መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
34. ገንዘብ እና ኦዲት


“34. ገንዘብ እና ኦዲት፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 (እ.አ.አ)]።

“34. ገንዘብ እና ኦዲት፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ

ልጅ ኤንቨሎፕ ይዞ

34.

ገንዘብ እና ኦዲት

34.0

መግቢያ

አሥራት እና የጾም በኩራት ቤተክርስቲያኗ የደህንነት እና በዘለዓለማዊ ህይወት ከፍ ከፍ የማድረግን ሥራን እንድትከታተል ያስችላታል (1.2 ይመልከቱ)። ይህ ገንዘብ የተቀደሰ ነው። የቤተክርስቲያኗን አባላት መስዋዕትነት እና እምነት ይወክላሉ (ማርቆስ 12፥41–44 ይመልከቱ)።

34.2

የአጥቢያ ገንዘብ-ነክ ጉዳዮች መሪ

34.2.1

የኤጲስ ቆጶስ አመራር

ኤጲስ ቆጶሱ የአጥቢያውን ገንዘብ የተመለከቱ የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉበት። የተወሰኑትን ስራዎች ለአማካሪዎቹ እና ጸኃፊዎቹ በውክልና ይሰጣል።

ኤጲስ ቆጶሱ፦

  • አባላት ሙሉ አስራት እንዲከፍሉ እና በቸርነት የጾም በኩራት እንዲሰጡ ያስተምራል እንዲሁም ያነሳሳል (34.3ን ይመልከቱ)።

  • የቤተክርስቲያኗ ገንዘብ በተገቢው ሁኔታ መያዙን እና መመዝገቡን ያረጋግጣል (34.5 ን ይመልከቱ)።

  • የሂሳብ መግለጫውን በየወሩ ይገመግማል እንዲሁም ማናቸውም ጉዳዮች በአፋጣኝ መፈታታቸውን ያረጋግጣል።

  • የድርጅት መሪዎች እና ጸሃፊዎች በተቀደሰ የቤተክርስቲያን ገንዘብ ላይ ያለባቸውን ኃላፊነት ማወቃቸውን ያረጋግጣል።

  • የአጥቢያውን ዓመታዊ በጀት ያዘጋጃል እንዲሁም ያስተዳድራል (34.6ን ይመልከቱ)።

  • የአስራት መግለጫን ለመቀበል በየአመቱ ከአጥቢያ አባላት ጋር ይገናኛል።

34.2.2

የአጥቢያ ጸሃፊዎች

ኤጲስ ቆጶሱ የአጥቢያ ፀሐፊውን ወይም ረዳት የአጥቢያ ፀሐፊውን የአጥቢያውን የገንዘብ መዝገብ እንዲጠብቁ ይመድባል። ጸሃፊዎች የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ ለመጠበቅ እንዲሁም የቤተክርስቲያኗ መዛግብት ትክክለኛ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ወቅታዊ ፖሊሲዎችን በጥንቃቄ ይከተላሉ።

ጸኃፊው የሚከተሉት ኃላፊነቶች አሉበት፦

  • ከኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል የተቀበለውን ማንኛውንም ገንዘብ ይመዘግባል እንዲሁም ባንክ ያስገባል።

  • የሂሳብ መግለጫውን በየወሩ ይገመግማል እንዲሁም ማናቸውም ጉዳዮች በአፋጣኝ መፈታታቸውን ያረጋግጣል።

  • የአጥቢያው በጀት ሲታቀድ ኤጲስ ቆጶሱን ይረዳል (34.6.1ን እና 34.6.2 ን ይመልከቱ)።

  • አባላት የአስተዋፅኦ መግለጫዎቻቸውን ማግኘት መቻላቸውን ያረጋግጣል እንዲሁም እንዳስፈላጊነቱ እገዛ ያደርጋል።

ጸሃፊዎች የመልከ ጼዴቅ ክህነት ያላቸው እና የታደሰ የቤተመቅደስ መግቢያ መታወቂያ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

