“11. ወጣት ሴቶች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።
“11. ወጣት ሴቶች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ
11.
ወጣት ሴቶች
11.1
ዓላማ እና ድርጅት
11.1.1
ዓላማዎች
የወጣት ሴቶች ድርጅት፣ ወጣት ሴቶች ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን እንዲገቡ እና እንዲጠብቋቸው እንዲሁም ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ወደ ወንጌሉ የሚያደርጉት መለወጥ ጥልቅ እንዲሆን ይረዳል።
11.1.2
የወጣት ሴቶች ጭብጭ
“እኔ መለኮታዊ ፍጥረት የሆንኩኝ እና ዘለዓለማዊ እጣፋንታ ያለኝ የተወደድኩ የሰማያዊ ወላጆች ሴት ልጅ ነኝ፡፡
“የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር እንደመሆኔ መጠን እንደ እርሱለመሆን እጥራለሁ። ግላዊ ራእይን እሻለሁ፣ በሱም መሰረት እተገብራለሁ እንዲሁም በተቀደሰ ስሙ ሌሎችን አገለግላለሁ።
“በሁሉም ጊዜ እና በሁሉም ነገር እንዲሁም በሁሉም ቦታ የእግዚአብሔር ምስክር ሆኜ እቆማለሁ፡፡
“በዘላለማዊ ህይወት ውስጥ ከፍ ከፍ ለመደረግ ብቁ ለመሆን ስጥር፣ የንስሀ ስጦታን አጥብቄ ይዛለው እንዲሁም በየቀኑ ለመሻሻል እሻለሁ፡፡ በእምነት ቤቴን እና ቤተሰቤን አጠነክራለሁ፣ የተቀደሱ ቃል ኪዳኖችን እፈጽማለውእንዲሁም እጠብቃለሁ፣ የቤተመቅደስ ስርዓቶችን እና በረከቶችን እቀበላለሁ፡፡”
11.1.3
የትምህርት ክፍሎች
ወጣት ሴቶች 12 ዓመት በሚሞላቸው በዓመቱ ውስጥ ካለው ጥር ጀምሮ የወጣት ሴቶች የትምህርት ክፍልን ይቀላቀላሉ።
የኤጲስ ቆጶስ አመራሮች እና ጎልማሳ ወጣት ሴት መሪዎች የትምህርት ክፍሎችን እንዴት በእድሜ እንደሚያደራጁ በጸሎት ይወስናሉ። እያንዳንዱ የትምህርት ክፍል መጠኑ ምንም ይሁን ምን ፕሬዚዳንት ሊኖረው ይገባል እንዲሁም የሚቻል ሲሆን አንድ ወይም ሁለት አማካሪዎች እና ጸሐፊ ይኖረዋል።
11.2
በደህንነት እና በዘላለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራ መሳተፍ
11.2.1
በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር
11.2.1.2
ወንጌልን መማር
የትምህርት ክፍል ስብሰባዎች የሚካሄዱት በወሩ በሁለተኛው እና በአራተኛው እሁድ ላይ ነው። ለ50 ደቂቃዎች ይዘልቃሉ። ከትምህርት ክፍሉ አመራር አባላት አንዷ ትመራዋለች። ጭብጡን በቃል ለማስታወስ በሚለማመዱበት ጊዜ የትምህርት ክፍሉን ትመራለች እንዲሁም ስለስራ ምድቦች፣ ሃላፊነቶች እና ሌሎች ጉዳዮች በጋራ ትመክራለች።
አንድ የትምህርት ክፍል አባል ወይም ጎልማሳ መሪ የወንጌል ትምህርትን ይመራል።
11.2.1.3
አገልግሎት እና አክቲቪቲዎች
አገልግሎት እና አክቲቪቲዎች ምስክርነቶችን የሚገነቡ፣ የቡድን አንድነትን የሚያሳድጉ እና ሌሎችን ለመባረክ አጋጣሚዎችን የሚሰጡ መሆን አለባቸው።
አንዳንድ አገልግሎት እና አክቲቪቲዎች ወጣት ወንዶችን እና ወጣት ሴቶችን ማካተት አለባቸው፣ በተለይ ትልልቅ ወጣቶች ከሆኑ።
አመታዊ አክቲቪቲዎች ከመደበኛ የወጣቶች አክቲቪቲዎች በተጨማሪ ወጣት ሴቶች በሚከተሉት ውስጥም በየዓመቱ መሳተፍ ይችላሉ፦
