መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
18. የክህነት ስርዓቶችን ማከናወን እና በረከቶችን መስጠት


“18. የክህነት ስርዓቶችን ማከናወን እና በረከቶችን መስጠት፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“18. የክህነት ስርዓቶችን ማከናወን እና በረከቶችን መስጠት፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ቤተሰብ በቤተመቅደስ አቅራቢያ ሲጓዝ

18.

የክህነት ስርዓቶችን ማከናወን እና በረከቶችን መስጠት

18.0

መግቢያ

ሥርዓቶች እና በረከቶች በክህነት ስልጣን እና በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሚከናወኑ ቅዱስ ተግባራት ናቸው። የክህነት ሥርዓቶች እና በረከቶች የእግዚአብሔርን ሃይል የመጠቀም እድል ይሰጣሉ ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥20ይመልከቱ)።

ሥርዓቶች እና በረከቶች በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ መመሪያ መሰረት መከናወን ይኖርባቸዋል። መሪዎች እነዚህ በተገቢው ፈቃድ (አስፈላጊ ከሆነ)፣ በተገቢ የክህነት ስልጣን፣ በትክክለኛው መንገድ እና ብቁ በሆኑ ተሳታፊዎች መከናወናቸውን ያረጋግጣሉ( 18.3ይመልከቱ)።

18.1

የደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥርዓቶች

ክህነት ለደህንነት እና በዘላለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑትን የወንጌል ሥርዓቶች የማከናወንን ስልጣን ያካትታል። ሰዎች እነዚህን ሥርዓቶች ሲቀበሉ ከአግዚአብሔር ጋር የተቀደሱ ቃል ኪዳኖችን ይገባሉ። የደህንነት እና በዘላለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግ ሥርዓቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።

  • ጥምቀት

  • ማረጋገጫ መቀበል እና የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታን መቀበል

  • የመልከ ጼዴቅ ክህነትን መስጠት እና በአንድ ክፍል መሾም (ለወንዶች)

  • የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ

  • የቤተመቅደስ እትመት

በቃል ኪዳኑ ውስጥ የተወለደ ልጅ 8 ዓመት ሳይሞላው ከሞተ ምንም አይነት ሥርዓቶች አያስፈልጉም ወይም አይከናወኑም። ልጁ በቃል ኪዳኑ ውስጥ ካልተወለደ እሱ ወይም እሷ የሚያስፈልገው/ጋት ብቸኛው ሥርዓት ከወላጆች ጋር መታተም ነው። በአዳኙ የኃጢያት ክፍያ ምክንያት፣ ዕድሜያቸው 8 ዓመት ሳይደርሱ የሚሞቱ ልጆች ሁሉ “በሰማይ ሰለስቲያል መንግስት ውስጥ [ድነዋል]” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 137፥10፤ በተጨማሪም ሞሮኒ 8፥8–12ይመልከቱ)።

18.3

በሥርዓቶች ወይም በረከቶች መሳተፍ

ሥርዓትን ወይም በረከትን የሚፈፅሙ ወይም በዚያ ውስጥ የሚሳተፉ ተገቢው የክህነት ስልጣን ሊኖራቸውና ብቁ ሊሆኑ ይገባል። በአጠቃላይ፣ የብቃት መለኪያው የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያን ከመያዝ ጋር የተያያዘ ነው። የሆነ ሆኖ፣ በመንፈስ ምሪት እና በዚህ ምዕራፍ ውስጥ በተሰጡት መመሪያዎች መሰረት፣ ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች በተገቢ የክህነት ክፍል የተሾሙ አባቶች እና ባሎች ሙሉ ለሙሉ ለቤተመቅደስ ብቁ ባይሆኑም አንዳንድ ሥርዓቶችን እና በረከቶችን እንዲያከናውኑ ወይም በእነዚያ ውስጥ እንዲሳተፉ ሊፈቅዱ ይችላሉ። ያልተፈቱ ከባድ ኃጢአቶች የሰራ የክህነት ተሸካሚ መሳተፍ የለበትም።

አንዳንድ ሥርዓቶችን እና በረከቶችን ለማከናወን ወይም ለመቀበል ተገቢ የክህነት ቁልፎችን ከያዘ የበላይ መሪ ፈቃድ ያስፈልጋል ( 3.4.1ይመልከቱ)። እንዳስፈላጊነቱ፣ እሱ ፈቃድ በሰጠው አማካሪ ሊሰጥ ይችላል። የሚከተሉትን ቻርቶች ይመልከቱ። የካስማ ፕሬዚዳንቶችን የሚያመለክቱት የሚስዮን ፕሬዚዳንቶችንም ያመለክታሉ። ኤጲስ ቆጶሳትን የሚያመለክቱት የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቶችንም ያመለከታሉ።

የደህንነትን እና በዘለአማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግን ሥርአቶች ለማከናወን ወይም ለመቀበል ፍቃድ መስጠት የሚያስችሉ ቁልፎችን የያዙ መሪዎች የትኞች ናቸው?

ሥርዓቶች

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ሥርዓቶች

ጥምቀት

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ኤጲስ ቆጶስ (8 ዓመት ለሆናቸው ልጆች እና እድሜያቸው 9 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ በአዕምሯዊ ውስንነት ምክንያት ጥምቀታቸው ለተራዘመ በመዝገብ ውስጥ ላሉ አባላት)

የሚስዮን ፕሬዚዳንት (ለተለወጡ)

ሥርዓቶች

ማረጋገጫ እና የመንፈስ ቅዱስ ሥጦታ

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ኤጲስ ቆጶስ (8 ዓመት ለሆናቸው ልጆች እና እድሜያቸው 9 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ በአዕምሯዊ ውስንነት ምክንያት ጥምቀታቸው ለተራዘመ በመዝገብ ውስጥ ላሉ አባላት)

የሚስዮን ፕሬዚዳንት (ለተለወጡ)

ሥርዓቶች

የመልከ ጼዴቅ ክህነትን መስጠት እና በአንድ ክፍል መሾም (ለወንዶች)።

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

የካስማ ፕሬዚዳንት

ሥርዓቶች

የቤተመቅደስ የመንፈስ ስጦታ

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ኤጲስ ቆጶስ እና የካስማ ፕሬዚዳንት

ሥርዓቶች

የቤተመቅደስ እትመት

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ኤጲስ ቆጶስ እና የካስማ ፕሬዚዳንት

ሌሎች ሥርዓቶችን እና በረከቶችን ለማከናወን ወይም ለመቀበል ፍቃድ መስጠት የሚያስችሉ ቁልፎችን የያዙ መሪዎች የትኞች ናቸው?

ሥርዓት ወይም በረከት

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ሥርዓት ወይም በረከት

ልጆችን መሰየም እና በረከት መስጠት

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ኤጲስ ቆጶስ

ሥርዓት ወይም በረከት

ቅዱስ ቁርባን

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ኤጲስ ቆጶስ

ሥርዓት ወይም በረከት

የአሮናዊን ክህነትን መስጠት እና በአንድ ክፍል መሾም (ለወጣት ወንዶች እና ለጎልማሳ ወንዶች)

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ኤጲስ ቆጶስ

ሥርዓት ወይም በረከት

በጥሪዎች እንዲያገለግሉ አባላትን መለየት

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

30፥8ይመልከቱ

ሥርዓት ወይም በረከት

ዘይትን መቀደስ

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ፈቃድ የማያስፈልገው

ሥርዓት ወይም በረከት

ለታመመው ሰው በረከት መስጠት

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ፈቃድ የማያስፈልገው

ሥርዓት ወይም በረከት

የአባቶች በረከቶችን ጨምሮ የመፅናናት እና የምክር በረከቶች

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ፈቃድ የማያስፈልገው

ሥርዓት ወይም በረከት

ቤቶችን መቀደስ

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ፈቃድ የማያስፈልገው

ሥርዓት ወይም በረከት

የመቃብር ቦታን መቀደስ

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ሥነ ሥርዓቱን በበላይነት የሚመራው የክህነት መሪ

