“14. ያላገቡ አባላት፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።
“14. ያላገቡ አባላት፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ
14.
ያላገቡ አባላት
14.0
መግቢያ
ያላገቡ ወይም የተፋቱ ወይም የትዳር ጓደኞቻቸውን በሞት ያጡ ወንዶች እና ሴቶች በቤተክርስቲያኗ አባልነት ጉልህ ድርሻ ይይዛሉ። ሁሉም በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ተስፋ ማግኘታቸው አስፈላጊ ነው (ኤተር 12፥4ን ይመልከቱ)። የሚከተሉት ዘለዓለማዊ እውነቶች እንዲህ ያለውን ተስፋ ለማዳበር ሊረዱ ይችላሉ፦
-
ቅዱሳት መጻሕፍት እና የኋለኛው ቀን ነቢያት የወንጌል ቃል ኪዳኖችን በመጠበቅ ታማኝ የሆነ ሁሉ በዘላለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የመደረግ እድል እንደሚኖረው ያረጋግጣሉ።
-
በዘላለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የመደረግ በረከቶች ሁሉ የሚሰጡበት ትክክለኛ ጊዜ እና መንገድ አልተገለጸም። ሆኖም የተረጋገጡ ናቸው (ሞዛያ 2፥41ን ይመልከቱ)።
-
ጌታን መጠበቅ ቀጣይነት ያለው ታዛዥነትን እና ወደእርሱ የሚደረግን መንፈሳዊ እድገት ያመለክታል (ኢሳይያስ 64፥4ን ይመልከቱ)።
-
እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ህይወትን ለሁሉም ልጆቹ አቅርቧል። ለአዳኙ የይቅርታ የጸጋ ስጦታ ብቁ የሆኑ እና በትዕዛዛቱ የሚኖሩ ሁሉ የዘለዓለም ህይወት ያገኛሉ። (ሞዛያ 26፥30፤ ሞሮኒ 6፥8 ይመልከቱ።)
-
በእነዚህ ማረጋገጫዎች መተማመን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በሚኖር እምነት ላይ በጥልቅ የተመሠረተ ነው። በጸጋው ምክንያት ከሟችነት ጋር የተያያዙ ነገሮች ሁሉ ተስተካክለዋል (አልማ 7፥11–13ይመልከቱ)።
ሁሉም አባላት በአጥቢያዎቻቸው እና በካስማዎቻቸው ውስጥ ባለው የደህንነት ሥራ እንዲረዱት ጌታ ይፈልጋል (1 ቆሮንቶስ 12፥12–27 ይመልከቱ)። በመንፈስ መሪነት፣ ያላገቡ አባላት ወደ መሪነት እና የአስተማሪነት የስራ መደቦች ይጠራሉ።
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ፦
-
“ያላገቡ አባላት“ የሚለው ቃል በአሁኑ ወቅት ያላገቡትን ሁሉንም የቤተክርስቲያኗን አባላት ያመለክታል።
-
“ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች“ የሚለው ቃል ዕድሜያቸው ከ18–30 የሚሆናቸውን ያመለክታል።
-
“ያላገቡ ጎልማሶች“ የሚለው ቃል ዕድሜያቸው 31 እና ከዚያ በላይ የሚሆናቸውን ያመለክታል።
14.1
በጂኦግራፊያዊ የቤተክርስቲያኗ ክፍሎቹ ውስጥ ያሉ ያላገቡ አባላት
14.1.1
የካስማ መሪዎች
14.1.1.2
የካስማ ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች እና ያላገቡ ጎልማሶች ኮሚቴዎች
የካስማ አመራሩ የካስማ ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች ኮሚቴዎችን ያቋቁማል።
የካስማ አመራሩ የካስማ ያላገቡ ጎልማሶች ኮሚቴዎችንም ሊያቋቁም ይችላል።
ኮሚቴዎች በወዳጅነት እንዲሁም በደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ውስጥ የመሳተፍ እድሎችን በመስጠት አባላትን ለመደገፍ ይፈልጋሉ (14.2ን ይመልከቱ)።
14.1.2
የአጥቢያ መሪዎች
14.1.2.1
የኤጲስ ቆጶስ አመራር
የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ በደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ውስጥ ያላገቡ አባላትን ለማሳተፍ ወሳኝ ነው። ላላገቡ አባላት የሚሆኑ ትርጉም ያላቸው ጥሪዎችን እና የስራ ምደባዎችን ለመለየት ከአጥቢያ ምክር ቤቱ ጋር አብረው ይሰራሉ። የነጠላ ወላጆችን ፍላጎቶች ለይተው ያውቃሉ እንዲሁም ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ይጥራሉ።