-
የወጣት ሴቶች ካምፕ (Young Women Camp Guide [የወጣት ሴቶች ካምፕ መመሪያ]ን ይመልከቱ)።
-
በአጥቢያ ወይም በካስማ የወጣቶች ጉባኤ ወይም ለወጣቶች ጥንካሬ(ኤፍኤስዋይ) ጉባኤ።
11.2.1.4
የግል እድገት
ይበልጥ አዳኙን ለመምሰል በሚያደርጓቸው ጥረቶች ወጣቶች በመንፈሳዊ፣ በማህበራዊ፣ በአካል እና በእውቀት ለማደግ ግቦችን እንዲያወጡ ተጋብዘዋል (ሉቃስ 2፥52ን ይመልከቱ)።
ለተጨማሪ መረጃ ChildrenandYouth.ChurchofJesusChrist.orgመረጃ።
11.2.2
እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መርዳት
ወጣት ሴቶች በቤተሰቦቻቸው ውስጥ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በወጣቶች አክቲቪቲ ወቅት እና በራሳቸው ሌሎችን ለማገልገል የዘወትር እድሎች ሊኖራቸው ይገባል።
11.2.2.1
አገልግሎት
ወጣት ሴቶች 14 ዓመት በሚሞላቸው ዓመት ውስጥ ካለው ጥር ጀምሮ የአገልግሎት የስራ ምደባ ይቀበላሉ። ለተጨማሪ መረጃ ምዕራፍ 21ን ይመልከቱ።
11.2.3
ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ መጋበዝ
ወጣት ሴቶች “በሁሉም ጊዜ በሁሉም ነገር፣ የእግዚአብሔር ምስክር በመሆን [ሲቆሙ]” ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ ይጋብዛሉ (ሞዛያ 18፥9)።
ወላጆች እና መሪዎች፣ ወጣት ሴቶች በህይወታቸው በሙሉ ወንጌልን ለማካፈል እንዲዘጋጁ ሊረዷቸው ይችላሉ።
11.2.4
ቤተስቦችን ለዘለዓለም ማጣመር
ወጣት ሴቶች በብዙ መንገዶች ቤተሰቦችን ለዘለዓለም በማጣመር መርዳት ይችላሉ።
-
ወላጆቻቸውን ያከብራሉ እንዲሁም በቤታቸው የክርስቶስ መሰል አኗኗር ምሳሌን ያስቀምጣሉ።
-
ዘለዓለማዊ ጋብቻን ጨምሮ የቤተመቅደስ ሥርዓቶችን ለመቀበል ይዘጋጃሉ።
-
የቤተመቅደስ ሥርዓቶች የሚያስፈልጓቸውን ቅድመ ዓያቶቻቸውን ይለያሉ ( FamilySearch.org)ይመልከቱ።
-
ሁኔታቸው እንደፈቀደ በሙታን ጥምቀቶች እና ማረጋገጫዎች ይሳተፋሉ።
11.3
የአጥቢያ የወጣት ሴቶች መሪዎች
11.3.1
የኤጲስ ቆጶስ አመራር
የኤጲስ ቆጶሱ እጅግ አስፈላጊ ኃላፊነት የአጥቢያቸውን ወጣት ሴቶች እና ወጣት ወንዶች መንከባከብ ነው። እርሱ እና አማካሪዎቹ ስሞቻቸውን ያጠናሉ እንዲሁም የቤት ሁኔታቸውን ይረዳሉ። ከእያንዳንዷ ወጣት ሴት ጋር ቢያንስ በዓመት ሁለት ጊዜ ይገናኛል (31.3.1ን ይመልከቱ)።
ኤጲስ ቆጶሱ ለአጥቢያው ወጣት ሴቶች ድርጅት ኃላፊነት አለበት። ከአጥቢያው የወጣት ሴቶች ፕሬዚዳንት ጋር በየወቅቱ ይገናኛሉ።
ኤጲስ ቆጶሱ እና አማካሪዎቹ በወጣት ሴቶች ስብሰባዎች፣ አገልግሎት እና አክቲቪቲዎች ላይ በየወቅቱ ይሳተፋሉ።
11.3.2
የጎልማሳ ወጣት ሴቶች አመራር
ኤጲስ ቆጶሱ አንዲት ጎልማሳ ሴት የአጥቢያ ወጣት ሴቶች ፕሬዚዳንት በመሆን እንድታገለገግል ይጠራታል፤ እንዲሁም ለአገልግሎት ይለያታል። ክፍሉ ትልቅ ከሆነ አማካሪዎቿ ሆነው የሚያገለግሉ አንድ ወይም ሁለት ሴቶችን በጥቆማ ታቀርባለች (ምራፍ 30 ን ይመልከቱ)።