34.3

አስተዋፅኦዎች

34.3.1

አስራት

አስራት ማለት የአንድን ሰው ገቢ አንድ አስረኛ ለእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን መስጠት ማለት ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 119፥3–4 ይመልከቱ፤ ትርፍ ማለት ገቢ ማለት ነው)። ገቢ ያላቸው አባላት ሁሉ አሥራት መክፈል አለባቸው።

34.3.1.2

የአስራት መግለጫ

እያንዳንዱ አባል የእርሱን ወይም የእርሷን የአሥራት መግለጫ ለመቀበል በየአመቱ የመጨረሻዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር ይገናኛል/ትገናኛለች።

ሁሉም አባላት የሚከተሉትን ለማከናወን ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር እንዲገናኙ ተጋብዘዋል፦

  • አሥራት ከፋይ መሆናቸውን ለኤጲስ ቆጶሱ ለመግለፅ።

  • የአስተዋጿቸው መዛግብት ትክክል መሆናቸውን ለማረጋገጥ።

የሚቻል ከሆነም፣ ሁሉም የቤተሰብ አባላት፣ ልጆችን ጨምሮ መገኘት አለባቸው።

34.3.2

የጾም በኩራት

የቤተክርስቲያን መሪዎች አባላት የጾምን ህግ እንዲኖሩ ያበረታታሉ። ይህ በቸርነት የጾም በኩራት መስጠትን ያካትታል (22.2.2 ን ይመልከቱ)።

ስለጾም በኩራት ገንዘብ አጠቃቀም ያሉት መመሪያዎች በ22.5.2 ውስጥ ቀርበዋል።

34.3.3

ለሚስዮናውያን የሚውል ገንዘብ

ለአጥቢያው የሚስዮናዊ ፈንድ የሚደረጉ መዋጮዎች በዋናነት በአጥቢያው ውስጥ ያሉ የሙሉ ጊዜ ሚስዮናውያን የሚጠበቅባቸውን የአስተዋፅኦ መጠን ለማሟላት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

ለአጠቃላይ የሚስዮናውያን ፈንድ የሚደረገውን አስተዋፅዖ ቤተክርስቲያኗ ለአጠቃላይ የሚስዮን ጥረቶች ትጠቀምበታለች።

34.3.7

አስተዋፅኦዎች ሊመለሱ አይችሉም።

አሥራት እና የጾም በኩራት ለቤተክርስቲያን ከተሰጡ በኋላ የጌታ ናቸው። ለእርሱ ተለይተው ተቀድሰዋል።

የካስማ ፕሬዚዳንቶች እና ኤጲስ ቆጶሳት እነዚህ መዋጮዎች መመለስ እንደማይችሉ አሥራትን እና በኩራቶችን ለሚሰጡ ሰዎች ያሳውቃሉ።

34.4

የአስራት እና የሌሎች በኩራት ሚስጥራዊነት

በአንድ ለጋሽ የሚከፈል አሥራት እና ሌሎች በኩራቶች በሚስጥር ይያዛሉ። ይህንን መረጃ ማግኘት ያለባቸው ኤጲስ ቆጶሱ እና እነዚህን አሰተዋፅዖዎች ለመመልከት ፈቃድ የተሰጣቸው ብቻ ናቸው።

34.5

የቤተክርስቲያን ገንዘብ አያያዝ

የካስማ ፕሬዚዳንቱ እና ኤጲስ ቆጰሱ ሁሉም የቤተክርስቲያን ገንዘብ በአግባቡ መያዙን ያረጋግጣሉ፡፡ ኤጲስ ቆጶሱ እና ጸሃፊዎች “Sacred Funds, Sacred Responsibilities [የተቀደሰ ገንዘ፣ የተቀደሱ ኃላፊነቶች]” የሚለውን ቪዲዮ ቢያንስ በዓመት አንዴ እንዲከልሱ ይበረታታሉ።