ሥርዓት ወይም በረከት

የፓትሪያርክ በረከቶች

ቁልፎችን የያዘው ማን ነው

ኤጲስ ቆጶስ

18.4

ለአካለ መጠን ላልደረሱ ልጆች የሚደረጉ ስርዓቶች

አንድ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ በረከት ሊቀበል፣ ሊጠመቅ፣ ማረጋገጫ ሊቀበል፣ በክህነት ክፍል ሊሾም ወይንም በአንድ ጥሪ ለአገልግሎት ሊለይ የሚችለው (1) በውሳኔው ላይ ለመሳተፍ ህጋዊ መብት ባላቸው ወላጆች ወይንም (2) በህጋዊ አሳዳጊዎች ስምምነት ነው።

18.6

ልጆችን መሰየም እና መባረክ

ልጆች በተለምዶ ወላጆቻቸው በሚኖሩበት አጥቢያ በጾም እና ምስክርነት ስብሰባ ወቅት ይሰየማሉ እንዲሁም ይባረካሉ።

18.6.1

በረከቱን ማን ይሰጣል

ህፃናትን የመሰየም እና የመባረክ ሥርዓት በመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚ አማካኝነት ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥70ውስጥ ባለው መመሪያ መሰረት ይከናወናል።

ልጁ ስም እና በረከት እንዲቀበል የሚፈልግ ሰው ወይም ቤተሰብ ሥርዓቱን ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር ያስተባብራል። እርሱ በአጥቢያ ውስጥ ልጆችን የመሰየም እና የመባረክ የክህነት ቁልፎችን ይይዛል።

አንድ ኤጲስ ቆጶስ፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ የሆነን አባት ሙሉ ለሙሉ ለቤተመቅደስ ብቁ ባይሆንም ልጁን እንዲሰይም እና እንዲባርክ ሊፈቅድለት ይችላል ( 18.3ይመልከቱ)። ኤጲስ ቆጶሳት፣ አባቶች የራሳቸውን ልጆች ለመባረክ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ያበረታታሉ።

18.6.2

መመሪያዎች

በኤጲስ ቆጶሱ በሚሰጠው አመራር መሰረት፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች ልጅን ለመሰየም እና ለመባረክ ክብ ሰርተው ይቆማሉ። እጆቻቸውን ህፃኑ ሥር ያደርጋሉ ወይም እጆቻቸውን በዕድሜ ከፍ በሚለው ልጅ ራስ ላይ ቀለል አድርገው ይጭናሉ። ከዚያም በክቡ ውስጥ የተሰበሰቡትን ወክሎ በረከቶቹን በድምፅ የሚናገረው፦

  1. በጸሎት ጊዜ እንደሚደረገው የሰማይ አባትን ይጠራል።

  2. በረከቱ በመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን እንደሚከናወን ይገልጻል።

  3. ለህፃኑ ስም ይሰጣል።

  4. ልጁን ይጠራል።

  5. መንፈስ ቅዱስ እንደመራው ለልጁ በረከት ይሰጣል።

  6. በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይዘጋል።

1:41

Naming and Blessing of Children

18.6.3

Child Record Form and Blessing Certificate [የልጅ መዝገብ ቅፅ እና የበረከት የምስክር ወረቀት]

አንድ ልጅ በረከት ከመቀበሉ በፊት ፀሃፊው Child Record Form [የልጅ መዝገብ ቅፅ] ለማዘጋጀት Leader and Clerk Resources (LCR)ይጠቀማል። ከበረከቱ በኋላ በዚያው ስርዓት ውስጥ የአባልነት መዝገብ ይፈጥራል እንዲሁም Blessing Certificate [የበረከት የምስክር ወረቀት]ያዘጋጃል። ይህ የምስክር ወረቀት በኤጲስ ቆጶሱ ይፈረማል ከዚያም ለህጻኑ ወላጆች ወይም ህጋዊ አሳዳጊዎች ይሰጣል።

በአባልነት መዝገቡ እና በምስክር ወረቀቱ ላይ ያለው ስም ከልደት የምስክር ወረቀቱ፣ ከመዘጋጃ ቤት ልደት መዝገቡ ወይም ከወቅቱ ህጋዊ ስም ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት።

18.7

ጥምቀት

አንድ ሰው የቤተክርስቲያኗ አባል ለመሆን እና መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ስልጣን ባለው ሰው በውሃ ውስጥ በመጥለቅ መጠመቅ ያስፈልገዋል። በዘለአለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ ለመደረግ የሚሹ ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ መከተል አለባቸው።

18.7.1

አንድ ሰው እንዲጠመቅ እና ማረጋገጫ እንዲቀበል ፈቃድ ማግኘት

18.7.1.1

የመዝገብ አባላት የሆኑ ልጆች

ኤጲስ ቆጶሱ በአጥቢያው የመዝገብ አባል የሆኑ 8 ዓመት የሆናቸውን ልጆች የማጥመቅ የክህነት ቁልፎችን አሉት። እነዚህ ልጆች ልክ በ8ኛ ዓመት የልደት ቀናቸው ወይም ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆዩ መጠመቅ እና ማረጋገጫ መቀበል አለባቸው ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 68፥27ይመልከቱ)። እነዚህ ቀድሞውኑ በቤተክርስቲያኗ የአባልነት መዛግብት ውስጥ የሚገኙ ልጆች ናቸው( 33.6.2ይመልከቱ)። ዕድሜያቸው 8 ዓመት ሲደርስ ኤጲስ ቆጶሱ ወንጌልን ለመቀበልና ለመጠመቅ እንዲሁም ማረጋገጫ ለማግኘት ሁሉም እድል እንዳላቸው ያረጋግጣል።

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የተመደበው አማካሪ በአባልነት መዝገብ ውስጥ የሚገኙ ልጆችን ለጥምቀት እና ማረጋገጫ ለመስጠት ቃለ መጠይቅ ያደርጋቸዋል። መመሪያዎች በ 31.2.3.1 ውስጥ ይገኛሉ።

Baptism and Confirmation Record [የጥምቀት እና የማረጋገጫ መዝገብ] አሞላል መረጃ ለማግኘት 18.8.3ይመልከቱ።

18.7.1.2

የተለወጡ

የሚስዮን ፕሬዚዳንቱ በሚስዮኑ ውስጥ የተለወጡትን የማጥመቅ የክህነት ቁልፎች አሉት። በዚህ ምክንያት የሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያን ለጥምቀት እና ማረጋገጫ ለመስጠት የተለወጡትን ቃለ መጠይቅ ያደርጉላቸዋል።

18.7.2

የጥምቀት ስርዓቶች

የጥምቀት ሥነ ሥርዓት ቀላል፣ አጭር እና በመንፈሳዊ የሚያንፅ መሆን አለበት። የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፦

  1. የመግቢያ ሙዚቃ

  2. ሥነ ሥርዓቱን የሚመራው ወንድም የሚያቀርበው አጭር የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት

  3. የመክፈቻ መዝሙር እና ጸሎት

  4. እንደ ጥምቀት እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ባሉ የወንጌል ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አንድ ወይም ሁለት አጫጭር መልዕክቶች

  5. የመዝሙር ምርጫ

  6. ጥምቀት

  7. በጥምቀቱ የተካፈሉት ልብስ እስከሚቀይሩ ድረስ የሚደረግ የአክብሮት ጊዜ (በዚህ ጊዜ መዝሙሮችን ወይም የመጀመሪያ ክፍል መዝሙሮችን ማጫወት ወይም መዘመር ይቻላል)

  8. በመዝገብ ውስጥ የሚገኙ 8 ዓመት የሆናቸው ልጆች ማረጋገጫ ይቀበላሉ፤ ለተለወጡ ማረጋገጫ የሚሰጠው በኤጲስ ቆጶሱ ከተወሰነ ነው ( 18.8ይመልከቱ)

