“7. የካስማ አመራር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።
“7. የካስማ አመራር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ።
7.
የኤጲስ ቆጶስ አመራር
7.1
ኤጲስ ቆጶሱ እና አማካሪዎቹ
ኤጲስ ቆጶሱ በአጥቢያ ውስጥ ያሉትን የቤተክርስቲያኗን ስራ ለመምራት የሚያስችሉ የክህነት ቁልፎችን ይይዛል (3.4.1ን ይመልከቱ)። እርሱ እና አማካሪዎቹ የኤጲስ ቆጶስ አመራርን ይመሰርታሉ።
ኤጲስ ቆጶሱ አምስት ዋና መሰረታዊ ኃላፊነቶች አሉት፦
-
እሱ በአጥቢያው ውስጥ ከፍተኛ ሊቀ ካህን ነው።
-
እሱ የአሮናዊ ክህነት ፕሬዚዳንት ነው።
-
ዋና ዳኛ ነው።
-
እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መንከባከብን ጨምሮ የደህንነት እና በዘlለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራን ያስተባብራል።
-
መዛግብትን፣ ገንዘብን እና የስብሰባ አዳራሽን አጠቃቀም ይቆጣጠራል።
የኤጲስ ቆጶሱ በአጥቢያው ላሉ መጪ ትውልዶች (ልጆች፣ ወጣቶች እና ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች) ዋና ኃላፊነት አለበት። በዚህ ኃላፊነት ላይ ለማተኮር ይችል ዘንድ ብዙ የሥራ ምደባዎችን በውክልና ይሰጣል (4.2.5 ን ይመልከቱ)።
7.1.1
ከፍተኛ ሊቀ ካህን
ኤጲስ ቆጶሱ የአጥቢያው ዋና መንፈሳዊ መሪ ነው።
7.1.1.1
የአጥቢያ ድርጅቶች እና አሮናዊ የክህነት ቡድኖች
ኤጲስ ቆጶሱ ለአጥቢያው የሴቶች መረዳጃ ማህበር እና ለወጣት ሴቶች ድርጅቶች ኃላፊነት አለበት። አማካሪዎቹን፣ ሰንበት ትምህርት ቤትን እና የመጀመሪያ ክፍል ድርጅቶችን እንዲሁም ሌሎች የአጥቢያ ፕሮግራሞችን በኃላፊነት ይሰጣቸዋል።
ኤጲስ ቆጶሱ አሮናዊ የክህነት ቡድኖችን በተመለከተ ያሉበት ኃላፊነቶች በ7.1.2 ውስጥ ተዘርዝረዋል። ኤጲስ ቆጶሱ የሽማግሌዎች ቡድኖችን በተመለከተ ያሉበት ኃላፊነቶች በ8.3.1 ውስጥ ተዘርዝረዋል።
7.1.1.2
ሥርዓቶች እና በረከቶች
ኤጲስ ቆጶሱ በአጥቢያ ውስጥ የሚከተሉትን የሥርዓቶች እና የበረከቶች አስተደደር ይመራል፦
-
ቅዱስ ቁርባን
-
ልጆችን መሰየም እና በረከት መስጠት
-
በመዝገብ ውስጥ ያሉ 8 ዓመት የሆናቸው ልጆች ጥምቀት እና ማረጋገጫ (አዲስ ለተለወጡ፣ 31.2.3.2ን ይመልከቱ)
-
አሮናዊ ክህነትን መስጠት እንዲሁም በዲያቆን፣ በአስተማሪ፣ እና በሽማግሌ ክፍል መሾም
7.1.1.3
ምክር ቤቶች እና ስብሰባዎች
ኤጲስ ቆጶሱ የአጥቢያ ምክር ቤትን እና የአጥቢያ ወጣቶች ምክር ቤትን ይመራል (29.2.5 እና 29.2.6ን ይመልከቱ)።
የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ የአጥቢያ የቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎችን እና በምዕራፍ 29 ውስጥ የተዘረዘሩትን ሌሎች የአጥቢያ ስብሰባዎች ያቅዳል።
7.1.1.4
ጥሪዎች እና ስንብቶች
ኤጲስ ቆጶሱ ጥሪዎችን እና ስንብቶችን በተመለከተ ያሉበት ኃላፊነቶች በምዕራፍ 30 ውስጥ ተዘርዝረዋል።