22:58

34.5.1

የጓደኝነት መርህ

የጓደኝነት መርህ ሁለት ግለሰቦችን ይፈልጋል—አንድ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባልን እና አንድ ጸኃፊን ወይም ሁለት የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባላትን—እነዚህ የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ በሚመዘግቡበት እና በሚሰጡበት ጊዜ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይጠይቃል።

መሪዎች የይለፍ ቃሎቻቸውን መጠበቅ አለባቸው እንዲሁም በጭራሽ ለሌሎች ማጋራት የለባቸውም (33.9.1.1ን ይመልከቱ)።

34.5.2

አስራትን እና ሌሎች በኩራቶችን መቀበል

ጌታ የቅዱሳንን አሥራት እና ሌሎች በኩራቶች እንዲቀበሉ እና ተጠያቂነትን እንዲያሰፍኑ ለኤጲስ ቆጶሳት በአደራ ሰጥቷቸዋል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥30–33119ን ይመልከቱ)። አሥራት እና የጾም በኩራት መቀበል የሚችሉት ኤጲስ ቆጶሱ እና አማካሪዎቹ ብቻ ናቸው። ሚስቶቻቸው፣ ሌሎች የቤተሰቦቻቸው አባላት፣ ጸሃፊዎች ወይም ሌሎች የአጥቢያ አባላት በምንም አይነት ሁኔታ እነዚህን አስተዋፅኦዎች መቀበል የለባቸውም።

34.5.3

አስራትን እና ሌሎች በኩራቶችን ማረጋገጥ እና መመዝገብ

አስተዋፅዖዎች በተሰበሰቡበት እሁድ መረጋገጥ እና መመዝገብ አለባቸው። አንድ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል አና ጸኃፊ ወይም ሁለት የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባላት እያንዳንዱን ኤንቨሎፕ በጋራ ይከፍታሉ። በውስጡ ያለው ገንዘብ Tithing and Other Offerings form [በአስራት እና ሌሎች በኩራቶች ቅፅ] ላይ ከተጻፈው መጠን ጋር አንድ አይነት መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። እያንዳንዱን ልገሳ በአግባቡ ይመዘግባሉ። ገንዘቡ እና የተጻፈው መጠን የሚለያይ ከሆነ ልዩነቱን ለመፍታት በተቻለ ፍጥነት ለጋሹን ያነጋግራሉ።

34.5.4

አስራትን እና ሌሎች በኩራቶችን በባንክ ማስገባት

የተመዘገበው የገንዘብ መጠን ከተቀበሉት ገንዘብ ጋር እኩል መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ ገንዘቡን ወደ ባንክ የማስገቢያ መረጃ መዘጋጀት አለበት።

የ24 ሰዓት የባንክ ተቀማጭ አገልግሎት በሚገኝበት ቦታ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባሉ እና ሌላ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ ገንዘቡ በተከፈተበትና በተረጋገጠበት ቀን ወደ ባንክ ያስገቡታል።

የ24 ሰዓት የባንክ ተቀማጭ አገልግሎት ከሌለና ባንኩ እሁድ ዝግ ከሆነ፣ ኤጲስ ቆጶሱ አንድን የመልከ ጼዴቅ ክህነትተሸካሚ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተቀማጭ እንዲያደርገው ይመድበዋል። እነዚህን ማድረግ አለበት፦

  • ገንዘቡ ባንክ እስኪገባ ድረስ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል።

  • ባንክ የገባበትን ቀን እና የተቀማጩን መጠን የሚያሳይ ደረሰኝ ይቀበላል።

34.5.5

ለቤተክርስቲያኗ ገንዘብ ጥበቃ ማድረግ

የቤተክርስቲያኗ ገንዘብ ሃላፊነት ያለባቸው አባላት ገንዘብ በመሰብሰቢያው አዳራሽ ማሳደር ወይም እንደ ስብሰባ እና አክቲቪቲዎች ባሉት በማናቸውም ጊዜያት ያለጥበቃ ጥለው መሄድ የለባቸውም፡፡

