መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
12. የመጀመሪያ ክፍል


“12. “የመጀመሪያ ክፍል፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“12. የመጀመሪያ ክፍል፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍትን ይዘው

12.

የመጀመሪያ ክፍል

12.1

ዓላማ እና ድርጅት

የመጀመሪያ ክፍል ቤትን ያማከለ በቤተክርስቲያን የተደገፈ ድርጅት ነው። ከ18 ወር እስከ 11 ዓመት ለሆናቸው ልጆች የተዘጋጀ ነው።

12.1.1

ዓላማ

የመጀመሪያ ክፍል ልጆችን በሚከተሉት መንገዶች ይረዳቸዋል፦

  • የሰማይ አባታቸው ፍቅር ይሰማቸዋል እንዲሁም ስለደስታ ዕቅዱ ይማራሉ።

  • ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና በሰማይ አባት እቅድ ውስጥ ስላለው ሚና ይማራሉ።

  • የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ይማራሉ እንዲሁም ይኖራሉ።

  • የመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖዎች ይሰሟቸዋል፣ ይለዩታል እንዲሁም ተግባራዊ እርምጃ ይወስዳሉ።

  • ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን ለመግባት እና ለመጠበቅ ይዘጋጃሉ።

  • በደህንነት እና በዘላለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራ ይሳተፋሉ።

12.1.3

የትምህርት ክፍሎች

በቂ ልጆች በሚኖሩበት ጊዜ በእድሜያቸው መሰረት በትምህርት ክፍሎች ይከፈላሉ።

ልጆች 12 ዓመት በሚሞላቸው ዓመት ውስጥ ካለው ጥር ጀምሮ ወደ ወጣት ሴቶች ወይንም ወደ ዲያቆናት ቡድኖች ይሸጋገራሉ።

12.1.4

የመዝሙር ጊዜ

የመዝሙር ጊዜ፣ ልጆች የሰማይ አባታቸው ፍቅር እንዲሰማቸው እና ስለደስታ ዕቅዱ እንዲማሩ ይረዳል። ልጆች ስለወንጌል መርሆዎች በሚዘምሩበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ስለእውነትነቱ ይመሰክርላቸዋል።

የመጀመሪያ ክፍል ፕሬዚዳንቱ እና የሙዚቃ መሪው፣ ልጆቹ በትምህርት ክፍላቸው እና በቤት ውስጥ እየተማሯቸው ያሉትን የወንጌል መርሆዎች ለማጠናከር ለእያንዳንዱ ወር መዝሙሮችን ይመርጣሉ።

12.1.5

የህጻናት ክፍል

የህጻናት ክፍል፣ ከ18 ወር እስከ 3 ዓመት የሚሆናቸው ልጆች የሰማይ አባታቸው ፍቅር እንዲሰማቸው እና ስለደስታ ዕቅዱ እንዲማሩ ይረዳል።

12.2

በደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራ መሳተፍ

12.2.1

በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር

12.2.1.2

ወንጌልን መማር

የእሁድ የመጀመሪያ ክፍል ስብሰባዎች። ከመጀመሪያ ክፍል አመራር አባላት አንዱ መክፈቻውን ይመራል።

መርሃ ግብሩ እንደሚከተለው ነው።

የስብሰባ ክፍል

ርዝመት

የስብሰባ ክፍል

መክፈቻ(ጸሎት፣ ቅዱሳት መጻህፍት ወይም የእምነት አንቀፅ እና ንግግር—ሁሉም በልጆች የሚሰጡ)

ርዝመት

(5 ደቂቃ)

የስብሰባ ክፍል

የመዝሙር ጊዜ

ርዝመት

(20 ደቂቃ)

የስብሰባ ክፍል

ከክፍል ወደ ክፍል መሸጋገሪያ

ርዝመት

(5 ደቂቃ)

የስብሰባ ክፍል

የትምህርት ክፍሎች እና የመዝጊያ ጸሎት

ርዝመት

(20 ደቂቃ)

ዕድሜያቸው ከ18 ወር እስከ 3 ዓመት ለሆኑ ሕፃናት የሚዘጋጀው የህጻናት ክፍል ለ50 ደቂቃዎች ይዘልቃል። Behold Your Little Ones [ትንንሾቻችሁን ተመልከቱ] የሚመከር መርሃ ግብርን ይሰጣል።

የልጆች የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ዝግጅት ዓመታዊው የልጆች የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ዝግጅት በዓመቱ የመጨረሻዎቹ ወራት ውስጥ ይካሄዳል።

