መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
10. የአሮናዊ ክህነት ቡድኖች


“10. የአሮናዊ ክህነት ቡድኖች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“10. የአሮናዊ ክህነት ቡድኖች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ወጣት ወንዶች በቤተክርስቲያን

10.

የአሮናዊ ክህነት ቡድኖች

10.1

ዓላማ እና ድርጅት

10.1.1

ዓላማዎች

የቡድኑ ዓላማ የክህነት ተሸካሚዎች በደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራን ለማከናወን አብረው እንዲሰሩ መርዳት ነው።

10.1.2

አሮናዊ የክህነት ቡድን ጭብጥ

“እኔ የእግዚአብሔር ውድ ልጅ ነኝ፣ እኔ እንድሰራው የሚፈልገው ስራ አለው።

“በሙሉ ልቤ፣ በሙሉ ኃይሌ፣ እና ጉልበቴ እግዚአብሔርን እወዳለሁ፣ ቃል ኪዳኖቼን እጠብቃለሁ እንዲሁም የእርሱን ክህነት ከቤቴ ጀምሮ ሌሎችን ለማገልገል እጠቀማለሁ።

“ለማገልገል፣ ታማኝ ለመሆን፣ ንስሃ ለመግባት እና በየቀኑ ለመሻሻል በየቀኑ ስጥር፣ የቤተመቅደስ በረከቶችን እና የወንጌልን ዘላቂ ደስታ ለመቀበል ብቁ እሆናለሁ።

“እውነተኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር በመሆን ታታሪ ሚስዮናዊ፣ ታማኝ ባል እና አፍቃሪ አባት ለመሆን እዘጋጃለሁ።

“ሁሉም ወደ ክርስቶስ እንዲመጡና የኃጢያት ክፍያውን በረከቶች እንዲቀበሉ በመጋበዝ አለምን ለአዳኙ ዳግም ምፅዓት በማዘጋጀት እረዳለሁ።”

10.1.3

ቡድኖች

10.1.3.1

የዲያቆናት ቡድን

ወጣት ወንዶች 12 ዓመት በሚሞላቸው ዓመት ውስጥ ካለው ጥር ጀምሮ የዲያቆናት ቡድንን ይቀላቀላሉ። በዚህ ጊዜ ዝግጁ እና ብቁ ከሆኑም በዲያቆናት ክፍል ሊሾሙ ይችላሉ።

የዲያቆን ሃላፊነቶች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥57–5984፥111 ውስጥ ተገልጸዋል። ሌሎች ተግባራት ቅዱስ ቁርባንን ማሳለፍ እና ኤጲስ ቆጶሱ በሚያከናውናቸው “ሁሉንም ሥጋዊ ነገሮች በማስተዳደር” ውስጥ መርዳትን ያካትታሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥68)።

10.1.3.2

የአስተማሪዎች ቡድን

ወጣት ወንዶች 14 ዓመት በሚሞላቸው ዓመት ውስጥ ካለው ጥር ጀምሮ የአስተማሪዎች ቡድንን ይቀላቀላሉ። በዚህ ጊዜ ዝግጁ እና ብቁ ከሆኑም በአስተማሪ ክፍል ሊሾሙ ይችላሉ።

አስተማሪዎች ከዲያቆናት ጋር አንድ አይነት ሃላፊነት አለባቸው። ቅዱስ ቁርባንን ያዘጋጃሉ እንዲሁም የአገልግሎት ወንድሞች በመሆን ያገለግላሉ። ተጨማሪ ሃላፊነቶች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥57–5984፥111 ውስጥ ተገልጸዋል።

10.1.3.3

የካህናት ቡድን

ወጣት ወንዶች 16 ዓመት በሚሞላቸው ዓመት ውስጥ ካለው ጥር ጀምሮ የካህናት ቡድንን ይቀላቀላሉ። በዚህ ጊዜ ዝግጁ እና ብቁ ከሆኑም በክህነት ክፍል ሊሾሙ ይችላሉ።

ካህናት ከዲያቆናት እና ከአስተማሪዎች ጋር አንድ አይነት ሃላፊነት አለባቸው። ተጨማሪ ሃላፊነቶች በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥46–52፣ 73–79 ውስጥ ተገልጸዋል።

10.1.4

የክህነት ቁልፎች

ስለእነዚህ ቁልፎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 3.4.1 ን ይመልከቱ።

10.1.5

ቡድኖችን ለአካባቢ በሚመች መልኩ ማስተካከል

ጥቂት ወጣት ወንዶች ባሉባቸው አጥቢያዎች ወይም ቅርንጫፎች፣ የአሮናዊ ክህነት ቡድኖች መመሪያ ለማግኘት እና አክቲቪቲዎችን ለማካሄድ ሊገናኙ ይችላሉ።

