስ ስንመጣ እና ሌሎችንም እንደዚሁ እንዲያደርጉ ስንረዳቸው፣ በእግዚአብሄር የደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራ ላይ ተሳተፍን ማለት ነው። ይህ ስራ በሁለቱ ታላቅ ትዕዛዛት የተመራ ነው፣ እነርሱም እግዚአብሔርን መውደድ እና ጎረቤትን መውደድ ናችው (ማቴዎስ 22፥37–39 ይመልከቱ)።

የደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ትኩረት የሚያደርገው በአምላክ በተመረጡ አራት ኃላፊነቶች ላይ ነው።

ይህ የአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ እነዚህን አራቱን የእግዚአብሔር ስራ ዘርፎች እንድትረዱ ያግዟችኋል። እነርሱን ለመፈጸም የሚጠበቅባችሁን በምታደርጉበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ይረዳችኋል (2 ኔፊ 32፥5 ይመልከቱ)።

1.2.1

በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር

በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር የሚከተሉትን ያካትታል፦

  • በክርስቶስ ማመን፣ በየቀኑ ንሰሀ መግባት፣ የመዳን እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥርዓቶችን በመቀበል ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን መግባት እና እነዚያን ቃል ኪዳኖች በመጠበቅ እስከ መጨረሻው ድረስ መፅናት (3.5.1 ይመልከቱ)።

  • በቤት እና በቤተክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መማር እና ማስተማር።

  • ለራሳችን እና ለቤተሰባችን የሚያስፈልገውን በማቅረብ ራስን የቻሉ መሆን።

1.2.2

እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መርዳት

እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መርዳት የሚከተሉትን ያካትታል፦

  • ግለሰቦችን፣ ቤተሰቦችን እና ማህበረሰቦችን ማገለልገል።

  • የቤተክርስቲያን ድጋፍን ጨምሮ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሃብትን ማካፈል።

  • ራሳቸውን የቻሉ እንዲሆኑ ሌሎችን መርዳት።

1.2.3

ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ መጋበዝ

ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ መጋበዝ የሚከተሉትን ያካትታል፦

  • በሚስዮናዊ ስራ መሳተፍ እና ሚስዮናዊ በመሆን ማገልገል።

  • አዲስ እና እንደገና የተመለሱ የቤተክርስቲያን አባላት በቃል ኪዳኑ ጎዳና እንዲገፋ መርዳት።

1.2.4

ቤተስቦችን ለዘለዓለም ማጣመር

ቤተስቦችን ለዘለአለም ማጣመር የሚከተሉትን ያካትታል፦

  • የራሳችንን የቤተመቅደስ ሥርዓት ስንፈፅም ቃል ኪዳኖችን መግባት።

  • ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን መግባት ይችሉ ዘንድ በሞት የተለዩንን ቅድመ ዓያቶቻችንን ማግኘት እና በቤተመቅደስ ውስጥ ለእነርሱ ስርዓቶችን መፈጸም።

  • የሚቻል ሲሆን እግዚአብሔርን ለማምለክ እና ሥርዓቶችን ለልጆቹ ለመፈጸም ዘወትር ወደ ቤተመቅደስ መሄድ።

1.3

የቤተክርስቲያኗ ዓላማ

ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኗን ያቋቋመው ግለሰቦች እና ቤተሰቦች የደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራን ለመስራት እዲችሉ ለማድረግ ነው (ኤፌሶን 4፥11–13 ይመልከቱ፤ በተጨማሪም በዚህ የመመሪያ መፅሐፍ ውስጥ 2.2 ይመልከቱ)። ይህ መለኮታዊ ዓላማ እንዲሳካ ለመርዳት ቤተክርስቲያኗ እና መሪዎቿ የሚከተሉትን ያቀርባሉ፦

  • የክህነት ስልጣን እና ቁልፎች።

  • ቃል ኪዳኖች እና ሥርዓቶች።

  • ነቢያዊ መመሪያ

  • ቅዱሳት መጻህፍት።

  • የወንጌል መማር ማስተማር ድጋፍ።

  • የአገልግሎት እና የመሪነት እድሎች

  • የቅዱሳን ማህበረሰብ።

1.3.1

የክህነት ስልጣን እና ቁልፎች

በክህነት አማካኝነት እግዚአብሔር የደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራን ያከናውናል። በምድር የእግዚአብሔርን ስራ ለመምራት የሚያስፈልጉ የክህነት ስልጣን እና ቁልፎች በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ዳግም ተመልሰዋል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110፥11–16112፥30 ይመልከቱ)። ዛሬ እነዚህ ቁልፎች በቤተክርስቲያኗ መሪዎች እጅ ናቸው። በእግዚአብሔር ሥራ ያግዙ ዘንድ ለሌሎች ጥሪ እና ፈቃድ ይሰጣሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥8፣ 65–67 ይመልከቱ)።

