መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
9.የሴቶች መረዳጃ ማህበር


“9. የሴቶች መረዳጃ ማህበር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“9. የሴቶች መረዳጃ ማህበር፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ሴት ቅዱሳት መጻህፍትን ስታጠና

9.

የሴቶች መረዳጃ ማህበር

9.1

ዓላማ እና ድርጅት

9.1.1

ዓላማዎች

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ዓላማ ነፍሳትን ማዳን እና ስቃይን መታደግ እንደሆነ አስተምሯል።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር መፈክር “ፍቅር ዘወትር አይወድቅም” የሚለው ነው (1 ቆሮንቶስ 13፥8)።

9.1.2

በሴቶች መረዳጃ ማህበር አባል መሆን

አንዲት ወጣት ሴት 18 ዓመት ሲሞላት በሴቶች መረዳጃ ማህበር መሳተፍ ልትጀምር ትችላለች። እርሷም 19 ዓመት ሲሆናት ወይም ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ወይም በሚስዮን ለማገልገል ከቤት ስትወጣ በሴቶች መረዳጃ ማህበር መሳተፍ ይገባታል።

ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ያገቡ ሴቶች የሴቶች መረዳጃ ማህበር አባላት ናቸው።

9.2

በደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ በማድረግ ስራ መሳተፍ

3:42

9.2.1

በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር

9.2.1.2

በሴቶች መረዳጃ ማህበር ውስጥ ወንጌልን መማር

ስብሰባዎቹ የሚካሄዱት በወሩ በሁለተኛው እና በአራተኛው እሁድ ላይ ነው። ለ50 ደቂቃዎች ይዘልቃሉ። የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር እነዚህን ስብሰባዎች ያቅዳሉ። ከአመራር አባላት አንዷ ትመራዋለች።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር ስብሰባዎች በጣም የቅርብ ጊዜ በሆነ በአንድ ወይም ከአንድ በላይ የአጠቃላይ ጉባኤ ንግግሮች ውስጥ በተውጣጡ ርዕሶች ላይ ያተኩራሉ።

9.2.1.3

አክቲቪቲዎች

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሮች አክቲቪቲዎችን ሊያቅዱ ይችላሉ። አብዛኞቹ አክቲቪቲዎች ከእሁድ ወይም ከሰኞ ምሽት ውጪ ባሉት ጊዜያት ይካሄዳሉ።

9.2.2

እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መርዳት

2:43

9.2.2.1

አገልግሎት

እህቶች የአገልግሎት የስራ ምደባዎችን ከሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ይቀበላሉ። ለተጨማሪ መረጃ ምዕራፍ 21ን ይመልከቱ።

9.2.2.2

የአጭር ጊዜ ፍላጎቶች

የአገልግሎት እህቶች የሚያገለግሏቸውን ሰዎች ፍላጎት ለማወቅ እና ምላሽ ለመስጠት ይፈልጋሉ። አባላት በህመም ጊዜ፣ በውልደት ጊዜ፣ በሞት ጊዜ፣ ከስራ መፈናቀል በሚከሰትበት ጊዜ እና ሌሎች ሁኔታዎች በሚገጥሟቸው ጊዜ የአጭር ጊዜ እርዳታ ሊፈልጉ ይችላሉ።

አስፈላጊ ሲሆን አገልጋይ እህቶች የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሮችን እርዳታ ይጠይቃሉ።

9.2.2.3

የረዥም ጊዜ ፍላጎቶች እና ራስን መቻል

በኤጲስ ቆጶሱ አስተባባሪነት፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እና የሽማግሌዎች ቡድን አመራሮች የአባላትን የረዥም ጊዜ ፍላጎቶች እና ራስን መቻል እውን በማድረግ ይረዳሉ።

የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት፣ የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት ወይም ሌላ መሪ፣ ግለሰቡ ወይም ቤተሰቡ ራስን የመቻል እቅድ እንዲያዘጋጁ ይረዳል።

9.2.2.4

አንድ የአጥቢያ አባል በሚሞትበት ጊዜ

አንድ የአጥቢያ አባል በሚሞትበት ጊዜ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እና የሽማግሌዎች ቡድን አመራሮች ማጽናኛ እና ድጋፍ ይሰጣሉ። በኤጲስ ቆጶሱ አመራር መሰረት፣ በቀብር ሥርዓቱ አፈጻጸም ላይ ሊረዱ ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ 38.5.8ን ይመልከቱ።

9.2.3

ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ መጋበዝ

የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንቷ የአባላትን የሚስዮናዊ ስራ በመምራት እንድትረዳ ከአመራር አባላቱ አንዷን ትመድባለች። እነዚህን ጥረቶች ለማስተባበር ከሽማግሌዎች ቡድን አመራር ከተመደበው አባል ጋር ትሰራለች (23.5.1ን ይመልከቱ)።

9.2.4

ቤተስቦችን ለዘለዓለም ማጣመር

የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንቷ የአባላትን የሚስዮናዊ ስራ በመምራት እንድትረዳ ከአመራር አባላቱ አንዷን ትመድባለች። እነዚህን ጥረቶች ለማስተባበር ከሽማግሌዎች ቡድን አመራር ከተመደበው አባል ጋር ትሰራለች (25.2.2ን ይመልከቱ)።