ክፍሉ ትንሽ ከሆነ፣ የወጣት ሴቶች ፕሬዘዳንቷ በወጣት ሴቶች ድርጅት ውስጥ የምትጠራ ብቸኛዋ ጎልማሳ መሪ ልትሆን ትችላለች። በዚህ ሁኔታ ለወጣት ሴቶች ትምህርቶችን እና አክቲቪቲዎችን ለማደራጀት ከወላጆች ጋር ትሰራለች።
አንድ ቅርንጫፍ የወጣት ሴቶች ፕሬዚዳንት ከሌለው፣ የወጣት ሴቶች ፕሬዚዳንት እስኪጠራ ድረስ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንቷ ለወጣት ሴቶች ትምህርትን ማደራጀት ትችላለች።
የወጣት ሴቶች ፕሬዚዳንት የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሏት። አማካሪዎቿ ይረዷታል።
11.3.4
የትምህርት ክፍል አመራር እና ጸሃፊ
11.3.4.1
ጥሪ፣ ድጋፍ አሰጣጥ እና ለአገልግሎት መለየት
እያንዳንዱ የወጣት ሴቶች የትምህርት ክፍል የትምህርት ክፍል አመራር ሊኖረው ይገባል።
አንድ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል አንዲት ወጣት ሴትን የትምህርት ክፍል ፕሬዚዳንት ሆና እንድታገለግል ይጠራል። አገልግሎት የሚሰጣቸው በቂ ወጣት ሴቶች ሲኖሩ፣ በአማካሪነት እና በፀሀፊነት የሚያገለግሉትን በጥቆማ ለማቅረብ የትምህርት ክፍል አባላትን በጸሎት መንፈስ ግምት ውስጥ ታስገባለች።
እነዚህን ጥሪዎች ከሰጠ በኋላ፣ አንድ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል ወጣት ሴቶቹ ድጋፍ እንዲሰጣቸው በትምህርት ክፍላቸው ያቀርባቸዋል። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የተመደበው አማካሪ ወጣት ሴቶቹን ለአገልግሎት ይለያቸዋል።
11.3.4.2
ኃላፊነቶች
የትምህርት ክፍሎች ፕሬዚዳንቶች፣ በአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት ውስጥ ያገለግላሉ (11.3.4.4ን ይመልከቱ)። የትምህርት ክፍል አመራሮች የሚከተሉት ኃላፊነቶችም አሉባቸው፦
11.3.4.3
የክፍል አመራር ስብሰባ
የወጣት ሴቶች የትምህርት ክፍል አመራሮች በየወቅቱ ይገናኛሉ። የትምህርት ክፍሉ ፕሬዚዳንት እነዚህን ስብሰባዎች ትመራለች። የትምህርት ክፍል አመራሮችን እንዲረዱ የተመደቡት ጎልማሳ ወጣት ሴቶችም ይሳተፋሉ።
11.3.4.4
የአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት
ስለአጥቢያ የወጣቶች ምክር ቤት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 29.2.6 ን ይመልከቱ።
11.6
ተጨማሪ መመሪያዎች እና ፖሊሲዎች
11.6.1
ለወጣቶች ጥበቃ ማድረግ
አዋቂዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ ከወጣቶች ጋር ሲገናኙ ቢያንስ ሁለት ኃላፊነት የሚሰማቸው ጎልማሶች መገኘት አለባቸው። ይህ እንዲሆን የትምህርት ክፍሎችን ማዋሃድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
ከወጣቶች ጋር የሚሰሩ ጎልማሶች ሁሉ ድጋፍ በተሰጣቸው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የልጆች እና የወጣቶች ጥበቃ ስልጠናን ማጠናቀቅ ProtectingChildren.ChurchofJesusChrist.orgአለባቸው( )።