7.1.2
የአሮናዊ ክህነት ፕሬዚዳንት
ኤጲስ ቆጶሱ እንደ አሮናዊ ክህነት ፕሬዚዳንት በአጥቢያ ውስጥ የሚከተሉት ኃላፈነቶች አሉበት። አማካሪዎቹ ይረዱታል።
-
ወላጆች ወጣቶችን ሲያስተምሩ ይረዳል።
-
የአሮናዊ ክህነት ቡድኖችን እና የወጣት ሴቶች የትምህርት ክፍሎችን በበላይነት ይቆጣጠራል። ኤጲስ ቆጶሱ የካህናት ቡድን ፕሬዚዳንት ነው ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥87–88ን ይመልከቱ)። የመጀመሪያ አማካሪው የአስተማሪዎች ቡድንን በተመለከተ ኃላፊነት አለበት። ሁለተኛ አማካሪው የዲያቆናት ቡድንን በተመለከተ ኃላፊነት አለበት።
-
ከአጥቢያው የወጣት ሴቶች ፕሬዚዳንት ጋር ይመክራሉ።
-
ከእያንዳንዱ ወጣት ጋር በመደበኛነት ይገናኛል።
7.1.3
ዋና ዳኛ
ኤጲስ ቆጶሱ የአጥቢያው ዋና ዳኛ ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥71–74ን ይመልከቱ)። የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉበት፦
7.1.4
የደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራን ማስተባበር
ኤጲስ ቆጶሱ በአጥቢያው ውስጥ ያለውን የደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራን ያስተባብራል (ምዕራፍ 1ን ይመልከቱ)። አማካሪዎቹ እና ሌሎች የአጥቢያ መሪዎች ያግዙታል።
7.1.4.1
ስጋዊ ፍላጎቶች ያሏቸውን ለመንከባከብ የሚደረጉ ጥረቶችን መምራት
ኤጲስ ቆጶሱ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ስለሚንከባከብበት መንገድ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 22.6.1ን ይመልከቱ።
7.1.5
መዛግብት፣ ገንዘብ እና የመሰብሰቢያ አዳራሽ
ስለመዛግብት መረጃ ለማግኘት፣ ምዕራፍ 33ን ይመልከቱ። አስራትን ጨምሮ ስለገንዘብ መረጃ ለማግኘት፣ ምዕራፍ 34ን ይመልከቱ። ስለመሰብሰቢያ አዳራሾች መረጃ ለማግኘት፣ ምዕራፍ 35ን ይመልከቱ።
7.3
የአጥቢያ ዋና ጸሃፊ እና ረዳት የአጥቢያ ዋና ጸሃፊዎች
የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ አንድ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ የአጥቢያ ዋና ጸሃፊ እንዲሆን በጥቆማ ያቀርባል።
የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉበት፦
-
ከኤጲስ ቆጶስ አመራሩ ጋር ይገናኛል እንዲሁም እንደተሰጠው የውይይት አጀንዳዎችን ያዘጋጃል።
-
የአጥቢያ ምክር ቤት አባል በመሆን ያገለግላል እንዲሁም በአጥቢያ ምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ ይሳተፋል።
-
ለኤጲስ ቆጶስ አመራሩ የቀጠሮ መርሃ ግብር ያስይዛል።
7.4
የአጥቢያ ጸሃፊ እና ረዳት የአጥቢያ ጸሃፊዎች
የአጥቢያ ጸሃፊ እና ረዳት የአጥቢያ ጸሃፊዎች ያሉባቸው ኃላፊነቶች በ33.4.2 ውስጥ ተዘርዝረዋል።