34.5.7

የካስማ እና የአጥቢያ ክፍያዎችን ማስተደደር

ያለበላይ መሪው ፈቃድ ምንም የካስማ ወይም የአጥቢያ ወጪዎች ሊወጡ ወይም ሊከፈሉ አይችሉም።

እያንዳንዱን ክፍያ ሁለት የተፈቀደላቸው መሪዎች መፍቀድ አለባቸው። ከሁለቱ አንዱ የካስማ አመራር ወይም የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል መሆን አለበት። ምንም እንኳን አማካሪዎች ክፍያዎችን የማፅደቅ ሥልጣን ቢኖራቸውም፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ ወይም ኤጲስ ቆጶሱ እያንዳንዱን ክፍያ መገምገም አለባቸው። መሪዎች የራሳቸውን ክፍያ ማፅደቅ የለባቸውም።

አንድ ኤጲስ ቆጶስ የጾም በኩራቶችን ከመጠቀሙ በፊት ወይም የኤጲስ ቆጶስ ትእዛዝን ለራሱ ወይም ለቤተሰቡ ከማፅደቁ በፊት የካስማ ፕሬዘደንቱን የፅሁፍ ማረጋገጫ ማግኘት ያስፈልገዋል። አንድ ኤጲስ ቆጶስ የጾም በኩራቶችን ወይም የኤጲስ ቆጶስ ትእዛዝን ለካስማ ፕሬዚዳንቱ ወይም ለቤተሰቡ ጥቅም ከማፅደቁ በፊት የዋና አካባቢ አመራርን የፅሁፍ ማረጋገጫ ማግኘት ያስፈልገዋል። ለመመሪያ 22.5.1.2 ይመልከቱ።

ተመላሽ ገንዘብ የሚጠይቅ አባል የሁሉንም ሪሲቶች ወይም ደረሰኞች የወረቀት ወይም ኤሌክትሮኒክ ቅጂ ያቀርባል። እርሱ ወይም እርሷ የግዢውን ዓላማ፣ መጠን፣ እና ቀን ያካትታል/ታካትታለች።

ገንዘብ አስቀድሞ ወጪ የተደረገ ከሆነ፣ አባሉ ዓላማውን፣ መጠኑን እና ቀኑን በመጥቀስ የክፍያ መጠየቂያ ቅፅ ያቀርባል። ወጪው ከተከፈለ በኋላ አባሉ (1) ለወጡት ወጪዎች ሪሲቶችን ወይም ደረሰኞችን ያቀርባል እንዲሁም (2) ጥቅም ላይ ያልዋለ ገንዘብን ይመልሳል። ተመላሽ ገንዘብ እንደገና ወደ ባንክ መግባት አለበት።

34.5.9

የገንዘብ መዛግብት አያያዝ

እያንዳንዱ ካስማ እና አጥቢያ ወቅታዊ፣ ትክክለኛ የገንዘብ መዛግብትን አለባቸው።

ስለመዛግብት እና ስለሪፖርቶች አጠቃቀም እንዲሁም ስለማቆየት መረጃ ለማግኘት ጸሐፊዎች ከቤተክርስቲያኗ ዋና መሥሪያ ቤት ወይም ከዋና አካባቢው ቢሮ የሚመጡ መመሪያዎችን መመልከት አለባቸው። የገንዘብ መዛግብት ቢያንስ ለሶስት አመታት እና ለተያዘው ዓመት በተጨማሪ ሊቆዩ ይገባል።

34.6

በጀት እና ወጪዎች

የተያዘ በጀት ፕሮግራም የካስማዎችን እና የአጥቢያዎችን አክቲቪቲዎች እና ፕሮግራሞች ወጪ ለመሸፈን አጠቃላይ የቤተክርስቲያን ገንዘብን ያቀርባል።