10.2

በደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራ መሳተፍ

10.2.1

በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር

10.2.1.2

ወንጌልን መማር

የቡድኖች ስብሰባዎች የሚካሄዱት በወሩ በሁለተኛው እና በአራተኛው እሁድ ላይ ነው። ለ50 ደቂቃዎች ይዘልቃሉ። የቡድን አመራር አባል (ወይንም በክህነት ቡድን ውስጥ ካሉት የኤጲስ ቆጶሱ ረዳቶች አንዱ) ይመራዋል። ጭብጡን በቃል ለማስታወስ በሚለማመዱበት ጊዜ ቡድኑ ይመራል እንዲሁም ስለስራ ምድቦች፣ ሃላፊነቶች እና ሌሎች ጉዳዮች በጋራ ይመክራል።

አንድ የቡድን አባል ወይም ጎልማሳ መሪ የወንጌል ትምህርትን ይመራል።

10.2.1.3

አገልግሎት እና አክቲቪቲዎች

አገልግሎት እና አክቲቪቲዎች ምስክርነቶችን የሚገነቡ፣ የቡድን አንድነትን የሚያሳድጉ እና ሌሎችን ለመባረክ አጋጣሚዎችን የሚሰጡ መሆን አለባቸው።

አንዳንድ አገልግሎት እና አክቲቪቲዎች፣ ወጣት ወንዶችን እና ወጣት ሴቶችን ማካተት አለባቸው በተለይ ትልልቅ ወጣቶች ከሆኑ።

አመታዊ አክቲቪቲዎች ከመደበኛ የወጣቶች አክቲቪቲዎች በተጨማሪ ወጣት ወንዶች በሚከተሉት ውስጥም በየዓመቱ መሳተፍ ይችላሉ፦

  • በአሮናዊ ክህነት ቡድን ካምፕሰፈር (Aaronic Priesthood Quorum Camp Guide [የአሮናዊ ክህነት ቡድን ካምፕ መመሪያ]]ን ይመልከቱ)።

  • በአጥቢያ ወይም በካስማ የወጣቶች ጉባኤ ወይም ለወጣቶች ጥንካሬ (ኤፍኤስዋይ) ጉባኤ።

10.2.1.4

የግል እድገት

ይበልጥ አዳኙን ለመምሰል በሚያደርጓቸው ጥረቶች ወጣቶች በመንፈሳዊ፣ በማህበራዊ፣ በአካል እና በእውቀት ለማደግ ግቦችን እንዲያወጡ ተጋብዘዋል (ሉቃስ 2፥52 ን ይመልከቱ)።

ለተጨማሪ መረጃ ChildrenandYouth.ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ።

10.2.2

እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መርዳት

ኤጲስ ቆጶሱ “ሁሉንም ምድራዊ ነገሮች [ሲያ]ስተዳደር” አሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎች ይረዳሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥68)። በቤተሰቦቻቸው ውስጥ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በወጣቶች አክቲቪቲ ወቅት እና በራሳቸው ሌሎችን ለማገልገል የዘወትር እድሎች ሊኖራቸው ይገባል።

10.2.2.1

አገልግሎት

የአሮናዊ የክህነት ተሸካሚዎች 14 ዓመት በሚሞላቸው በዓመቱ ውስጥ ካለው ከጥር ጀምሮ የአገልግሎት የስራ ምደባ ይቀበላሉ። ለተጨማሪ መረጃ ምዕራፍ 21ን ይመልከቱ።

10.2.3

ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ መጋበዝ

የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎች “ሁሉንም ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ [የ]መጋበዝ“ ሃላፊነት አለባቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥59)።

ወጣት ወንዶች የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ለመስጠት እና ህይወታቸውን ሙሉ ወንጌልን ለማካፈል እንዲዘጋጁ ወላጆች እና መሪዎች ያበረታታሉ።

10.2.4

ቤተስቦችን ለዘለዓለም ማጣመር

የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎች በብዙ መንገዶች ቤተሰቦችን ለዘለዓለም በማጣመር መርዳት ይችላሉ።

  • ወላጆቻቸውን ያከብራሉ እንዲሁም በቤታቸው የክርስቶስ መሰል አኗኗር ምሳሌን ያስቀምጣሉ።

  • ዘለዓለማዊ ጋብቻን ጨምሮ የቤተመቅደስ ሥርዓቶችን ለመቀበል ይዘጋጃሉ።

  • የቤተመቅደስ ሥርዓቶች የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ዓያቶቻቸውን ያገኛሉ ( FamilySearch.org)ይመልከቱ።

  • ሁኔታቸው እንደፈቀደ በሙታን ጥምቀቶች እና የአባልነት ማረጋገጫ መቀበል ላይ ይሳተፋሉ።

10.3

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

የኤጲስ ቆጶሱ ዋነኛው ኃላፊነት የአጥቢያቸውን ወጣት ወንዶች እና ወጣት ሴቶች መንከባከብ ነው። ስሞቻቸውን ያጠናል እንዲሁም የቤት ሁኔታቸውን ይረዳል። በአክቲቪቲዎቻቸው እና በእሁድ ስብሰባዎች ላይ ዘወትር ይገኛል።