  9. አስፈላጊ ከሆነ አዲስ የተለወጡ ምስክርነታቸውን ያካፍላሉ

  10. የመዝጊያ መዝሙር እና ጸሎት

  11. የማጠቃለያ ሙዚቃ

በመዝገብ ውስጥ ያለ ልጅ ለመጠመቅ ሲዘጋጅ፣ ከኤጲስ ቆጶስ አመራር አባላት አንዱ እና የመጀመሪያ ክፍል አመራር የጥምቀት አገልግሎትን ለማቀድ እና መርሃ ግብር ለማውጣት ከቤተሰቡ ጋር ይመክራሉ። ከኤጲስ ቆጶስ አመራር አባላት አንዱ ሥነ ሥርዓቱን ይመራል። በዚያ ወር ውስጥ ከአንድ በላይ ልጅ የሚጠመቅ ከሆነ የጥምቀት ሥነ ሥርዓታቸውን በአንድ ቀን ሊያደርጉ ይችላሉ።

ብዛት ያላቸው በመዝገብ ውስጥ ያሉ ልጆች ባሉበት ካስማ ውስጥ ከበርካታ ክፍሎች የመጡ ልጆች አንድ የጥምቀት ሥነ ሥርዓት ሊያከናውኑ ይችላሉ። ከካስማ አመራር አባላት አንዱ ወይም አንድ የተመደበ ከፍተኛ አማካሪ ሥነ ሥርዓቱን ይመራል።

አንድ አባት ክህነትን ተቀብሎ ጥምቀቱን ራሱ እስኪያከናውን ድረስ የቤተሰብ አባል ጥምቀት ሊዘገይ አይገባም።

በኤጲስ ቆጶስ አመራሩ መሪነት፣ የአጥቢያው የሚስዮን መሪ (የተጠራ ከሆነ) ወይም በአጥቢያው የሚስዮናዊ ስራን የሚመራ የሽማግሌዎች ቡድን አመራር አባል የጥምቀት ሥነ ሥርዓቱን ያቅዳል እንዲሁም ይመራል። ከሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያን ጋር ይቀናጃሉ።

18.7.3

ሥርዓቱን ማን ያከናውናል

የጥምቀት ሥርዓት በካህን ወይም በመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚ ይከናወናል። የጥምቀት ሥነ ሥርዓትን የሚያከናውነው ሰው ከኤጲስ ቆጶሱ (ወይም ጥምቀቱን የሚያከናውነው ሚስዮናዊ ከሆነ ከሚስዮን ፕሬዚዳንቱ) ፈቃድ ማግኘት አለበት።

አንድ ኤጲስ ቆጶስ፣ ካህን ወይንም የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ የሆነ አባት ሙሉ ለሙሉ ለቤተመቅደስ ብቁ ባይሆንም ልጁን እንዲያጠምቅ ሊፈቅድለት ይችላል( 18.3ይመልከቱ)። ኤጲስ ቆጶሳት፣ አባቶች ልጆቻቸውን ለማጥመቅ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ያበረታታሉ።

18.7.4

ሥርዓቱ የት ይከናውናል

ጥምቀት በመጠመቂያ ገንዳ (ካለ) ውስጥ መከናወን አለበት። የመጠመቂያ ገንዳ ከሌለ፣ አስተማማኝ የሆነን የውሃ አካል መጠቀም ይቻላል።

ለደህንነት ሲባል፣ ገንዳው በሚሞላበት ጊዜ አንድ ኃላፊነት የሚሰማው ጎልማሳ ሰው መገኘት አለበት፣ እንዲሁም የገንዳው ውሃ እስኪፈስ፣ እስኪጸዳ እና እስኪቆለፍ ድረስ መቆየት አለበት። እያንዳንዱ የጥምቀት ሥነ ሥርዓት ከተከናወነ በኋላ ወዲያውኑ ውሃው ከገንዳው መፍሰስ አለበት። በአገልግሎት ላይ በማይሆንበት ጊዜ የገንዳው በሮች መቆለፍ ይኖርባቸዋል።

18.7.5

አለባበስ

ጥምቀትን የሚያከናውኑ እና የሚጠመቁ ሰዎች እርጥብ በሚሆንበት ጊዜ ወደ ውስጥ የማያሳይ ነጭ ልብስ ይለብሳሉ። የቤተመቅደስ ቡራኬን የተቀበለ ሰው ጥምቀቱን በሚያከናውንበት ጊዜ የቤተመቅደስ አልባሳትን ከዚህ ልብስ ስር ይለብሳል። የአካባቢ ክፍሎች በበጀት ገንዘብ የጥምቀት አልባሳትን ይገዛሉ እንዲሁም የሚጠቀሙባቸውን ሰዎች አያስከፍሉም።

18.7.6

ምስክሮች

በበላይነት ከሚመራው ፈቃድ ያገኙ ሁለት ምስክሮች እያንዳንዱ ጥምቀት በትክክል ስለመፈጸሙ ለማረጋገጥ ይመለከታሉ። ልጆችን እና ወጣቶችን ጨምሮ የተጠመቁ የቤተክርስቲያኗ አባላት እንደምስክር ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ።

ቃላቶቹ በ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥73ውስጥ እንደተቀመጡት በትክክል ካልተባሉ ጥምቀቱ መደገም ይኖርበታል። የግለሰቡ የአካል ክፍል፣ ፀጉር ወይም ልብስ ሙሉ በሙሉ ካልጠለቀም መድገም ይኖርበታል።

18.7.7

መመሪያዎች

የጥምቀት ሥርዓት ለማከናወን አንድ ካህን ወይም የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚ፦

  1. ከሚጠመቀው ሰው ጋር ውሃው ውስጥ ይቆማል።

  2. በግራ እጁ የግለሰቡን የቀኝ እጅ አንጓ ይይዛል(ለአመቺነት እና ለደህንነት ሲባል)። ተጠማቂው/ዋ በቀኝ እጁ/እጇ የክህነት ተሸካሚውን የግራ እጅ አንጓ ይይዛል/ትይዛለች።

  3. እርሱም የቀኝ እጁን በትከሻ ልክ ወደጎን ዘርግቶ ክርኑ ላይ ቀጥ አድርጎ ወደ ላይ በማጠፍ ያነሳል።

  4. የግለሰቡን ሙሉ ስም ይጠራል ከዚያም እንዲህ ይላል፣ “በኢየሱስ ክርስቶስ በተሰጠኝ ስልጣን መሰረት በአብ፤ በወልድ፤ እናም በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠምቅሃለሁ (አጠምቅሻለሁ)። አሜን” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥73)።

  5. ግለሰቡ/ቧ አፍንጫውን/ዋን በቀኝ እጁ/ጇ እንዲይዝ/ድትይዝ (ለአመቺነት) ያደርጋል፤ ከዚያም ቀኝ እጁን በግለሰቡ/ቧ ጀርባ የላይኛው ክፍል በማድረግ ልብሶቹን/ቿን ጨምሮ ግለሰቡን/ቧን ሙሉ በሙሉ ያጠልቀዋል/ቃታል።

  6. ግለሰቡ ከውሃው እንዲወጣ ይረዳዋል።

3:16

Baptism of a New Member

18.8

መረጋገጫ መቀበል እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ

አንድ ግለሰብ ከተጠመቀ/ች በኋላ፣ እሱ ወይም እሷ የቤተክርስቲያኗ አባል በመሆን ማረጋገጫ ያገኛል/ታገኛለች እንዲሁም እጅን በመጫን መንፈስ ቅዱስን ይቀበላል/ትቀበላለች ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥41የሐዋሪያት ስራ 19፥1–6ይመልከቱ)። እነዚህ ሁለቱ ሥርዓቶች ከተጠናቀቁ እና በትክክል ከተመዘገቡ በኋላ ግለሰቡ/ቧ የቤተክርስቲያኗ አባል ይሆናል/ትሆናለች ( ዮሐንስ 3፥5ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 33፥113 ኔፊ 27፥20ይመልከቱ)።