1.3.2

ቃል ኪዳኖች እና ሥርዓቶች

በሰማይ አባት እቅድ መሰረት፣ በደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የመደረግን ሥርዓቶች ስንቀበል ቃል ኪዳኖችን እንገባለን (ዮሃንስ 3፥5 ይመልከቱ፤ በተጨማሪም በዚህ የመመሪያ መፅሐፍ ውስጥ ምዕራፍ 18 ይመልከቱ)። እነዚህ ቃል ኪዳኖች እና ሥርዓቶች ይበልጥ እንደ እግዚአብሔር ለመሆን እና ከእርሱ ጋር ለመኖር ለመመለስ በጣም አስፈላጊ ናቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥19–22 ይመልከቱ)።

1.3.3

ነቢያዊ መመሪያ

በተመረጡ ነቢያቶቹ አማካኝነት እግዚአብሔር እውነትን ይገለልጻል እንዲሁም በመንፈስ የተነሳሳ መመሪያ እና ማስጠንቀቂያ ይሰጣል (አሞፅ 3፥7ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥4 ይመልከቱ)። ይህ መመሪያ ወደዘለአለም ህይወት ወደሚመራው ጎዳና እንድንገባ እና በዚያ እንድንረጋ ይረዳናል።

1.3.4

ቅዱሳት መጻህፍት

በጌታ ነቢያት እና ሃዋርያት አመራር ስር፣ ቤተክርስቲያኗ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ቃል ትሰጣለች እንዲሁም ትጠብቃለች። ቅዱሳት መጻህፍት ስለኢየሱስ ይመሰክራሉ፣ ወንጌሉን ያስተምራሉ እንዲሁም በእርሱ እንድናምን ይረዱናል (Jacob 7፥10–11ሔለማን 15፥7 ይመልከቱ)።

1.3.5

የወንጌል መማር ማስተማር ድጋፍ

ግለሰቦች እና ቤተሰቦች የወንጌልን እውነት ለመማር እና እነዚህን እውነቶች ለቤተሰብ አባላት እንዲሁም ለሌሎች ለማስተማር ባለባቸው ኃላፊነት ቤተክርስቲያኗ ትደግፋለች (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥77–78፣ 118 ይመልከቱ፤ በተጨማሪም በዚህ የመመሪያ መፅሐፍ ውስጥ 2.2.3 ይመልከቱ)።

1.3.6

የአገልግሎት እና የመሪነት እድሎች

በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚሰጡ ጥሪዎች እና የስራ ምድቦች አማካኝነት፣ እግዚአብሔር ለአባላት የማገልገል እና የመምራት እድሎችን ይሰጣል። የተቸገሩ አባላትን ለመርዳት እና ለሌሎች ሰብአዊ እርዳታ መስጠት ትችል ዘንድ ቤተክርስቲያኗ መዋቅር ዘርግታለች (ሞዛያ 18፥27–29)።

1.3.7

የቅዱሳን ማህበረሰብ

እንደ ቅዱሳን ማህበረሰብ፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት እግዚአብሔርን ለማምለክ እና ቅዱስ ቁርባኑን በመውሰድ አዳኙን ለማስታወስ ዘወትር ይሰበሰባሉ (ሞሮኒ 6፥4–6ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77 ይመልከቱ)። በተጨማሪም አባላት እርስ በርሳቸው ይተሳሰባሉ እንዲሁም አንዳቸው ሌላውን ያገለግላሉ (ኤፌሶን 2፥19 ይመልከቱ)።

1.4

በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ ያላችሁ ሚና

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ መሪ በመሆን የተጠራችሁት የምታገለግሏቸው በደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ላይ ሲሳተፉ እንድታስተምሯቸው እና እንድትደግፏቸው ነው (1.2ይመልከቱ)። ጥሪያችሁን የማሟላት እና “የእግዚአብሔርን ቃል በሙሉ ትጋት [የማስተማር]” ሃላፊነት አለባችሁ (ያዕቆብ 1፥19)። በእርሱ የወይን እርሻ ውስጥ ከጌታ ጋር መስራት ታላቅ ደስታን ያመጣል (ያዕቆብ 5፥70–72 ይመልከቱ)።

እንድትሰሩ ስለሚጋብዛችሁ ስለእግዚአብሔር ስራ እና ስለቤተክርስቲያኑ አላማ ግልፅ የሆነ ግንዛቤ ማግኘታችሁ፣ በጥረቶቻችሁ ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ በማምጣት ላይ እንድታተኩሩ ይረዳችኋል።

በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያሉትን መርሆዎች ደጋግማችሁ ተመልከቱ። በምታገለግሏቸው ሰዎች ህይወት ውስጥ የእግዚአብሔርን አላማዎች እንዴት እውን ለማድረግ መርዳት እንደምትችሉ ለማወቅ በጸሎት መንፈስ እሹ። በመንፈስ ቅዱስ ማነሳሳት አማካኝነት እግዚአብሔር ይመራችኋል።