መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
15. የሀይማኖት መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች እና ኢንስቲትዩቶች


“15. የሀይማኖት መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች እና ኢንስቲትዩቶች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“15. የሀይማኖት መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች እና ኢንስቲትዩቶች፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ወጣት ሴት በክፍል ውስጥ እጇን አውጥታ

15.

የሀይማኖት መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች እና ኢንስቲትዩቶች

15.0

መግቢያ

የሀይማኖት መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች እና ኢንስቲትዩቶች (መ&ኢ) ወጣቶች እና ወጣት ጎልማሶች በኢየሱስ ክርስቶስ እና በዳግም በተመለሰው ወንጌል ላይ ያላቸውን እምነት እንዲያሳድጉ በመርዳት ወላጆችን እና መሪዎችን ያግዛሉ።

መ&ኢ ተወካይ፣ መሪዎች የመ&ኢ ፕሮግራሞችን እንዲያስተዳድሩ ለመርዳት ለእያንዳንዱ ካስማ ይመደባል።

15.1

መንፈሳዊ ትምህርት ቤት

መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ወጣቶች ከቅዱሳት መጻሕፍት እና ከኋለኛው ቀን ነቢያት ትምህርት የሚገኘውን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የሚያጠኑበት የአራት ዓመት ፕሮግራም ነው። የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በአጠቃላይ ከ14–18 ዕድሜ ያላቸው ናቸው።

የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ፣ የወጣቶች መሪዎች እንዲሁም የቡድን እና የትምህርት ክፍል አመራሮች እያንዳንዱ ወጣት በመንፈሳዊ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ እንዲሳተፍ ያበረታታሉ።

15.1.1

አስተማሪዎች

የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት አስተማሪዎች በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ያላቸው እንዲሁም በዳግም የተመለሰው ወንጌል ምስክርነት ያላቸው የቤተክርስቲያኗ አባላት መሆን አለባቸው። የሚያስተምሯቸውን መርሆዎች የሚኖሩ እና ከወጣቶች ጋር በደንብ መስራት የሚችሉ መሆን አለባቸው። የሚቻል ሲሆን፣ ወቅታዊ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል።

የካስማ አመራር አባል ወይም የተመደበ ከፍተኛ አማካሪ የካስማ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት አስተማሪን እና የካስማ ተቆጣጣሪዎችን ይጠራል፣ ለአገልግሎት ይለያል እንዲሀም ያሰናብታል።

የአስተማሪዎችን እና ተማሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል መንፈሳዊ ትምህርት በሚካሄድበት ህንፃ ወይም ቤት ውስጥ ሁለት ጎልማሶች መገኘት አለባቸው።

15.1.2

የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት አማራጮች

መንፈሳዊ ትምህርት ቤት በጣም አጋዥ የሚሆነው ተማሪዎች በእያንዳንዱ የሳምንቱ ቀናት ከአስተማሪ ጋር ቢገናኙ ነው። ነገር ግን ይህ ከደህንነት፣ ከቦታ ርቀት እና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የሚቻል ላይሆን ይችላል።

የቤተክርስቲያን መሪዎች ከሚከተሉት የትኛውን አማራጭ እንደሚወስኑ ከመ&ኢ ተወካዮች ጋር ይመክራሉ፦

  • የትኛው አማራጭ ተማሪዎች ወንጌልን እንዲማሩ እና በመንፈሳዊ እንዲያድጉ በተሻለ ሁኔታ ይረዳል።

  • የትኛው አማራጭ የተማሪዎችን ደህንነት ይጠብቃል።

  • የትኛው አማራጭ ወላጆች ላይ አላስፈላጊ ጫና አያሳርፍም።

በእሁድ ቀን የትምህርት ክፍሎች መሰጠት አይኖርበትም።

15.1.3

ህንፃዎች፣ መሣሪያዎች እና ቁሳቁሶች

የካስማ እና የአጥቢያ መሪዎች ለመንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች የሚሆኑ የመሰብሰቢያ አዳራሾች ወይም የአባላት ቤቶች መኖራቸውን ያረጋግጣሉ።

የመ&ኢ ተወካዩ ለእያንዳንዱ ክፍል ለአስተማሪዎችና ለተማሪዎች ቁሳቁሶችን ያቀርባል። ተማሪዎች የታተመም ሆነ ዲጂታል የራሳቸውን ቅዱሳት መጻህፍት ማምጣት አለባቸው።

15.1.5

ክሬዲት እና ምረቃ

የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ያለማቋረጥ ክፍል ከተገኙ፣ ከተሳተፉ እና ከክፍል ውጪ ቅዱሳት መጻህፍትን ካጠኑ ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ መማር እና ለውጣቸውን ማጠናከር ይችላሉ። እነዚህን ነገሮች ሲያደርጉ፣ በየአመቱ የመንፈሳዊ ትምህርት ክሬዲት ያገኛሉ እንዲሁም ከመንፈሳዊ ትምህር ቤት ሊመረቁ ይችላሉ።

አንድ ተማሪ ከመንፈሳዊ ትምህርት ቤት ለመመረቅ፣ የአራት አመት ክሬዲት ማግኘትና ከአንድ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል የቤተክርስቲያን ድጋፍ ማግኘት አለበት።

15.2

ኢኒስቲትዩት

የኢኒስቲትዩት አስተማሪዎች በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ያላቸው እንዲሁም ዳግም የተመለሰው የእርሱ ወንጌል ምስክርነት ያላቸው የቤተክርስቲያን አባላት መሆን አለባቸው። ዕድሜያቸው ከ18-30 ዓመት የሆኑ ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች ሁሉ፣ ትምህርት እየተማሩ ቢሆኑም ባይሆኑም፣ በኢንስቲትዩት እንዲሳተፉ መበረታታት አለባቸው።

15.3

የቤተክርስቲያኗ ትምህርት ቤቶች እና የቤተክርስቲያኗ የትምህርት ስርዓት

ስለቤተክርስቲያኗ አንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ BYU–Pathway Worldwide [ዓለም ዓቀፍ ቢዋይዩ ፓዝ ዌይ] እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃ ለማግኘት CES.ChurchofJesusChrist.org. ተማሪዎች በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ለመማር ስለሚያስፈልገው የቤተክርስቲያን መሪዎች ድጋፍ አሞላል መረጃም እዚያ ይገኛል።

በተጨማሪም፣ የቅጥር የቤተክርስቲያን መሪዎች ማረጋገጫ መረጃ በCES Ecclesiastical Clearance Office [ሲኢኤስ የቤተክርስቲያን መሪዎች ማረጋገጫ ጽ/ቤት] በኩል ሊገኝ ይችላል፦ help.ChurchofJesusChrist.org.