ኤጲስ ቆጶሱ የማረጋገጫ አሰጣጥ አፈጻጸምን በበላይነት ይመራል። የስምንት ዓመት ልጀች በተለምዶ በተጠመቁ ቀን ማረጋገጫ ይሰጣቸዋል። የተለወጡ ግለሰቦች በተለምዶ ማረጋገጫ የሚቀበሉት በሚኖሩበት አጥቢያ ውስጥ በሚደረግ በማንኛውም የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ ሲሆን ከተጠመቁ በኋላ ባለው እሁድ ቢሆን ይመረጣል።

የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባሉ አዳዲስ አባላትን ሲያስተዋውቅ በ29.2.1.1 ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተላል።

18.8.1

ሥርዓቱን ማን ያከናውናል

በክቡ ውስጥ የተሰበሰቡትን ወክሎ በረከቶቹን በድምፅ መናገር የሚችለው ለቤተመቅደስ ብቁ የሆነ የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚ የሆነ ብቻ ነው። ሆኖም አንድ ኤጲስ ቆጶስ፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ የሆነ አባት ሙሉ ለሙሉ ለቤተመቅደስ ብቁ ባይሆንም ልጁ ማረጋገጫ ሲቀበል/ስትቀበል በክቡ ወስጥ እንዲቆም ሊፈቅድለት ይችላል ( 18.3ይመልከቱ)።

በዚህ ሥርዓት ቢያንስ አንድ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል ይሳተፋል። የተለወጠውን ያስተማሩት ሚስዮናውያን ሽማግሌዎች ከሆኑ፣ ኤጲስ ቆጶሱ እንዲሳተፉ ይጋብዛቸዋል።

18.8.2

መመሪያዎች

በኤጲስ ቆጶስ አመራር መመሪያ መሰረት፣ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች ማረጋገጫ በመስጠት ላይ ሊሳተፉ ይችላሉ። እጆቻቸውን በግለሰቡ ራስ ላይ ቀለል አድርገው ይጭናሉ። ከዚያም በክቡ ውስጥ የተሰበሰቡትን ወክሎ በረከቶቹን በድምፅ የሚናገረው፦

  1. ግለሰቡን በሙሉ ስሙ ወይም በሙሉ ስሟ ይጠራዋል/ታል።

  2. ሥርዓቱ በመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን እንደሚከናወን ይገልጻል።

  3. ግለሰቡን/ቧን የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል አድርጎ ማረጋገጫ ይሰጠዋል/ይሰጣታል።

  4. “የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ተቀበል/ይ” ሳይሆን “መንፈስ ቅዱስን ተቀበል/ይ” ይላል።

  5. መንፈስ ቅዱስ እንደመራው በረከቶችን ይሰጣል።

  6. በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይዘጋል።

1:54

Confirming a Recently Baptized Member

18.8.3

የጥምቀት እና የማረጋገጫ መዝገብ እና የምስክር ወረቀት

የመዝገብ አባል የሆነ አንድ ልጅ ለጥምቀት ቃለ መጠይቅ ከመደረጉ በፊት ፀሃፊው Baptism and Confirmation Form [የጥምቀት እና የማረጋገጫ ቅፅ] ለማዘጋጀት LCR[ኤልሲአር]ይጠቀማል። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የተመደበው አማካሪ ቃለ መጠይቁን ያደርጋል እንዲሁም ቅጹ ላይ ይፈርማል። ጥምቀት እና ማረጋገጫው ከተከናወነ በኋላ ጸሃፊው የልጁን የአባልነት መዝገብ ለማዘመን በ LCR[ኤልሲአር]ውስጥ የሚገኘውን ይህንን ቅፅ ይጠቀማል።

አንድ የሙሉ ጊዜ ሚስዮናዊ አንድን የተለወጠ ለጥምቀት ቃለመጠይቅ ሲያደርግ የArea Book Planner (ABP) መተግበሪያን በመጠቀም የጥምቀት እና የማረጋገጫ መዝገብን ይሞላል። ከጥምቀት እና ከማረጋገጫው በኋላ ሚስዮናውያኑ መረጃውን በABP ውስጥ ይመዘግቡና በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ለአጥቢያው ጸሃፊ ይልካሉ። የአጥቢያው ጸሃፊ መረጃውን በLCR [ኤልሲአር] ውስጥ ይገመግምና የአባልነት መዝገቡን ይፈጥራል።

የአባልነት መዝገቡ ከተፈጠረ በኋላ ጸሃፊው የጥምቀት እና የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያዘጋጃል። ይህ የምስክር ወረቀት በኤጲስ ቆጶሱ ይፈረማል ከዚያም ለግለሰቡ ይሰጣል።

በአባልነት መዝገቡ እና በምስክር ወረቀቱ ላይ ያለው ስም ከልደት የምስክር ወረቀቱ፣ ከመዘጋጃ ቤት ልደት መዝገቡ ወይም ከወቅቱ ህጋዊ ስም ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት።

18.9

ቅዱስ ቁርባን

የቤተክርስቲያኗ አባላት እግዚአብሔርን ለማምለክ እና ቅዱስ ቀርባኑን ለመካፈል በሰንበት ቀን ይሰበሰባሉ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥7559፥9ሞሮኒ 6፥5–6ይመልከቱ)። ይህ ሥርአት በሚከናወንበት ወቅት፣ የአዳኙን የስጋ እና የደም መስዋዕት ለማስታወስ እና ቅዱስ ቃል ኪዳናቸውን ለማደስ ከዳቦው እና ከውሃው ይካፈላሉ( ማቴዎስ 26፥26–28የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ማርቆስ 14፥20–25ሉቃስ 22፥15–203 ኔፊ 18ሞሮኒ 6፥6ይመልከቱ)።

18.9.1

ቅዱስ ቁርባንን ለማስተዳደር ፈቃድ ማግኘት

ኤጲስ ቆጶሱ በአጥቢያ ውስጥ ቅዱስ ቁርባንን የማስተዳደር የክህነት ቁልፎች አሉት። ቅዱስ ቁርባኑን በማዘጋጀት፣ በመባረክ፣ በማሳለፍ የሚሳተፉ ሁሉ ከእርሱ ወይም እርሱ ከመደበው ሰው ፈቃድ ማግኘት አለባቸው።

18.9.2

ሥርዓቱን ማን ያከናውናል

  • አስተማሪዎች፣ ካህናት፣ እና የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚዎች ቅዱስ ቁርባኑን ሊያዘጋጁ ይችላሉ።

  • ካህናት እና የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚዎች ቅዱስ ቁርባኑን ሊባርኩ ይችላሉ።

  • ዲያቆናት፣ አስተማሪዎች፣ ካህናት፣ እና የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚዎች ቅዱስ ቁርባኑን ሊያሳልፉ ይችላሉ።

18.9.3

የቅዱስ ቁርባን መመሪያዎች

ቅዱስ ቁርባን ባለው ቅዱስ ተፈጥሮ ምክንያት፣ የክህነት መሪዎች ሥርዓት ያለው እና አክብሮት የተሞላበት እንዲሆን በጥንቃቄ መዘጋጀት አለባቸው።

ቅዱስ ቁርባንን የሚያከናውኑ ሰዎች ጌታን እንደሚወክሉ ተገንዝበውበክብር ሊያደርጉት ይገባል።

ቅዱስ ቁርባንን ማሳለፍ እንደሁኔታው እንጂ ከመጠን በላይ መደበኛ መሆን የለበትም።

ምንም እንኳን ቅዱስ ቁርባን የሚዘጋጀው ለቤተክርስቲያኗ አባላት ቢሆንም፣ ሌሎች እንዳይካፈሉ ለመከላከል ምንም መደረግ የለበትም።

18.9.4

መመሪያዎች

  1. ቅዱስ ቁርባኑን የሚያዘጋጁ፣ የሚባርኩ ወይም የሚያሳልፉ በመጀመሪያ እጃቸውን በሳሙና ወይም በሌላ ማፅጃ መታጠብ አለባቸው።

  2. አስተማሪዎች፣ ካህናት ወይም የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች ከስብሰባው በፊት የዳቦ ማቅረቢያ ሳህኖች ካልተቆረሱ ዳቦዎች ጋር፣ የውሃ ማቅረቢያ ሳህኖች ከንጹህ የውሃ ስኒዎች ጋር እንዲሁም ንጹህ የጠረጴዛ ጨርቆች መዘጋጀታቸውን ያረጋግጣሉ።