-
ከኤጲስ ቆጶስ አመራር አባላት አንዱ እያንዳንዱን ያላገባ ወጣት ጎልማሳ ቢያንስ በዓመት አንዴ ይገናኘዋል።
-
የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ የካስማ ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች ኮሚቴን ሊያደራጅ ይችላል።
14.1.2.2
ላላገቡ ወጣት ጎልማሶች የተመደቡ የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር አባላት
የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንቶች እያንዳንዳቸው ከአመራር አባላቶቻቸው አንዱን ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች እንዲረዱ ሊመድቡ ይችላሉ። እነዚህ የአመራር አባላት ያላገቡ ወጣት ጎልማሶችን ጠንካራ ጎን ያውቃሉ እንዲሁም ፍላጎቶቻቸውን በማሟላት ይረዳሉ።
የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት በአጥቢያ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ስለነዚህ ጥረቶች ሪፖርት ሊያቀርቡ ይችላሉ።
14.1.2.3
ያላገቡ ወጣት ጎልማሳ መሪዎች
ብዙ ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች ባሉበት አጥቢያ ውስጥ፣ የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ አንድ ያላገባ/ች ወጣት ጎልማሳ ወንድ ወይም ሴት ያላገባ/ች ወጣት ጎልማሳ መሪዎች አድርጎ ሊጠራቸው ይችላል። ኃላፊነቶቻቸው እነዚህን ሊያካትቱ ይችላሉ፦
-
ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች በደህንነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥራ ውስጥ እንዲሳተፉ መርዳት (14.2ን ይመልከቱ)።
-
በካስማ ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች ኮሚቴ ውስጥ ማገልገል።
-
የተመሰረተ ከሆነ የአጥቢያ ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች ኮሚቴን መምራት።
-
ከሽማግሌዎች ቡድን አመራር እና ከሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራር ጋር በየወቅቱ ይገናኛል። በእነዚህ ስብሰባዎች ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች ያላቸውን ጥንካሬ እና ፍላጎታቸውን ለማሟላት እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ይወያያሉ። እንዲሁም ያላገቡ ወጣት ጎልማሶችን በማገልገል ላይ ያተኩራሉ።
14.2
በደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ስራ መሳተፍ
14.2.1
በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መኖር
14.2.1.1
የቤተሰብ የቤት ምሽት እና የወንጌል ጥናት
ለመሳተፍ የሚፈልጉ መሪዎች ወይም አባላት አንድ ወይም ከዚያ በላይ የቤት ምሽት ቡድኖችን ላላገቡ ጎልማሶች እንዲሁም ሌሎች ቡድኖችን ላላገቡ ወጣት ጎልማሶች ማደራጀት ይችላሉ።
14.2.1.3
አክቲቪቲዎች
በአጥቢያ ወይም በካስማ መሪዎች አመራር፣ ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች በተለይ ለእነሱ የሚሆኑ አክቲቪቲዎችን ሊያቅዱ እና ሊሳተፉባቸው ይችላሉ። እነዚህን ምሳሌዎች ሊያካትቱ ይችላሉ፦
-
የቤተመቅደስ ጉብኝት
-
የቤተሰብ ታሪክ ሥራ
-
ወንጌልን ማካፈል
-
የማህበረሰብ አገልግሎት
-
ሙዚቃ እና ባህላዊ ዝግጅቶች
-
ስፖርት
በካስማ መሪዎች አመራር፣ ያላገቡ ጎልማሶች ተመሳሳይ አክቲቪቲዎችን በካስማ ደረጃ ሊያቅዱ ይችላሉ።