መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
33. መዛግብት እና ሪፖርቶች


“33. መዛግብት እና ሪፖርቶች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“33. መዛግብት እና ሪፖርቶች፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ምስል
ሰዎች ኮምፒተር እየተመለከቱ

33.

መዛግብት እና ሪፖርቶች

33.0

መግቢያ

መዝገብ አያያዝ በጌታ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁልጊዜ አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ፦

አዳም “የመታሰቢያ መፅሃፍ” ይፅፍ ነበር (ሙሴ 6፥5)።

ሞሮኒ በክርስቶስ ቤተክርስቲያን የተጠመቁት ሰዎች ስም የተመዘገበው “እንዲታወሱ እና በእግዚአብሔር መልካም ቃል እንዲመግቡ ነው” ሲል አስተምሯል (ሞሮኒ 6፥4)።

“በጌታ ፊት እውነትን ይመዘግብ ዘንድ” በእያንዳንዱ አጥቢያ መዝጋቢ መጠራት እንዳለበት ጆሴፍ ስሚዝ አስተምሯል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥2)።

33.1

የቤተክርስቲያኗ መዛግብት አጠቃላይ እይታ

የቤተክርስቲያኗ መዛግብት የተቀደሱ ናቸው። በውስጣቸው የያዟቸው መረጃዎች ጥንቃቄን የሚጠይቁ ናቸው ስለዚህ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል። የቤተክርስቲያኗ የመዝገብ ሥርዓቶች በጥሪዎች ላይ በመመሥረት የአባልነት መረጃ የማግኘት ፈቃድን ይሰጣሉ።

መዛግብት መሪዎችን በሚከተሉት ሊረዱ ይችላሉ፦

  • ማን ልዩ እንክብካቤ ሊያስፈልገው እንደሚችል ይለያሉ።

  • አንድ ግለሰብ የትኞቹን የደህንነት ሥርዓቶች እንደተቀበለ ወይም ሊያስፈልገው እንደሚችል ይለያሉ።

  • አባላት ያሉበትን ይጠቁማል።

የሚከተሉት የመዛግብት አይነቶች በቤተክርስቲያኗ ክፍሎች ይቀመጣሉ፦

  • የአባላት ተሳትፎ ሪፖርት (33.5ን ይመልከቱ)

  • የአባልነት መዛግብት (33.6ን ይመልከቱ)

  • ታሪካዊ መዛግብት (33.7ን ይመልከቱ)

  • የገንዘብ መዛግብት (ምዕራፍ 34ን ይመልከቱ።

33.2

ለጸሃፊዎች የሚሆን አጠቃላይ መመሪያ

የታደሰ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል።

ጸሃፊዎች የቤተክርስቲያኗን ገንዘቦች ለመጠበቅ እንዲሁም የቤተክርስቲያኗ መዛግብት ትክክለኛ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ወቅታዊ ፖሊሲዎችን በጥንቃቄ ይከተላሉ። ጸሃፊዎች ማናቸውንም ታማኝነት የሚጎድላቸው ነገሮች ወዲያውኑ ለክህነት መሪዎች ያሳውቃሉ። ታማኝነት የሚጎድላቸው ነገሮችን በመፍታት ረገድ ችግሮች ከተከሰቱ፣ ጸኃፊዎች በቤተክርስቲያኗ ዋና መሥሪያ ቤት የሚገኘውን Confidential Records Office [የሚስጥራዊ መዝገቦች ቢሮ] ማነጋገር አለባቸው።

የሥልክ ቁጥር፦1-801-240-2053 ወይም 1-800-453-3860፣ የውስጥ መሥመር ቁጥር 2-2053

ነጻ የሥልክ መሥመር (GSD phone)፦ 855-537-4357

ኢሜል፦ ConfidentialRecords@ChurchofJesusChrist.org

ጸሐፊዎች በአገልግሎት የሚቆዩበት የጊዜ ገደብ ኃላፊነታቸውን ለመማር እና ስራቸው ወጥነት እንዲኖረው በቂ መሆን አለበት። የካስማ አመራር አባላት ወይም የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባላት ስላልሆኑ፣ የካስማ አመራሩ ወይም የኤጲስ ቆጶስ አመራሩ በአዲስ መልክ ሲደራጅ መሰናበት አይኖርባቸውም።