  3. የአጥቢያው አባላት የቅዱስ ቁርባን መዝሙርን ሲዘምሩ፣ ቅዱስ ቁርባኑን የሚባርኩት በአክብሮት ይነሳሉ ከዚያም የዳቦ ሳህኖቹን የሚሸፍነውን ጨርቅ ይገልጡና ዳቦውን ለመጉረስ በሚመች መጠን ይቆርሳሉ።

  4. ከመዝሙሩ በኋላ ዳቦውን የሚባርከው ሰው ተንበርክኮ የዳቦውን የቅዱስ ቁርባን ጸሎት ያቀርባል ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥77ይመልከቱ)።

  5. ኤጲስ ቆጶሱ የቅዱስ ቁርባን ጸሎቶች በግልፅ፣ በትክክል እና በክብር መባሉን ያረጋግጣል። አንድ ሰው ቃላቱን ቢሳሳት እና ራሱን ቢያርም ተጨማሪ እርማት አያስፈልግም። ግለሰቡ ስህተቱን ካላረመ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ጸሎቱን እንደዲደግም በትህትና ይጠይቀዋል።

  6. ከጸሎቱ በኋላ የክህነት ተሸካሚዎች ዳቦውን በአክብሮት ለአባላት ያሳልፋሉ። የበላይ መሪው መጀመሪያ ይቀበላል፤ ከዚያ በኋላ የተቀመጠ ቅደም ተከተል የለም። ሳህኑ ለአባላት ከተሰጠ በኋላ፣ አንዳቸው ለሌላው ሊያሳልፉ ይችላሉ።

  7. የሚቻል ሲሆንን አባላት በቀኝ እጃቸው ይካፈላሉ።

  8. ዳቦው ለሁሉም አባላት ከተላለፈ በኋላ፣ ቅዱስ ቁርባኑን የሚያሳልፉት ሰዎች ሳህኖቹን ወደ ቅዱስ ቁርባን ጠረጴዛው ይመልሳሉ። ቅዱስ ቁርባኑን የሚባርኩት ሰዎች የዳቦ ሳህኖቹን በጨርቅ ይሸፍኑና የውሃ ሳህኖቹን ይገልጣሉ።

  9. ውሃውን የሚባርከው ሰው ተንበርክኮ የውሀውን የቅዱስ ቁርባን ጸሎት ያቀርባል ( (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥79ይመልከቱ)። ወይን የሚለውን ቃል ውሃ በሚል ይተካዋል።

  10. ከጸሎቱ በኋላ የክህነት ተሸካሚዎች ውሃውን በአክብሮት ለአባላት ያሳልፋሉ። የበላይ መሪው መጀመሪያ ይቀበላል፤ ከዚያ በኋላ የተቀመጠ ቅደም ተከተል የለም።

  11. ውሃው ለሁሉም አባላት ከተላለፈ በኋላ፣ ቅዱስ ቁርባኑን የሚያሳልፉት ሰዎች ትሪዎቹን ወደ ቅዱስ ቁርባን ጠረጴዛው ይመልሳሉ። ቅዱስ ቁርባኑን የባረኩት ሰዎች ሳህኖቹን በጨርቅ ይሸፍናሉ፣ እንዲሁም ቅዱስ ቁርባኑን የባረኩት እና በአክብሮት ያሳለፉት ወደመቀመጫቸው ይሄዳሉ።

  12. ከስብሰባው በኋላ ቅዱስ ቁርባኑን ያዘጋጁት ያጸዳሉ፣ የጠረጴዛ ጨርቁን ያጥፋሉ እንዲሁም ጥቅም ላይ ያልዋለውን ዳቦ ያስወግዳሉ።

3:32

Blessing the Sacrament

18.10

ክህነትን መስጠት እና በክፍል መሾም

ሁለት የክህነት ምድቦች አሉ፦ አሮናዊ እና መልከ ጼዴቅ (3.3ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥16 ይመልከቱ)። ለአንድ ሰው ክህነት ሲሰጠው፣ በዚያ የክህነት ክፍል ውስጥም ይሾማል። ሁለቱም የክህነት ስልጣኖች ከተሰጡ በኋላ አንድ ሰው የሚያስፈልገው በዚያ ክህነት ውስጥ ላሉት ለሌሎች ክፍሎች መሾም ብቻ ነው።

18.10.1

የመልከ ጼዴቅ ክህነት

የካስማ ፕሬዘደንቱ የመልከ ጼዴቅ ክህነትን ለመስጠት እንዲሁም በሽማግሌ እና በሊቀ ካህን ክፍሎች ለመሾም የሚያስችል የክህነት ቁልፎች አሉት። ሆኖም ኤጲስ ቆጶሱ አብዛኛውን ጊዜ ለእነዚህ ሹመቶች በጥቆማ ያቀርባል።

18.10.1.1

ሽማግሌዎች

ብቁ የሆኑ ወንድሞች 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ሲሆናቸው የመልከ ጼዴቅ ክህነትን ሊቀበሉና ሽማግሌ ሆነው ሊሾሙ ይችላሉ። በግለሰብ ሁኔታዎች ላይ በመመስረት፣ ኤጲስ ቆጶሱ አንድ ወጣት 18ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ካከበረ በኋላ ወዲያውኑ ሽማግሌ ሆኖ እንዲሾም በጥቆማ ይቅረብ ወይስ ከክህነት ቡድኑ ጋር ረዘም ላለ ጊዜ ይቆይ የሚለውን ይወስናል።

ይህንን ውሳኔ ለማድረግ፣ ኤጲስ ቆጶሱ በመጀመሪያ ከወጣቱ እና ከወላጆቹ ወይም ከአሳዳጊዎቹ ጋር ይመክራል። ብቁ የሆኑ ወንዶች 19 ዓመት ሲሞላቸው ወይም ኮሌጅ ለመማር፣ የሙሉ ጊዜ ሚስዮን ለማገልገል፣ በውትድርና ለማገልገል ወይም የሙሉ ጊዜ ሥራ ለመቀጠር ከቤት ከመውጣታቸው በፊት በሽማግሌ ክፍል መሾም አለባቸው።

ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ በቅርብ የተጠመቁ ወንዶች የሚከተሉትን ካሟሉ ሽማግሌ ሆነው ይሾማሉ፦

  • አሮናዊ ክህነትን ከተቀበሉ እና በክህነት ካገለገሉ።

  • በቂ የወንጌል ግንዛቤ ካዳበሩ።

  • ብቁ መሆናቸውን ካሳዩ።

የቤተክርስቲያን አባል በሆነበት የጊዜ ርዝመት ላይ መመካት አያስፈልግም።

18.10.1.2

ሊቀ ካህናት

ወንዶች ሊቀ ካህናት ሆነው የሚሾሙት ለካስማ አመራር፣ ለከፍተኛ ምክር ቤት ወይም ለኤጲስ ቆጶስ አመራር አገልግሎት ሲጠሩ ነው።

18.10.1.3

ቃለ መጠይቅ ማድረግ እና ድጋፍ ማግኘት

በካስማ አመራሩ ፈቃድ፣ ኤጲስ ቆጶሱ በMelchizedek Priesthood Ordination Record [በመልከ ጼዴቅ የክህነት ሹመት መዝገብ] ላይ በተሰጠው መመሪያ መሰረት ይህንን ወንድም ቃለ መጠይቅ ያደርገዋል። ከዚያም በተጨማሪም ከካስማ አመራር አባላት አንዱ ቃለ መጠይቅ ያደርገዋል። በሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ፈቃድ፣ የአውራጃ ፕሬዚዳንቱ አንድን ወንድም ሽማግሌ ሆኖ እንዲሾም ቃለ መጠይቅ ሊያደርግ ይችላል( 6.3ይመልከቱ)።