2:49

9.3

የሴቶች መረዳጃ ማህበር መሪዎች

9.3.1

ኤጲስ ቆጶስ

ኤጲስ ቆጶሱ ከሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት ጋር አብዛኛውን ጊዜ በየወሩ ይገናኛል። የአገልግሎት እህቶችን አገልግሎት ጨምሮ ስለደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ ስለማድረግ ሥራ ይወያያሉ።

9.3.2

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር

9.3.2.1

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራርን መጥራት

ኤጲስ ቆጶሱ አንዲት ሴት የአጥቢያ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆን እንድታገለገግል ይጠራል። ክፍሉ ትልቅ ከሆነ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንቷ አማካሪዎቿ ሆነው የሚያገለግሉ አንድ ወይም ሁለት ሴቶች በጥቆማ ታቀርባለች።

አንዳንድ ትናንሽ ክፍሎች የወጣት ሴቶች ወይም የመጀመሪያ ክፍል ፕሬዚዳንት ላይኖራቸው ይችላል። በእነዚህ ክፍሎች፣ ወላጆች ለወጣቶች እና ለልጆች ትምህርትን በሚያቅዱበት የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንቷ ልትረዳቸው ትችላለች።

9.3.2.2

ኃላፊነቶች

የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚደንት የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉባት፦ አማካሪዎቿ ይረዷታል።

  • በአጥቢያ ምክር ቤት ታገለግላለች።

  • የሴቶች መረዳጃ ማህበር በደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ውስጥ ለመሳተፍ የሚያደርጋቸውን ጥረቶች ትመራለች (ምዕራፍ 1ን ይመልከቱ)።

  • የአገልጋይ እህቶችን አገልግሎት ታደራጃለች እንዲሁም በበላይነት ትቆጣጠራለች።

  • በኤጲስ ቆጶሱ አመራር መሰረት ከአጥቢያው ጎልማሳ አባላት ጋር ትመካከራለች።

    3:13
  • የሴቶች መረዳጃ ማህበሩ ያላገቡትን እና ያገቡትን ወጣት ጎልማሳ እህቶችች ለማጠናከር የሚያደርጋቸውን ጥረቶች ታስተባብራለች።

  • ከእያንዳንዱ የሴቶች መረዳጃ ማህበሩ አባላት ጋር በግለሰብ ደረጃ ቢያንስ በዓመት አንዴ ትገናኛለች።

  • የመረዳጃ ማህበሩን መዛግብት፣ ሪፖርቶች እና ገንዘብ በበላይነት ትቆጣጠራለች ( LCR.ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ)።

9.3.2.3

የአመራር ስብሰባ

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር እና ጸሃፊዋ በየወቅቱ ይገናኛሉ። ፕሬዚዳንቷ እነዚህን ስብሰባዎች ትመራለች። የመወያያ አጀንዳዎቹ የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

  • እህቶችን እና ቤተበቦቻቸውን እንዴት ማጠናከር እንደሚቻል ማቀድ።

  • የሚስዮናዊ ሥራን እንዲሁም የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ሥራን ማስተባበር።

  • ከአጥቢያ ምክር ቤት ስብሰባዎች ለሚመጡ የስራ ምደባዎች ምላሽ መስጠት።

  • ከአገልግሎት ቃለ መጠይቅ የሚገኙ መረጃዎችን መገምገም።

  • እህቶች በመረዳጃ ማህበር ጥሪዎች እና በምደባዎች እንዲያገለግሉ ግምት ውስጥ ማስገባት።

  • የመረዳጃ ማህበር ስብሰባዎችን እና አክቲቪቲዎችን ማቀድ።

9.3.3

ጸሃፊ

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሩ፣ አንዲት ሴት የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፀሃፊ በመሆን እንድታገለግል በጥቆማ ሊያቀርብ ይችላል።

9.4

ወጣት ሴቶች በሴቶች መረዳጃ ማህበር እንዲሳተፉ በማዘጋጀት መርዳት

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ወጣት ሴቶች በሴቶች መረዳጃ ማህበር ለመሳተፍ እንዲዘጋጁ ለመርዳት ከወጣት ሴቶች፣ ከወላጆቻቸው እና ከወጣት ሴቶች መሪዎች ጋር ይሰራል።

መሪዎች፣ ወጣት ሴቶች እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች ግንኙነታቸውን እንዲያጎለብቱ ዘላቂ እድሎችንም ይሰጣሉ። የአገልግሎት እህቶች በመሆን በአንድነት ማገልገል ግንኙነቶችን ለመፍጠር አንዱ ጠቃሚ መንገድ ነው።

9.6

ተጨማሪ መመሪያዎች እና ፖሊሲዎች

9.6.2

መሠረተ ትምህርት

እንዳስፈላጊነቱ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር፣ አባላት ማንበብ እና መጻፍ እንዲማሩ ለመርዳት ከኤጲስ ቆጶሱ፣ ከሽማግሌዎች ቡድን አመራር እና ከአጥቢያ ምክር ቤት ጋር ይሰራል።