33.4

የአጥቢያ መዛግብት እና ሪፖርቶች

33.4.1

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ኤጲስ ቆጶሱ የአጥቢያውን የመዝገብ አያያዝ በበላይነት ይመራል።

33.4.2

የአጥቢያ ጸሃፊ

እያንዳንዱ አጥቢያ ብቃት ያለው የሚሰራ የአጥቢያ ጸኃፊ ሊኖረው ይገባል። የሚጠቆመው በኤጲስ ቆጶስ አመራር ሲሆን የሚጠራው እና ለአገልግሎት የሚለየው በካስማ አመራር ወይም በተመደበ ከፍተኛ አማካሪ ነው። የመልከ ጼዴቅ ክህነት ያለው እና የታደሰ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ያለው መሆን ይኖርበታል። የአጥቢያ ምክር ቤት አባል ነው። 29.2 ውስጥ በተመለከተው መሰረት በአጥቢያ ስብሰባዎች ይሳተፋል።

የአጥቢያ ጸኃፊ በኤጲስ ቆጶስ አመራር እና በካስማ ጸኃፊዎች ስልጠና ይሰጠዋል። ረዳት የአጥቢያ ጸኃፊዎች እንዲረዱ ሊጠሩ ይችላሉ።

33.4.2.1

የመዘገብ አያያዝ ኃላፊነቶች

የአጥቢያ ጸኃፊ ወይም የተመደበ ረዳት ጸኃፊ የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉበት፦

  • በአጥቢያ የአመራር ስብሰባዎች ላይ የተሰጡ የስራ ምድቦችን እና ውሳኔዎችን መዝግቦ ይይዛል።

  • መዛግብት እና ሪፖርቶች ትክክለኛ እና ወቅታዊ መሆናቸውን ያረጋግጣል።

የአጥቢያ ጸኃፊ ስለቤተክርስተያኗ የመዝገብ አያያዝ መሳሪያዎች አሰራር የሚያውቅ መሆን አለበት (33.0ን ይመልከቱ)። እነዚህን መሳሪያዎች በመጠቀም መሪዎች የሚከተሉትን እንዲለዩ ይረዳል፦

  • የአባላትን እና የድርጅቶችን ፍላጎቶች።

  • ገንዘብን ጨምሮ ያሉ ሃብቶችን።

አባላት በአባልነት መረጃቸው ላይ የሚገኝን ማንኛውንም ስህተት እንዲያሳውቁ የአጥቢያ ፀኃፊዎች ያበረታታሉ።

ሌሎች የመዝገብ አያያዝ ኃላፊነቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

  • ሥርዓቶች በትክክል እና በአፋጣኝ መመዝገባቸውን ማረጋገጥ።

  • ለአጥቢያ ጉባኤ የOfficers Sustained form [የመሪዎች ድጋፍ ቅፅ]ን ማዘጋጀት።

  • ለአጥቢያ የአባልነት ምክር ቤቶች መረጃ መያዝ።

  • የገንዘብ መዛግብትን መያዝ (34.2.2ን ይመልከቱ)።

33.5

የአባል ተሳትፎ ሪፖርት

የአባል ተሳትፎ ሪፖርቶች መሪዎች በአባላት እድገትና ፍላጎት ላይ እንዲያተኩሩ ያግዛቸዋል።

33.5.1

የሪፖርቶች ዓይነቶች

33.5.1.1

የተሳትፎ ሪፖርቶች

የቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች እና የእሁድ የክህነት እንዲሁም የድርጅት ሥብሰባዎች ተሳትፎLCR [ኤልሲአር] ወይም Member Tools [በአባል መሳሪያዎች] በመጠቀም በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ይመዘገባል።

የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ። የቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች ተሳትፎ በየሳምንቱ በአጥቢያ ጸኃፊ ወይም በአጥቢያ ረዳት ጸኃፊ ይመዘገባል። ቁጥሩ ጎብኚዎችን ጨምሮ በአካል ወይም በቀጥታ ስርጭት በስብሰባ ላይ የተሳተፉ ሰዎች ቁጥር ነው።