18.10.2

የአሮናዊ ክህነት

ኤጲስ ቆጶሱ የአሮናዊ ክህነትን ለመስጠት እንዲሁም በዲያቆን፣ በአስተማሪ እና በካህን ክፍሎች ለመሾም የሚያስችል የክህነት ቁልፎች አሉት። ብቁ የሆኑ ወንድሞች በተለምዶ በእነዚህ ክፍሎች የሚሾሙት በሚከተሉት ዕድሜዎች ላይ ሲሆን፣ ከዚያ ቀደም ብሎ አይሆንም፦

  • ዲያቆን 12 ዓመት በሚሞላቸው ዓመት መጀመሪያ ላይ

  • አስተማሪ 14 ዓመት በሚሞላቸው ዓመት መጀመሪያ ላይ

  • ካህን 16 ዓመት በሚሞላቸው ዓመት መጀመሪያ ላይ

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የተመደበው አማካሪ፣ ዲያቆናት ወይም አስተማሪዎች ሆነው የሚሾሙ በመንፈሳዊ ዝግጁ መሆናቸውን ለመወሰን ቃለ መጠይቅ ያደርግላቸዋል። ኤጲስ ቆጶሱ ካህን ሆነው የሚሾሙትን ቃለ መጠይቅ ያደርግላቸዋል።

ወጣት ለክህነት ሹመት ቃለ መጠይቅ ከመደረጉ በፊት የኤጲስ ቆጶስ አባል ከወጣቱ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ፈቃድ ያገኛል። ወላጆቹ የተፋቱ ከሆነ ህጋዊ የማሳደግ መብት ካለው/ላቸው ወላጅ/ጆች ፈቃድ ያገኛል።

18.10.3

አንድ ሰው ከመሾሙ በፊት ድጋፍ እንዲያገኝ ማቅረብ

አንድ ወንድም ቃለ መጠይቅ ከተደረገለት እና በክህነት ክፍል ለመሾም ብቁ ሆኖ ከተገኘ በኋላ፣ ለድጋፍ ይቀርባል( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥65፣ 67ይመልከቱ)። ሽማግሌዎች ወይም ሊቀ ካህናት ሆነው የሚሾሙ ወንድሞች በካስማ ጉባኤ አጠቃላይ ክፍለ ጊዜ ላይ በአንድ የካስማ አመራር አባል ይቀርባሉ(ለአውራጃ ፕሬዚዳንቶች መመሪያዎች 6.3 ይመልከቱ)። ዲያቆናት፣ አስተማሪዎች ወይም ካህናት ሆነው የሚሾሙ ወንድሞች በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ላይ በኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል ይቀርባሉ።

ድጋፍ ማሰጠቱን የሚመራው ሰው ያንን ወንድም እንዲቆም ይጠይቀዋል። የአሮናዊ ወይም የመልከ ጼዴቅ (ከተፈለገ) ክህነትን ለመስጠት እና ያንን ወንድም በክህነት ክፍል ለመሾም የቀረበውን ሀሳብ ያስታውቃል። ከዚያም የቀረበውን ሀሳብ አባላቱ እንዲደግፉት ይጋብዛል። ለምሳሌ፣ አንድን ወንድም ሽማግሌ በመሆን እንዲሾም ለማቅረብ፣ እነዚህን የመሳሰሉ ቃላትን መጠቀም ይችላል፦

[ስም] የመልከ ጼዴቅ ክህነትን እንዲቀበል እና ሽማግሌ በመሆን እንዲሾም ሃሳብ እናቀርባለን። ይህንን የሚደግፉ እጃቸውን በማውጣት ማሳየት ይችላሉ። [ለአፍታ ማቆም፡፡] የሚቃወሙ ካሉ በተመሳሳይ ማሳየት ይችላሉ። [ለአፍታ ማቆም፡፡]”

በጥሩ አቋም ላይ ያለ/ች አባል ሹመቱን ከተቃወመ/ች፣ የበላይ መሪው ወይም ሌላ የተመደበ የክህነት መሪ ከስብሰባው በኋላ በግል ከእርሱ ወይም ከእርሷ ጋር ይገናኛል። መሪው አባሉ ለምን እንደተቃወመ/ች ለመረዳት ይፈልጋል። ግለሰቡን በክህነት ክፍል ከመሾም ሊያግደው የሚችል ሥነምግባር እንዳለበት አባሉ የሚያውቅ/የምታውቅ ስለመሆኑ ግንዛቤ ይወስዳል።

በአንዳንድ ሁኔታዎች አንድን ወንድም በካስማ ጉባኤ ላይ ከማቅረብ በፊት ሽማግሌ ወይም ሊቀ ካህን በመሆን መሾም ሊያስፈልግ ይችላል። ይህ ሲሆን በአጥቢያው የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ድጋፍ ለማግኘት ይቀርባል። ከዚያም በቀጣዩ የካስማ ጉባኤ ሹመቱን ለማጸደቅ (ከላይ የተገለጸውን ድጋፍ የማሰጠት ሂደት በመከተል) ይቀርባል።

18.10.4

ሥርዓቱን ማን ያከናውናል

የካስማ ፕሬዚዳንቱ ወይም አንድ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ በእርሱ አመራር አንድን ሰው በሽማግሌ ክፍል መሾም ይችላል። በሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ፈቃድ፣ የአውራጃ ፕሬዚዳንቱ ወይም አንድ ሰው በእርሱ ፈቃድ ሥርዓቱን ሊያካሂድ ይችላል( 6.3ይመልከቱ)። ክብ ሰርተው መቆም የሚችሉት የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚዎች ብቻ ናቸው ።

የካስማ ፕሬዚዳንቱ ወይም አንድ ሊቀ ካህን በእርሱ አመራር አንድን ሰው በሊቀ ካህን ክፍል መሾም ይችላል። ክብ ሰርተው መቆም የሚችሉት ሊቀ ካህናት ብቻ ናቸው።

አንድን ሰው በመልከ ጼዴቅ የክህነት ክፍል የሚሾም ግለሰብ ለቤተመቅደስ ብቁ መሆን አለበት። የካስማ ፕሬዚዳንቱ ወይም እሱ የወከለው አንድ ሰው መገኘት አለበት።

አንድ ካህን ወይም የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚ አንድን ወንድም በዲያቆን፣ በአስተማሪ ወይም በካህን ክፍል ሊሾም ይችላል። ከኤጲስ ቆጰሱ ፈቃድ ማግኘት አለበት። ኤጲስ ቆጰሱ ወይም እሱ የወከለው አንድ ሰው መገኘት አለበት።

በአሮናዊ ክህነት ሹመት ለመሳተፍ አንድ ሰው ካህን ወይም የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ መሆን አለበት።

አንድ ኤጲስ ቆጶስ፣ ካህን ወይንም የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ የሆነ አባት ሙሉ ለሙሉ ለቤተመቅደስ ብቁ ባይሆንም ልጁን በዲያቆን፣ በአስተማሪ ወይም በካህን ክፍል አንዲሾም ሊፈቅድለት ይችላል( 18.3ይመልከቱ)። አባቶች ልጆቻቸውን ለመሾም ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ኤጲስ ቆጶሳት ያበረታታሉ።

18.10.5

መመሪያዎች

ለአንድ ሰው ክህነትን ለመስጠት እና በክህነት ክፍል ለመሾም አንድ ወይም ከአንድ በላይ የተፈቀደላቸው የክህነት ተሸካሚዎች እጃቸውን ላላ አድርገው በግለሰቡ እራስ ላይ ይጭናሉ። ከዚያም በድምፅ የሚናገረው፦

  1. ግለሰቡን በሙሉ ስሙ ይጠራዋል።

  2. ሥርዓቱን (አሮናዊም ሆነ የመልከ ጼዴቅ ክህነት) ለማከናወን በግለሰብ ደረጃ የያዘውን ስልጣን ይገልጻል።

  3. ከዚህ በፊት የተሰጠ ካልሆነ አሮናዊ ወይም የመልከ ጼዴቅ ክህነትን ይሰጣል።

  4. ግለሰቡን በአሮናዊ ወይም በመልከ ጼዴቅ የክህነት ክፍል ይሾማል እንዲሁም የዚያን ክፍል መብቶች፣ ሃይል እና ሥልጣን ይሰጠዋል።