ብዙዎቹ አክቲቪቲዎች ቀላል እንዲሁም አነስተኛ ወይም ምንም ወጪ የማይጠይቁ መሆን አለባቸው።

34.6.1

የካስማ እና የአጥቢያ በጀቶች

እያንዳንዱ ካስማ እና አጥቢያ ዓመታዊ በጀት ያዘጋጃል እንዲሁም ያንቀሳቅሳል። የካስማው ፕሬዚዳንት የካስማውን በጀት ያስተዳድራል፤ እንዲሁም ኤጲስ ቆጶሱ የአጥቢያውን በጀት ያስተደዳራል።

መመሪያዎች ከታች ተዘርዝረዋል፦

  • ሁልጊዜ የሚያስፈልጉ ወጪዎች መካተታቸውን ለማረጋገጥ ባለፈው ዓመት የወጡትን ወጪዎች መጠን መገምገም።

  • ድርጅቶች የበጀት ፍላጎቶቻቸውን በዝርዝር እንዲገምቱ መጠየቅ።

  • የተፈቀደ የበጀት አሰራርን በመጠቀም በጀቱን ማጠናቀር።

34.6.2

የተያዘ በጀት

34.6.2.1

የበጀት ምደባ

የበጀት ገንዘብ በሚከተሉት ምድቦች ውስጥ በሚደረግ ተሳትፎ ላይ በመመስረት በየሩብ ዓመቱ ይመደባል፦

  • የቅዱስ ቁርባን ስብሰባ

  • ወጣት ወንዶች

  • ወጣት ሴቶች

  • የመጀመሪያ ክፍል ልጆች ከ7 – 10 ዓመት

  • ያላገቡ ወጣት ጎልማሶች

የተሳትፎ ሪፖርትን በትክክል እና በሰዓቱ ማቅረብ አስፈላጊ ነው (33.5.1.1 ን ይመልከቱ)።

34.6.2.2

ተገቢ የበጀት አጠቃቀም

የካስማ ፕሬዘደንቶች እና ኤጲስ ቆጶሳት የተያዘ የበጀት ገንዘብ በጥበብ ጥቅም ላይ መዋሉን ያረጋግጣሉ።

የአጥቢያ ወይም የካስማ የተያዘ የበጀት ገንዘብ የአክቲቪቲዎችን፣ የፕሮግራሞችን፣ የማኑዋሎችን እና የአቅርቦቶችን ወጪዎች ለመሸፈን ጥቅም ላይ መዋል አለበት።

34.6.2.3

ትርፍ በጀት

የተረፈ የተያዘ የበጀት ገንዘብ ጥቅም ላይ መዋል የለበትም። የተረፈ የአጥቢያ ገንዘብ ወደካስማው መመለስ አለበት።

34.7

ኦዲት

34.7.1

የካስማ የኦዲት ኮሚቴ

የካስማ ፕሬዘደንቱ የካስማ የኦዲት ኮሚቴን ይሰይማል። ይህ ኮሚቴ የካስማ እና የአጥቢያ ገንዘብ በቤተክርስቲያን ፖሊሲ መሰረት መያዙን ያረጋግጣል።

34.7.3

የገንዘብ ኦዲት

የካስማ ኦዲተሮች የካስማን፣ የአጥቢያዎችን እና የቤተሰብ ታሪክ ማዕከላትን የሂሳብ መዛግብት በአመት ሁለት ጊዜ ይመረምራሉ።

የክፍሉ የበላይ መሪ እና ሂሳብ ለመስራት የተመደበው ጸሐፊ በኦዲት ወቅት ጥያቄዎችን ለመመለስ ዝግጁ መሆን አለባቸው።

34.7.5

የቤተክርስቲያኗ ገንዘብ መጥፋት፣ መሰረቅ፣ መመዝበር ወይም አላግባብ ጥቅም ላይ መዋል

የሚከተሉት ከተከሰቱ የካስማ ፕሬዚዳንቱ ወይም የካስማ ኮሚቴ ሰብሳቢው ጉዳዩን በአስቸኳይ እንዲያውቁ ማድረግ ይገባል

  • የቤተክርስቲያን ገንዘብ ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ።

  • አንድ መሪ የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ ከመዘበረ ወይም አላግባብ ጥቅም ላይ ካዋለ።