የመጀመሪያ ክፍል አመራር እና የሙዚቃ መሪው በጸሎት መንፈስ ዝግጅቱን ያቅዳሉ። የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ መመሪያ ይሰጣል። ልጆች መዘመር፣ ንግግር መስጠት እና ታሪኮችን፣ ቅዱሳት መጻህፍትን መጥቀስ ወይም ምስክርነቶችን ማካፈል ይችላሉ።

የቤተመቅደስ እና የክህነት ዝግጅት ስብሰባ። የመጀመሪያ ክፍል አመራር በየዓመቱ የቤተመቅደስ እና የክህነት ዝግጅት ስብሰባን ያቅዳል። የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ መመሪያ ይሰጣል። ስብሰባው 10 ዓመት ለሆናቸው ልጆች የተዘጋጀ ነው። ወላጆች ይጋበዛሉ።

12.2.1.3

አገልግሎት እና አክቲቪቲዎች

ከጥር ወር ጀምሮ 8 ዓመት የሚሞላቸው ልጆች በመጀመሪያ ክፍል አክቲቪቲዎች ላይ መሳተፍ ሊጀምሩ ይችላሉ።

የመጀመሪያ ክፍል አክቲቪቲዎች ከእሁድ ወይም ከሰኞ ምሽት ውጪ ባሉት ጊዜያት ይካሄዳሉ።

  • የሚቻል ሲሆን፣ የመጀመሪያ ክፍል አክቲቪቲዎች በወር ሁለት ጊዜ ይካሄዳሉ።

  • ወንዶች እና ሴቶች በተለምዶ ለየብቻ ይሰበሰባሉ። ሆኖም፣ የተወሰኑ ተግባራትን ለማከናወን ወይም ጥቂት ልጆች ባሉባቸው ቦታዎች ሊዋሃዱ ይችላሉ።

ኤጲስ ቆጶሱ፣ በመጀመሪያ ክፍል የወንድ እና የሴት ልጆች በጀት እና አክቲቪቲዎች በቂ እና ፍትሃዊ መሆናቸውን ያረጋግጣል።

12.2.1.4

የግል እድገት

ይበልጥ አዳኙን ለመምሰል በሚያደርጓቸው ጥረቶች ልጆች—እድሜያቸው 8 በሚሞላበት ዓመት በመንፈሳዊ፣ በማህበራዊ፣ በአካል እና በእውቀት ለማደግ ግቦችን እንዲያወጡ ተጋብዘዋል (ሉቃስ 2፥52ን ይመልከቱ)።

ግቦችን ለማውጣት እና ለመመዝገብ Personal Development: Children’s Guidebook [የግል እድገት፦ የልጆች መመሪያ መፅሐፍ] መጠቀም ይችላሉ።

12.3

የአጥቢያ የመጀመሪያ ክፍል መሪዎች

12.3.1

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

የኤጲስ ቆጶሱ የመጀመሪያ ኃላፊነት ልጆችን ጨምሮ መጪው ትውልድ ናቸው። ኤጲስ ቆጶሱ በመጀመሪያ ክፍል ላለበት ኃላፊነት እንዲረዳው አንድ አማካሪን ሊመድብ ይችላል። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የተመደበው አማካሪ ከመጀመሪያ ክፍል ፕሬዚዳንቱ ጋር በየወቅቱ ይገናኛል።

ኤጲስ ቆጶሱ እና አማካሪዎቹ በየወቅቱ በመጀመሪያ ክፍል ይሳተፋሉ።

12.3.2

የመጀመሪያ ክፍል አመራር

ኤጲስ ቆጶሱ አንዲት ጎልማሳ ሴትን የአጥቢያ የመጀመሪያ ክፍል ፕሬዚዳንት በመሆን እንድታገለገግል ይጠራታል፤ እንዲሁም ለአገልግሎት ይለያታል።

ክፍሉ ትንሽ ከሆነ፣ የመጀመሪያ ክፍል ፕሬዘዳንቷ ብቸኛዋ የተጠራች መሪ ልትሆን ትችላለች። በዚህ ሁኔታ ትምህርቶችን፣ የመዝሙር ጊዜን እና አክቲቪቲዎችን ለማደራጀት ከወላጆች ጋር ትሰራለች። ክፍሉ ትልቅ ከሆነ፣ ተጨማሪ ጥሪዎች በዚህ ቅደም ተከተል መሰረት ይሞላሉ፦ አማካሪዎች፣ የሙዚቃ መሪ፣ አስተማሪዎች እና የህጻናት ክፍል መሪዎች፣ ጸሃፊ እንዲሁም የአክቲቪቲ መሪዎች ናቸው።