  5. መንፈስ ቅዱስ እንደመራው በረከቶችን ይሰጣል።

  6. በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይዘጋል።

ተገቢው ክህነት ተሰጥቶት የነበረን አንድን ግለሰብ በክህነት ክፍል ለመሾም ሥርዓቱን የሚያከናውነው ሰው ደረጃ 3ን ይተዋል።

1:58

Ordination to the Priesthood

18.10.6

የሹመት መዝገብ እና የምስክር ወረቀት

አንድ ወንድም በአሮናዊ ክህነት ለመሾም ቃለ መጠይቅ ከመደረጉ በፊት ፀሃፊው Aaronic Priesthood Ordination Record [የአሮናዊ የጥምቀት እና የማረጋገጫ ቅፅ] ለማዘጋጀት LCR[ኤልሲአር]ይጠቀማል። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የተመደበው አማካሪ ቃለ መጠይቁን ያደርጋል እንዲሁም ሁሉም የብቁነት ሁኔታዎች ከተሟሉ ቅጹ ላይ ይፈርማል።

ከሹመቱ በኋላ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የተመደበው አማካሪ ቅጹን ያጠናቅቃል ከዚያም ለጸሃፊው ይሰጣል። ሹመቱን በ LCR[ኤልሲአር] ውስጥ ይሞላል ከዚያም የሹመት የምስክር ወረቀት ያዘጋጀል።

የግለሰቡ ወቅታዊ ህጋዊ ስም በሹመት መዝገቡ እና በምስክር ወረቀቱ ላይ መስፈር አለበት።

18.11

አባላትን በጥሪዎች እንዲያገለግሉ መለየት

ለአብዛኛዎቹ የቤተክርስቲያኗ ምድቦች ለማገልገል የተጠሩ እና የተደገፉ አባላት ለዚህ ምድብ መለየት ይገባቸውል (ዮሃንስ 15፥16ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥11፤ በተጨማሪም በዚህ መመሪያ መፅሃፍ ውስጥ 3.4.3.1 ይመልከቱ)። ለአገልግሎት በሚለይበት ወቅት፣ ግለሰቡ (1) በጥሪው የመስራት ስልጣን እና (2) መንፈስ ቅዱስ እንደመራው በረከቶች ይሰጡታል።

የካስማ ፕሬዚዳንቶች፣ ኤጲስ ቆጶሳት እና የቡድን ፕሬዚዳንቶች ለአገልግሎት በሚለዩበት ጊዜ የአመራር ቁልፍን ይቀበላሉ ( 3.4.1.1ይመልከቱ)። ሆኖም ቁልፎች የሚለው ቃል በአመራር ውስጥ ያሉ አማካሪዎች ጨምሮ አባላት በሌሎች ጥሪዎች እንዲያገለግሉ በሚለዩበት ጊዜ ጥቅም ላይ መዋል የለበትም።

18.11.1

ለአገልግሎት መለየቱን ማን ያከናውናል

ለአገልግሎት መለየት በመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚ ይከናወናል። ተገቢው የክህነት ቁልፎች ካሉት መሪ ፈቃድ ማግኘት ይኖርበታል። ለአገልግሎት ለመለየት ፈቃድ የተሰጣቸው በ30.8 ውስጥ ተጠቁመዋል። አንድ ሰው ሊቀ ካህን መሆንን ለሚጠይቅ ክፍል ሲለይ አንድ ሽማግሌ በክቡ ውስጥ የተሰበሰቡትን ወክሎ በረከቶቹን በድምፅ መናገር ወይም በክቡ ውስጥ መቆም አይኖርበትም።

በበላይ መሪው መመሪያ መሰረት፣ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚዎች ለአገልግሎት በመለየት ላይ ሊሳተፉ ይችላሉ። ፕሬዚዳንቶች ለአገልግሎት የሚለዩት ከአማካሪዎቻቸው አስቀድመው ነው።

አንድ የበላይ መሪ፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ የሆነ ባል ወይም አባት ሙሉ ለሙሉ ለቤተመቅደስ ብቁ ባይሆንም ባለቤቱ ወይም ልጆቹ ለአገልግሎት ሲለዩ በክቡ ወስጥ እንዲቆም ሊፈቅድለት ይችላል።( 18.3ይመልከቱ)።

18.11.2

መመሪያዎች

አንድ ወይም ከአንድ በላይ የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸከሚዎች እጆቻቸውን በግለሰቡ ራስ ላይ ላላ አድርገው ይጭናሉ። ከዚያም በክቡ ውስጥ የተሰበሰቡትን ወክሎ በረከቶቹን በድምፅ የሚናገረው፦

  1. ግለሰቡን በሙሉ ስሙ ወይም በሙሉ ስሟ ይጠራዋል/ታል።

  2. በመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን እንደሚያከናውን ይገልጻል።

  3. ግለሰቡን ለካስማ፣ ለአጥቢየ፣ ለቡድን ወይም ለትምህርት ክፍል ጥሪዎች ለአገልግሎት ይለየዋል።

  4. ግለሰቡ ሊቀበል የሚገባው ከሆነ ቁልፎቹን ይሰጠዋል።

  5. መንፈስ ቅዱስ እንደመራው በረከቶችን ይሰጣል።

  6. በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይዘጋል።

18.12

ዘይትን መቀደስ

የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚዎች የታመሙትን ወይም የተጎሳቆሉትን ለመቀባት የወይራ ዘይትን ጥቅም ላይ ከማዋላቸው በፊት መቀደስ አለባቸው( ያዕቆብ 5፥14ይመልከቱ)። ሌላ ዘይት መጠቀም አይቻልም።

አባላት የተቀደሰ ዘይትን አይጠጡም ወይም በታመመ የሰውነት ክፍሎች ላይ አያደርጉም።

18.12.1

ሥርዓቱን ማን ያከናውናል

አንድ ወይም አንድ በላይ የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚዎች ዘይቱን ሊቀድሱ ይችላሉ። ከክህነት መሪ ፈቃድ መጠየቅ አያስፈልጋቸውም።

18.12.2

መመሪያዎች

ዘይቱን ለመበረክ የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚ፦

  1. ክዳኑ የተከፈተ የዘይት ዕቃ ይይዛል።

  2. በጸሎት ጊዜ እንደሚደረገው የሰማይ አባትን ይጠራል።

  3. በመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን እንደሚያከናውን ይገልጻል።

  4. ዘይቱን (ዕቃውን ሳይሆን) ይቀድሳል እንዲሁም የታመሙትን እና የተጎሳቆሉትን ለመቀባት እና ለመባረክ ይሆን ዘንድ ለአገልግሎት ይለየዋል።

  5. በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይዘጋል።

1:12

Consecrating Oil

18.13

ለታመመው ሰው በረከት መስጠት

“እጅን በመጫን” ለታመሙት በረከት መስጠት ሁለት ክፍሎች አሉት፦ በዘይት መቀባት እና የተቀባውን በበረከት ማተም። የተቀደሰ ዘይት ከሌለ ዘይት ሳይደረግ በመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን በረከቱ ሊሰጥ ይችላል።

18.13.1

በረከቱን ማን ይሰጣል

ብቁ የሆኑ የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚዎች ብቻ ለታመሙት እና ለተጎሳቆሉት መስጠት ይችላሉ። ከክህነት መሪ ፈቃድ መጠየቅ አያስፈልጋቸውም። ከተቻለ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ያለው አባት ለታመሙ የቤተሰቡ አባላት ሊሰጥ ይችላል።

በተለምዶ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚዎች ለታመሙ ሰዎች ይሰጣሉ። ሆኖም መቀባቱንም ማተሙንም አንድ ሰው ሊየከናውን ይችላል።

18.13.2

መመሪያዎች

ዘይትን መቀባት በአንድ የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚ ይከናወናል። እርሱም፦