የእሁድ የሽማግሌዎች ቡድን እና የድርጅት ሥብሰባዎች። ተሳትፎ በየሳምንቱ በሽማግሌዎች ቡድን እና በድርጅት ጸኃፊዎች እና አማካሪዎች ይመዘገባል። ወጣት መሪዎችም ተሳትፎን በመመዝገብ ሊያግዙ ይችላሉ። ቁጥሩ ጎብኚዎችን ጨምሮ በአካል ወይም በቀጥታ ስርጭት በስብሰባ ላይ የተሳተፉ ቁጥር ነው። በአጥቢያው ውሰጥ በመጀመሪያ ክፍል ወይም እንደወጣት መሪዎች የሚያገለግሉ አባላት በተሳታፊነት እንደተገኙ ይመዘገባሉ።

የአጥቢያ ጸሐፊው ማንኛውንም ድርጅት ወክሎ ተሳትፎን መመዝገብ ይችላል።

33.5.1.2

የአገልግሎት ቃለ መጠይቅ ሪፖርቶች

21.3ን ይመልከቱ።

33.5.1.3

የሩብ ዓመት ሪፖርት

በሪፖርቱ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ቁጥር የተለየ ፍላጎት ያለውን ትክክለኛ ግለሰብ ይወክላል (ሔለማን 15፥13ን ይመልከቱ)።

የሩብ ዓመት ሪፖርቱ መሪዎች ለአገልግሎት ስለሚያደርጉት ጥረቶች መነሳሳትን ሲሹ ለመሪዎች ግንዛቤዎችን ሊሰጡ የሚችሉ ጠቃሚ መረጃዎችን ይይዛል።

የካስማ እና የአጥቢያ መሪዎች የግለሰቦችን እድገት ለመገምገም የሩብ ዓመት ሪፖርት በየወቅቱ ይመለከታሉ።

እያንዳንዱ አጥቢያ የሩብ ዓመት ሪፖርትን በመሙላት ለቤተክርስቲያኗ ዋና መሥሪያ ቤት ይልካል። ጸሐፊው ሪፖርቱን ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር ይገመግማል እንዲሁም በእያንዳንዱን ሩብ ዓመት ማብቂያ ላይ ከወሩ 15ኛው ቀን በፊት ያቀርባል።

33.5.2

የአባልነት ዝርዝር

የቤተክርስቲያኗ መዝገብ አያያዝ መሳሪያዎች መሪዎች የአባልነት ዝርዝሮችን እንዲያገኙ ያስችሏቸዋል። እነዚህ ዝርዝሮች መሪዎች የሚከተሉትን እንዲለዩ ሊረዱ ይችላሉ፦

  • የትኞቹ አባላት ብቁ የሆኑባቸውን ሥርዓቶች ገና እንዳልተቀበሉ።

  • የትኞቹ ወጣት ወንዶች እና ወጣት ሴቶች በሚስዮን ለማገልገል ብቁ እንደሆኑ።

  • የትኞቹ ወጣቶች የታደሰ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ እንደሌላቸው።

  • የትኞቹ ወጣቶች ከኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ መያዝ እንዳለባቸው።

የሽማግሌዎች ቡድን እና የድርጅት መሪዎች የቡድናቸው ወይም የድርጅታቸው አባል የሆኑትን ሰዎች ዝርዝሮች ሊኖራቸው ይገባል።

33.6

የአባልነት መዛግብት

የአባልነት መዛግብት የአባላትን ስም፣ የአድራሻ መረጃ፣ የሥርዓት ዝርዝሮችን እና ሌሎች ወሳኝ መረጃዎችን ያካትታሉ።

የአባልነት መዛግብት አባሉ በሚኖርበት አጥቢያ መቀመጥ አለባቸው። ውስን መሆን ያለባቸው ልዩ ሁኔታዎች የሚመለከታቸውን ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች ፈቃድ ይፈልጋሉ። ልዩ ሁኔታን ለመጠየቅ ይችል ዘንድ ጥያቄውን ለቀዳሚ አመራር ፅ/ቤት ለማቅረብ የካስማ ፕሬዚዳንቱ LCR [ኤልሲአር] ይጠቀማል።

የሚከተሉትን በአፋጣኝ ማድረግ ወሳኝ ነው፦

  • የሥርዓት መረጃን መመዝገብ

  • ወደ አጥቢያው የሚገቡ ወይም ከአጥቢያው የሚወጡ አባላትን መዛግብት ማዛወር።

  • ለአዳዲስ አባላት እና ለአባል ወላጆች አዲስ ልጆች መዛግብትን መፍጠር።

  • የአባልን ሞት መመዝገብ።

  • ጋብቻን እና የቤተሰብ መረጃን መመዝገብ።

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዘደንቱ፣ አንድ አባል የሚከተሉትን ለመቀበል ቃለ መጠይቅ ከመደረጉ በፊት የአባልነት መዝገቡ በተገቢው አጥቢያ ውስጥ እንዳለ ያረጋግጣል፦