ኤጲስ ቆጶሱ የክህነት ቡድን ፕሬዚዳንት ነው።

በኤጲስ ቆጶስ አመራር የመጀመሪያ አማካሪው የአስተማሪዎች ቡድንን በተመለከተ ኃላፊነት አለበት። ሁለተኛ አማካሪው የዲያቆኖች ቡድንን በተመለከተ ኃላፊነት አለበት።

ኤጲስ ቆጶሱ አሮናዊ ክህነትን በተመለከተ የሚከተሉት ተጨማሪ ኃላፈነቶች አሉበት፦

  • ከእያንዳንዱ ወጣት ወንድ ጋር ቢያንስ በዓመት ሁለት ጊዜ ይገናኛል (31.3.1ን ይመልከቱ)።

  • ወጣት ወንዶች የመልከ ጼዴቅ ክህነትን እንዲቀበሉ በማዘጋጀት ይረዳል።

  • የአሮናዊ ክህነት ቡድንን መዛግብት፣ ሪፖርቶች እና ገንዘብ በበላይነት ይቆጣጠራል።

የቡድን አማካሪዎች እና ስፔሻስቶች በተጠየቁ ጊዜ እነዚህን ኃላፊነቶች የተመለከቱ እገዛዎች ይሰጣሉ።

10.4

የወጣቶች ቡድን መሪዎች

10.4.1

ጥሪ፣ ድጋፍ አሰጣጥ እና ለአገልግሎት መለየት

ኤጲስ ቆጶሱ የክህነት ቡድኑን ለመምራት አንድ ወይም ሁለት ካህናት ረዳቶቹ እንዲሆኑ ይጠራል።

የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ የዲያቆናት እና የአስተማሪዎች ቡድን ፕሬዚዳንቶችን ይጠራል። አገልግሎት የሚሰጣቸው በቂ የአሮናዊ ክህነት ተሸካሚዎች ሲኖሩ፣ እነዚህ ወጣት ወንዶች በአማካሪነት እና በፀሀፊነት የሚያገለግሉትን በጥቆማ በማቅረብ የቡድን አባላትን በጸሎት መንፈስ ግምት ውስጥ ያስገባሉ።

እነዚህን ጥሪዎች ከሰጠ በኋላ፣ አንድ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል የወጣቶች ቡድን መሪዎች ድጋፍ እንዲሰጣቸው በቡድናቸው ስብሰባ ላይ ያቀርባቸዋል። ኤጲስ ቆጶሱ ረዳቶቹን እንዲሁም የዲያቆናት እና የአስተማሪዎች ቡድን ፕሬዚዳንቶችን ለአገልግሎት ይለያቸዋል። የክህነት ቁልፎችን ለቡድን ፕሬዚዳንቶች ይሰጣል። ሌሎች የአመራር አባላትን እና ጸሃፊዎችን ለአገልግሎት እንዲለዩ አማካሪዎቹን ሊመድብ ይችላል።

10.4.2

ኃላፊነቶች

  • ቡድኑ በደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ውስጥ ለመሳተፍ የሚያደርጋቸውን ጥረቶች ይመራል (ምዕራፍ 1ን ይመልከቱ)።

  • በቡድኑ ስብሰባዎች ላይ የማይሳተፉትን ጨምሮ፣ እያንዳንዱን የቡድን አባል ጋር ይተዋወቃል እንዲሁም ያገለግላል።

  • በአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት ውስጥ ያገለግላል (10.4.4ን ይመልከቱ)።

  • የቡድኑን አባላት ስለክህነት ሃላፊነቶቻቸው ያስተምራል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥85–88ን ይመልከቱ)።

  • የቡድን ስብሰባዎችን ያቅዳል እንዲሁም ይመራል (10.2.1.2ን ይመልከቱ)።

  • የቡድን አገልግሎቶችን ያቅዳል እንዲሁም ይፈፅማል (10.2.1.3ን ይመልከቱ)።

10.4.3

የቡድን አመራር ስብሰባ

የአሮናዊ ክህነት ቡድን አመራሮች በየወቅቱ ይገናኛሉ። የቡድኑ ፕሬዚዳንት እነዚህን ስብሰባዎች ይመራል። ቢያንስ ሁለት ጎልማሶች ይሳተፋሉ—ከኤጲስ ቆጶስ አመራር አንዱ፣ አንድ አማካሪ ወይንም አንድ ስፔሻሊስት።

10.4.4

የአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት

ስለአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 29.2.6ን ይመልከቱ።

10.8

ተጨማሪ መመሪያዎች እና ፖሊሲዎች

10.8.1

ለወጣቶች ጥበቃ ማድረግ

ጎልማሶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ከወጣቶች ጋር ሲገናኙ ቢያንስ ሁለት ኃላፊነት የሚሰማቸው ጎልማሶች መገኘት አለባቸው።

ከወጣቶች ጋር የሚሰሩ ጎልማሶች ሁሉ ድጋፍ በተሰጣቸው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የልጆች እና የወጣቶች ጥበቃ ስልጠናን ማጠናቀቅ አለባቸው (ProtectingChildren.ChurchofJesusChrist.org)ይመልከቱ።