  1. የተቀደሰ ዘይት ጠብታ በግለሰቡ ራስ ላይ ያደርጋል።

  2. እጆቹን ላላ አድርጎ በግለሰቡ ራስ ላይ ይጭንና ግለሰቡን/ቧን በሙሉ ስሙ/ስሟ ይጠራዋል/ታል።

  3. በመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን እንደሚያከናውን ይገልጻል።

  4. የታመሙትን እና የተጎሳቆሉትን ለመቀባት እና ለመባረክ የተቀደሰ ዘይትን እንደሚቀባ ይገልጻል።

  5. በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይዘጋል።

የተቀባውን ዘይት ለማተም አንድ ወይም ከአንድ በላይ የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸከሚዎች እጆቻቸውን በግለሰቡ ራስ ላይ ላላ አድርገው ይጭናሉ። ከዚያም የተቀባውን ዘይት የሚያትመው፦

  1. ግለሰቡን በሙሉ ስሙ ወይም በሙሉ ስሟ ይጠራዋል/ታል።

  2. የተቀባውን ዘይት የሚያትመው በመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን እንደሆነ ይገልጻል።

  3. መንፈስ ቅዱስ እንደመራው በረከቶችን ይሰጣል።

  4. በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይዘጋል።

2:3

Administering to the Sick

18.14

የአባቶችት በረከቶችን ጨምሮ የመፅናናት እና የምክር በረከቶች

18.14.1

በረከቱን ማን ይሰጣል

የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸከሚዎች ለቤተሰብ የመፅናናት እና የምክር በረከቶችን ለቤተሰብ ሊሰጡ ይችላሉ።

የመልከ ጼዴቅ ክህነት ያለው አባት ለልጆቹ የአባቶች በረከቶችን ሊሰጥ ይችላል። ወላጆች፣ ልጆቻቸው በችግር ጊዜ የአባቶች በረከቶችን እንዲፈልጉ ያበረታታሉ። የአባቶች በረከቶች ለግል አገልግሎት ሊመዘገቡ ይችላሉ።

አንድ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸከሚ የመፅናናት እና የምክር በረከቶችን ወይም የአባቶች በረከቶችን ለመስጠት ከክህነት መሪ ፈቃድ መጠየቅ አያስፈልገውም።

18.14.2

መመሪያዎች

የመፅናናት እና የምክር በረከቶችን ወይም የአባቶች በረከቶችን ለመስጠት አንድ ወይም ከአንድ በላይ የተፈቀደላቸው የክህነት ተሸካሚዎች እጃቸውን ላላ አድርገው በግለሰቡ ራስ ላይ ይጭናሉ። ከዚያም በድምፅ የሚናገረው፦

  1. ግለሰቡን በሙሉ ስሙ ወይም በሙሉ ስሟ ይጠራዋል/ታል።

  2. በረከቱ በመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን እንደሚከናወን ይገልጻል።

  3. መንፈስ ቅዱስ እንደመራው በረከቶችን፣ መፅናናትን እና ምክርን ይሰጣል።

  4. በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይዘጋል።

18.15

ቤቶችን መቀደስ

የቤተክርስቲያን አባላት ቤቶቻቸውን በመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን ሊያቀድሱ ይችላሉ።

18.15.2

መመሪያዎች

አንድን ቤት ለመቀደስ የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚ፦

  1. በጸሎት ጊዜ እንደሚደረገው የሰማይ አባትን ይጠራል።

  2. በመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን እንደሚያከናውን ይገልጻል።

  3. ቤትን መንፈስ ቅዱስ የሚያድርበት የተቀደሰ ቦታ እንዲሆን ይቀድሳል እንዲሁም ሌሎች ቃላትን መንፈስ እንደመራው ይሰጣል።

  4. በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይዘጋል።

18.16

የመቃብር ቦታን መቀደስ

18.16.1

የመቃብር ቦታን ማን ይቀድሳል

መቃብርን የሚቀድስ ሰው የመልከ ጼዴቅ ክህነት ሊኖረው ይገባል እንዲሁም አገልግሎቱን ከሚመራው የክህነት መሪ ፈቃድ ማግኘት አለበት።

18.16.2

መመሪያዎች

መቃብርን ለመቀደስ የመልከ ጼዴቅ የክህነት ተሸካሚ፦

  1. በጸሎት ጊዜ እንደሚደረገው የሰማይ አባትን ይጠራል።

  2. በመልከ ጼዴቅ የክህነት ስልጣን እንደሚያከናውን ይገልጻል።

  3. የቀብር ቦታውን ለሟቹ አካል ማረፊያ አድርጎ ይመድበዋል እንዲሁም ይቀድሰዋል።

  4. እስከሙታን ትንሳኤ ድረስ (ተገቢ ሲሆን) ቦታው የተቀደሰ እንዲሁም የተጠበቀ እንዲሆን ይጸልያል።

  5. ሰማያዊ አባት፣ ቤተሰቡን እንዲያፅናና ይጠይቃል እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ እንደመራው መንፈሳዊ ሃሳቦችን ይገልጻል።

  6. በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይዘጋል።

የቤተክርስቲያኗ አባል አስከሬን የሚቃጠል ከሆነ፣ የበላይ መሪው የተቃጠለው አስከሬን አመድ የተቀመጠበትን ቦታ ለመቀደስ ወይም ላለመቀደስ በራሱ ፍርድ ይሰጣል።

1:58

Dedication of Graves

18.17

የፓትሪያርክ በረከቶች

እያንዳንዱ ብቁ የሆነ የተጠመቀ አባል ከሰማይ አባት የሚመጣውን የተነሳሳ መመሪያ የሚሰጠውን የፓትርያርክ በረከት የማግኘት መብት አለው ( ዘፍጥረት 48፥14–16፤ 492 ኔፊ 4፥3–11ይመልከቱ)።

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የተመደበ አማካሪ የፓትርያርክ በረከት ለመቀበል የሚፈልጉትን አባላት ቃለ መጠይቅ ያደርጋቸዋል። አባሉ ብቁ ከሆነ ቃለ መጠይቅ የሚያደርገው Patriarchal Blessing Recommend [የፓትርያርክ በረከት መታወቂያ ያዘጋጃል። በ Patriarchal Blessing System በኩል ወደ ChurchofJesusChrist.org.ይልከዋል።

የፓትርያርክ በረከት መታወቂያ ሰጪው ግለሰብ አባሉ የበረከቱን አስፈላጊነት እና ቅዱስ ተፈጥሮ ለመረዳት በደንብ የበሰለ መሆኑን ያረጋግጣል።

18.17.1

የፓትርያርክ በረከትን መቀበል

መታወቂያ ከተቀበለ በኋላ፣ አባሉ የፓትርያርክ በረከትን መቀበል ይችል ዘንድ ቀጠሮ ለመያዝ ከፓትርያርኩ ጋር ግንኙነት ያደርጋል። በቀጠሮው ቀን አባሉ ወደ ፓትርያርኩ የሚሄደው በጸሎት መንፈስና በእሁድ አለባበስ መሆን አለበት።

እያንዳንዱ የፓትርያርክ በረከት ቅዱስ፣ ሚስጥራዊ እና የግል ነው። ስለዚህ ሊገኙ ከሚችሉ ውስን የቤተሰብ አባላት በስተቀር የሚሰጠው በግል ነው።

የፓትርያርክ በረከት የሚቀበል ሰው ቃላቱን በጥንቃቄ መያዝ፣ ማሰላሰል እና በዚህ ህይወት እንዲሁም በዘለአለማዊ ህይወት እንደሚሰጡ ቃል የተገቡትን በረከቶች ለመቀበል ብቁ ሆኖ መኖር አለበት።

የቤተክርስቲያኗ አባላት በረከቶችን ማወዳደር እንዲሁም ቅርብ ከሆኑ የቤተሰብ አባላት በስተቀር ለሌሎች ማካፈል የለባቸውም። የፓትርያርክ በረከቶች በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ወይም በሌሎች ህዝባዊ ስብሰባዎች ላይ መነበብ የለባቸውም።