  • የቤተክርስቲያን ጥሪ ለመስጠት።

  • የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ለመስጠት።

  • የመልከ ጼዴቅ ክህነትን ለመስጠት ወይም በዚያ ክህነት አንድ ክፍል ውስጥ ለመሾም።

መዝገቡ ከሚከተሉት ውስጥ የትኛውንም እንደማያካትትም ያረጋግጣል፦

  • ማብራሪያ

  • ስለእትመት ወይም ስለሥርዓት እገዳ የተሰጠ ሃሳብ

  • መደበኛ የአባልነት እገዳዎች

ከኤጲስ ቆጶሱ ወይም ከፀሐፊው ውጭ የአባልነት መዛግብት በማናቸውም አይነት ሁኔታዎች ለማንም ሊሰጡ ወይም በማንም ሊታዩ አይችሉም።

አባላት የራሳቸውን እና በቤት የሚኖሩ የማናቸውንም ጥገኛ ልጆች የአባልነት መረጃ በMember Tools app [በአባል መሳሪያዎች መተግበሪያ] ላይ ማየት ይችላሉ። የታተመ Individual Ordinance Summaries from [የግለሰብ የሥርዓት ማጠቃለያ ቅፅ] ቅጂዎችን ከጸሐፊው ሊጠይቁም ይችላሉ። ስህተቶች ከተገኙ ጸሐፊው በአባልነት መዝገቦች ላይ መስተካከላቸውን ያረጋግጣል።

33.6.1

በቤተክርስቲያኗ መዛግብት ውስጥ የሰፈሩ ስሞች

በአባልነት መዛግብት እና በሥርዓት የምስክር ወረቀት ላይ የሚሰፍረው የአካባቢው ህግ ወይም ልማድ ባስቀመጠው መሰረት የግለሰቡ ህጋዊ ሙሉ ስም ነው።

33.6.2

የመዝገብ አባላት

የሚከተሉት ግለሰቦች የመዝገብ አባላት ናቸው እናም የአባልነት መዝገብ ሊኖራቸው ይገባል፦

  • የተጠመቁ እና ማረጋገጫ የተቀበሉ።

  • ዕድሜያቸው ከ9 ዓመት በታች የሆኑ በረከትን የተቀበሉ ሆኖም ያልተጠመቁ።

  • በየትኛውም የዕድሜ ክልል የሚገኙ በአእምሮ ውስንነት ምክንያት ተጠያቂነት የሌለባቸው።

  • ከ9 ዓመት በታች የሆኑ በረከትን ያልተቀበሉ ልጆች፣ የሚከተሉት ሁለቱም በሚሟሉበት ጊዜ፦

    • ከወላጆቻቸው ወይም ከቅድመ ዓያቶቻቸው አንዱ የቤተክርስቲያኗ አባል ሲሆን።

    • ሁለቱም ወላጆች መዝገብ እንዲፈጠር ፈቃድ ሲሰጡ። (አንድ ወላጅ ብቻ ልጁን የማሳደግ ህጋዊ መብት ያለው ከሆነ፣ የዚያ ወላጅ ፈቃድ በቂ ነው።)

እድሜው 9 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነ፣ በአባልነት መዝገብ ላይ የሚገኝ ሆኖም ያልተጠመቀ እና ማረጋገጫ ያልተቀበለ ሰው የመዝገብ አባል አይደለም። ሆኖም፣ ግለሰቡ 18 ዓመት እስኪሞላው ድረስ፣ ግለሰቡ የሚኖርበት ክፍል የአባልነት መዝገቡን ይይዛል። በዚያን ጊዜ ግለሰቡ ላለመጠመቅ ከመረጠ፣ ኤጲስ ቆጶሱ የአባልነት መዝገቡን ይሰርዘዋል። የካስማ ፕሬዚዳንቱ ፈቃድ ያስፈልጋል።

ወላጅን ጨምሮ በግለሰቡ ወይም በህጋዊ አሳዳጊ ካልተጠየቀ በስተቀር፣ በአእምሮ ውስንነት ምክንያት ያልተጠመቁ ሰዎች መዛግብት አይሰረዙም።

