መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
13. የሰንበት ትምህርት ቤት


“13. የሰንበት ትምህርት ቤት፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 [እ.አ.አ)]።

“13. የሰንበት ትምህርት ቤት፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ምስል
ቤተሰቦች ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነቡ

13.

የሰንበት ትምህርት ቤት

13.1

ዓላማዎች

የሰንበት ትምህርት ቤት መሪዎች፣ አስተማሪዎች እና የትምህርት ክፍሎች፦

  • “የመንግሥቱን ትምህርት“ በማስተማር በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለንን እምነት ያጠናክራሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥77)።

  • ቤትን ያማከለ እና በቤተክርስቲያን የተደገፈ የወንጌል መማር ማስተማርን ያግዛሉ።

  • አባላት በአዳኙ መንገድ እንዲያስተምሩ ይረዳሉ።

13.2

የአጥቢያ የሰንበት ትምህርት ቤት አመራር

13.2.1

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ የሰንበት ትምህርት ቤቱን በበላይነት ይቆጣጠራል። አብዛኛውን ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ በእርሱ አመራር አማካኝነት ይህን ኃላፊነት እንዲወጣ ከአማካሪዎቹ አንዱን ይመድባል።

13.2.2

የሰንበት ትምህርት ቤት ፕሬዚዳንት

13.2.2.1

የሰንበት ትምህርት ቤት ፕሬዚዳንትን መጥራት

ኤጲስ ቆጶሱ አንድን የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚ የአጥቢያ የሰንበት ትምህርት ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን እንዲያገለገግል ይጠራል እንዲሁም ለአገልግሎት ይለየዋል። አማካሪዎች የሚያስፈልጉ ከሆነ እና በዚህ ቦታ ሊያገለግሉ የሚችሉ በቂ ወንዶች ካሉ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ፕሬዚዳንቱ አንድ ወይም ሁለት አማካሪዎችን በጥቆማ ሊያቀርብ ይችላል።

13.2.2.2

ኃላፊነቶች

  • በአጥቢያ ምክር ቤት ያገለግላል።

  • በቤት እና በቤተክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መማር ማስተማርን የማሻሻል ጥረቶችን በበላይነት ይቆጣጠራል።

  • ጎልማሳ አባላትን የሰንበት ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ሆነው እንዲያገለግሉ ለኤጲስ ቆጶስ አመራር በጥቆማ ያቀርባል።

  • የሰንበት ትምህርት ቤት አስተማሪዎችን ያግዛል፣ ያበረታታል እንዲሁም ያስተምራል።

  • ከኤጲስ ቆጶሱ በሚሰጠው መመሪያ መሰረት የአስተማሪዎች ምክር ቤት ስብሰባዎችን ይመራል (Teaching in the Savior’s Way [በአዳኙ መንገድ ማስተማር]፣ 3)።

13.2.3

የሰንበት ትምህርት ቤት አስተማሪዎች

ለማስተማር ሲዘጋጁ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ቅዱሳት መጻህፍትን፣ ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች እና ኑ፤ ተከተሉኝ—ሰንበት ትምህርት ቤት ይጠቀማሉ።

13.3

የሰንበት ትምህርት ቤት የትምህርት ክፍል

የትምህርት ክፍል ስብሰባዎች የሚካሄዱት በወሩ የመጀመሪያ እና ሶስተኛ እሁዶች ላይ ነው።

በኤጲስ ቆጶሱ ፈቃድ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ፕሬዚዳንቱ ለጎልማሶች እና ለወጣቶች የትምህርት ክፍሎችን ያደራጃል።

በእያንዳንዱ የወጣቶች የትምህርት ክፍል ቢያንስ ሁለት ሃላፊነት የሚሰማቸው ጎልማሶች መገኘት አለባቸው።

ከወጣቶች ጋር የሚሰሩ ጎልማሶች ሁሉ ድጋፍ በተሰጣቸው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የህጻናት እና የወጣቶች ጥበቃ ስልጠናን ማጠናቀቅ ProtectingChildren.ChurchofJesusChrist.orgአለባቸው ( )።

13.4

በአጥቢያ ውስጥ መማር እና ማስተማርን ማሻሻል

የአጥቢያ መሪዎች በድርጅቶቻቸው ውስጥ መማር እና ማስተማርን የማሻሻል ኃላፊነት አለባቸው። የሰንበት ትምህት ቤት ፕሬዚዳንቱን እርዳታ መጠየቅ ይችላሉ።

13.5

በቤት ውስጥ መማር እና ማስተማርን ማሻሻል

ወላጆች ወንጌልን ለልጆቻቸው የማስተማር ኃላፊነት አለባቸው። የሰንበት ትምህት ቤት ፕሬዚዳንቱን እንደአስተማሪ መሻሻል ስለሚችሉበት መንገድ እርዳታ መጠየቅ ይችላሉ።

አትም