የመጀመሪያ ክፍል አመራር፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ቃል ኪዳኑ መንገድ እንዲገቡ እና ዕድገት እንዲያሳዩ ለማዘጋጀት ይረዳል።

ይህንን ለማድረግ፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ለመጠመቅ እና ማረጋገጫ ለማግኘት እንዲያዘጋጁ ለመርዳት የመጀመሪያ ክፍል ፕሬዚዳንቷ ከአመራር አባላት አንዷን ልትመድብ ትችላለች። የመጀመሪያ ክፍል ፕሬዚዳንቷ፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ለቤተመቅደስ እና ለክህነት ሲያዘጋጁ እንድትረዳቸው ሌላ የአመራር አባል ልትመድብ ትችላለች።

የመጀመሪያ ክፍል ፕሬዚዳንቷ የሚከተሉት ተጨማሪ ኃላፊነቶች አሉባት። አማካሪዎቿ ይረዷታል።

  • በአጥቢያ ምክር ቤት ታገለግላለች።

  • የመጀመሪያ ክፍል አመራር ስብሰባዎችን በየወቅቱ ታካሂዳለች።

  • በተጠየቀች ጊዜ በመዝገብ ውስጥ ላሉ ልጆች የጥምቀት ፕሮግራሞችን በማቀድ ትረዳለች (18.7.2ን ይመልከቱ)።

  • የእሁድ የመጀመሪያ ክፍል ስብሰባዎችን መክፈቻ ታቅዳለች እንዲሁም ትመራለች።

  • የመጀመሪያ ክፍል ልጆችን፣ አስተማሪዎችን እና መሪዎችን በግለሰብ ደረጃ ታገለግላለች።

  • የመጀመሪያ ክፍል መሪዎችን እና አስተማሪዎችን ስለኃላፊነቶቻቸው ታስተምራለች እንዲሁም ስለጥሪዎቻቸው ገለጻ በመስጠት በኃላፊነቶቻቸው ትረዳቸዋለች (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር] [2016(እ.አ.አ)]፣ 38ይመልከቱ)።

  • የመጀመሪያ ክፍልን መዛግብት፣ ሪፖርቶች እና ገንዘብ በበላይነት ትቆጣጠራለች።

12.3.4

የሙዚቃ መሪ እና ፒያኖ ተጫዋች

የሙዚቃ መሪዋ እና ፒያኖ ተጫዋቿ በመዝሙር ጊዜ በሙዚቃ አማካኝነት ልጆችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌልታስተምራለች።

ፒያኖ ተጫዋች ወይም ፒያኖ ከሌለ መሪዎች ቅጂን መጠቀም ይችላሉ።

12.3.5

አስተማሪዎች እና የህጻናት ክፍል መሪዎች

የመጀመሪያ ክፍል አመራር፣ ወንዶችን እና ሴቶችን የመጀመሪያ ክፍል አስተማሪዎች እና የህጻናት ክልፍ መሪዎች በመሆን እንዲያገለግሉ ለኤጲስ ቆጶስ አመራሩ በጥቆማ ያቀርባል። እነዚህ አባላት በተወሰኑ የዕድሜ ክልሎች ያሉ ልጆችን እንዲያስተምሩ እና እንዲያገለግሉ ተጠርተዋል።

ኑ፤ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል (እድሜ 3–11) እና Behold Your Little Ones [ትንንሾቻችሁን ተመልከቱ] (የህጻናት ክፍል)።

12.3.6

የአክቲቪቲ መሪዎች

የመጀመሪያ ክፍል አክቲቪቲ መሪዎች አገልግሎትን እና አክቲቪቲዎችን ሲያቅዱ እድሜያቸው 8 በሚሞላበት ዓመት ካለው ጥር ጀምሮ ልጆችን ያገለግላሉ (12.2.1.3 ይመልከቱ)። አገልግሎት እና አክቲቪቲዎች በደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። አስደሳች እና አሳታፊ ናቸው።

12.5

ተጨማሪ መመሪያዎች እና ፖሊሲዎች

12.5.1

ለልጆች ጥበቃ ማድረግ

ጎልማሶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ከልጆች ጋር ሲገናኙ ቢያንስ ሁለት ኃላፊነት የሚሰማቸው ጎልማሶች መገኘት አለባቸው።

ከልጆች ጋር የሚሰሩ ጎልማሶች ሁሉ ድጋፍ በተሰጣቸው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የልጆች እና የወጣቶች ጥበቃ ስልጠናን ማጠናቀቅ አለባቸው ProtectingChildren.ChurchofJesusChrist.orgአለባቸው( )።