33.6.3

አዲስ የአጥቢያ አባላት መዛግብት

የአጥቢያ ፀሐፊው ወይም የአጥቢያ ረዳት ፀሐፊው የግለሰቡን የሥርዓት ማጠቃለያ ትክክለኛነት ለመገምገም የአባልነት መዝገቦቻቸው እንደደረሱ ከአዲስ የአጥቢያ አባላት ጋር ይገናኛል።

33.6.6

ከጂዮግራፊያዊ አጥቢያቸው ውጭ የሚያገለግሉ አባላት መዛግብት

33.6.6.2

የሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያንን መዛግብት

24.6.2.8ን ይመልከቱ።

33.6.13

የተፋቱ ወላጆች ልጆች መዛግብት

ሁሉሙ የአባልነት መዛግብት በአካባቢው ህግ ወይም ልማድ መሰረት የተቀመጠውን የግለሰብ ሥም ይጠቀማሉ። ይህ የተፋቱ ወላጆች ልጆችን ያካትታል።

የተፋቱ ወላጆች ያሏቸው ልጆች ብዙውን ጊዜ በሁለቱም ወላጆች አጥቢያዎች ውስጥ የቤተክርስቲያኗ ስብሰባዎችን ይካፈላሉ። የልጁን ኦፊሴላዊ የአባልነት መዝገብን የሚይዝ እና የሚያዘምን አንድ ክፍል ብቻ ሲኖር፣ ከክፍል ውጭ የሆነ የአባል መዝገብ እሱ/ዋ በሚገኝበት/በምትገኝበት በሁለተኛው አጥቢያ ሊፈጠር ይችላል። ይህ የልጁን ስም እና የአድራሻ መረጃ በአጥቢያ ዝርዝሮች ላይ እና በክፍል ስም ዝርዝር ላይ እንዲታይ ያስችላል።

ከክፍል ውጭ የአባል መዝገብ ያላቸው ልጆች ጥሪ ሊቀበሉም ይችላሉ።

33.6.15

የአባልነት መዛግብት የዝውውር እገዳ

መደበኛ የአባልነት እገዳዎች ወይም ሌላ አሳሳቢ ጉዳይ በመጠባበቅ ላይ እያለ አንድ አባል ወደ ሌላ ቦታ ከተዛወረ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም ፈቃድ ያለው ጸሐፊ በአባልነት መዝገቡ ላይ የዝውውር እገዳ ሊጥል ይችላል። ይህንን ለማድረግ LCR [ኤልሲአርን] ይጠቀማል።

እገዳውን የጣለው የክህነት መሪ እንዲዛወር እስካልፈቀደ ድረስ የዝውውር እገዳ የተጣለበት መዝገብ ወደ አዲስ ክፍል አይዛወርም።

33.6.16

“አድራሻው የማይታወቅ” ማህደር ከሚለው የመጡ መዛግብት

አንዳንድ ጊዜ፣ አንድ አባል መዝገቡ/ቧ በቤተክርስቲያኗ ዋና መሥሪያ ቤት “አድራሻ የማይታወቅ ማህደር“ ውስጥ ከገባ በኋላ አድራሻው/ዋ ይገኛል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የአጥቢያው ጸኃፊ በLCR [ኤልሲአር] በኩል መዝገቡን ለማግኘት ይጠይቃል።

33.6.17

የሥርዓት መረጃን መመዝገብ እና ማስተካከል

ምዕራፍ 18ን ይመልከቱ።

33.6.19

የአባልነት መዛግብትን ኦዲት ማድረግ

በየአመቱ፣ የካስማ ፀሐፊው ወይም ረዳት የካስማ ፀሐፊው የአባልነት መዛግብት ኦዲት LCR [ኤልሲአርን] በመጠቀም በየአጥቢያው መካሄዱን ያረጋግጣሉ። ኦዲት በየዓመቱ ሰኔ 30 መጠናቀቅ አለበት።

33.7

ታሪካዊ መዛግብት

33.7.1

የአጥቢያ እና የካስማ ታሪኮች

ጌታ ቤተክርስቲያኗን የተመለከቱ “የአስፈላጊ ነገሮች ሁሉ ታሪኮች“ እንዲጻፉ እና እንዲያዙ አዟል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 69፥3፤ በተጨማሪም ቁጥር 5ን፤ አልማ 37፥2ን ይመልከቱ)።

በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ክፍል ያንን ክፍል የሚመለከቱ አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ መመዝገብ አለበት።

ታሪክን ፅፎ ማቆየት የሚፅፉትን እና የሚያነቡትን እምነት የሚያጠናክር መንፈሳዊ ሥራ ነው።

የካስማ ጸኃፊ ወይም የተመደበ ረዳት የካስማ ጸኃፊ የካስማውን ታሪክ ያዘጋጃል። ኤጲስ ቆጶሱም ለአጥቢያው ተመሳሳይ አካሄድን ይከተላል። ተጨማሪ መረጃዎች በ Stake, District, and Mission Annual Histories [ካስማ፣ አውራጃ እና ሚስዮን ዓመታዊ ታሪኮች] ChurchofJesusChrist.org ላይ ይገኛሉ፡፡

33.8

የመዛግብት ሚስጥራዊነት

የቤተክርስቲያኗ መዛግብት የሚገኙት በወረቀት ላይም ይሁን በዲጂታል መልኩ ሚስጥራዊ ናቸው። እነዚህ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • የአባልነት መዛግብትን።

  • የገንዘብ መዛግብትን።

  • የስብሰባ ማስታወሻዎችን።

  • ኦፊሴላዊ ቅጾችን እና ሰነዶችን (የአባልነት ምክር ቤቶች መዛግብትን ጨምሮ)።

መሪዎች፣ ከአባላት የሚሰበሰበው መረጃ፦

  • ቤተክርስቲያኗ በምትፈልገው ነገር ላይ የተወሰነ መሆኑን።

  • ለተፈቀዱ የቤተክርስቲያኗ ዓላማዎች ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ መሆናቸውን።

  • እንዲጠቀሟቸው ለተፈቀደላቸው ብቻ የሚሰጡ መሆናቸውን።

በኤሌክትሮኒክ መንገድ የተከማቸ መረጃ ደህንነቱ የተጠበቀ እና በተገቢ ሁኔታ ጥበቃ የሚደረግለት መሆን አለበት (33.9.1ን ይመልከቱ)።

33.9

የመዛግብት አስተዳደር

33.9.1

ጥበቃ

የቤተክርስቲያኗ መዛግብት፣ ሪፖርቶች እና መረጃዎች ሁሉ ካልተፈቀደ አጠቃቀም፣ መለወጥ፣ መወገድ ወይም ይፋ መደረግ ሊጠበቁ ይገባል። ይህ መረጃ ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ መቀመጥ አለበት።

የጠፉ ወይም የተሰረቁ የቤተክርስቲያኗ ይዞታ የሆኑ መሳሪያዎች ወይም የማከማቻ ሚዲያዎች ወደሚከተለው በአፋጣኝ ሪፖርት መደረግ incidents.ChurchofJesusChrist.orgአለባቸው። የቤተክርስቲያኗን መረጃ አላግባብ ጥቅም ላይ ማዋልም ሪፖርት መደረግ አለበት።

33.9.1.1

የተጠቃሚ ስሞች እና የይለፍ ቃላት

የካስማ ፕሬዚዳንቶች፣ ኤጲስ ቆጶሳት እና ሌሎች መሪዎች የቤተክርስቲያኗ የተጠቃሚ ስማቸውን እና የይለፍ ቃላቸውን ለአማካሪዎች፣ ለጸኃፊዎች፣ ለዋና ጸሃፊዎች ወይም ለሌሎች ማሳወቅ የለባቸውም።

33.9.1.3

የመረጃ ጥበቃ ነጻነት

ብዙ አገሮች የግል መረጃ አያያዝን የሚቆጣጠሩ የመረጃ ጥበቃ ሕጎችን አውጥተዋል። ይህ በአባልነት መዛግብት ውስጥ ያሉ መረጃዎችን እና ግለሰቦችን የሚለዩ ሌሎች የቤተክርስቲያኗ መዛግብትን ያካትታል። ስለቤተክርስቲያኗ መዝገቦች የአካባቢ አስተዳደር የመረጃ ጥበቃ ሕጎች አተገባበር ጥያቄዎች ያሏቸው መሪዎች የቤተክርስቲያኗን የመረጃ ጥበቃ ነጻነት ቢሮ ማነጋገር DataPrivacyOfficer@ChurchofJesusChrist.org ይችላሉ።

አትም