“37. የተለዩ ካስማዎች፣ አጥቢያዎች እና ቅርንጫፎች፣” ከአጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ [2023 [እ.አ.አ)]
“37. የተለዩ ካስማዎች፣ አጥቢያዎች እና ቅርንጫፎች፣” ከአጠቃላይ የመመሪያ መፅሐፍ የተመረጡ
37.
የተለዩ ካስማዎች፣ አጥቢያዎች እና ቅርንጫፎች
37.0
መግቢያ
አንድ የካስማ ፕሬዚዳንት አባላትን ለማገልገል በዚህ ምዕራፍ እንደተብራራው የተለዩ ካስማዎች፣ አጥቢያዎች እና ቅርንጫፎች እንዲፈጠሩ ሃሳብ ማቅረብ ይችላል።
37.1
የቋንቋ አጥቢያዎች እና ቅርንጫፎች
አንድ የካስማ ፕሬዚዳንት (1) የአካባቢውን የአፍ መፍቻ ቋንቋ ለማይናገሩ ወይም (2) የምልክት ቋንቋ ለሚጠቀሙ የካስማ አባላት የቋንቋ አጥቢያ ወይም ቅርንጫፍ እንዲፈጠር ሀሳብ ሊያቀርብ ይችላል።
37.7
በካስማዎች፣ በሚስዮኖች እና በዋና አካባቢዎች ያሉ ቡድኖች
ቡድኖች በኤጲስ ቆጶስ፣ በቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት ወይም በሚስዮን ፕሬዚዳንት የበላይነት የሚመሩ ፈቃድ ያላቸው አነስተኛ የአባላት ስብሰቦች ናቸው። የካስማ ወይም የሚስዮን ፕሬዚዳንቱ የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲኖሩ ቡድን እንዲፈጠር ሃሳብ ሊያቀርብ ይችላል፦
-
አባላት ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎች ከአጥቢያ ወይም ከቅርንጫፍ ጋር ለመገናኘት የሚያደርጉት ጉዞ አስቸጋሪ ከሆነ።
-
አነስተኛ ቁጥር ያላቸው አባላት በአጥቢያው ወይም በቅርንጫፉ ውስጥ ከሚነገረው የተለየ ቋንቋ የሚናገሩ ከሆነ።
-
በወታደራዊ አገልግሎት ውስጥ ያሉ አባላት በቡድን ቢደራጁ በተሻለ ሁኔታ አገልግሎት ሊያገኙ ይችላሉ።
አንድ ቡድን ቢያንስ ሁለት አባላት ሊኖሩት ይገባል። አንደኛው በአሮናዊ ክህነት ውስጥ ብቁ ካህን መሆን አለበት ወይም ብቁ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተሸካሚ መሆን አለበት።
በካስማዎች ውስጥ የካስማ ፕሬዚዳንቱ ቡድኑን እንዲያደራጅ እና እንዲከታተል አንድን ኤጲስ ቆጶስ ወይም የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት ይመድባል። በሚስዮን ውስጥ የሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ቡድኑን እንዲያደራጅ እና እንዲከታተል አንድን የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት ይመድባል።
የካስማ ፕሬዚዳንቱ፣ የሚስዮን ፕሬዚዳንቱ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቱ የቡድን መሪ ይጠራል፣ እንዲሁም ለአገልግሎት ይለያል። የቡድን መሪው ቅዱስ ቁርባንን ማስተዳደርን ጨምሮ የቡድን ስብሰባዎችን ያደራጃል እንዲሁም ይመራል።
የቡድን መሪው የክህነት ቁልፎች የሉትም እናም የሚከተሉትን ለማድረግ ፈቃድ የለውም፦
-
አስራትና በኩራቶችን መቀበል።
-
ለአባላት ስለከባድ ኃጢያት ምክር መስጠት።
-
መደበኛ እና መደበኛ ያልሆነ የአባልነት እገዳዎችን መጣል።
-
የክህነት ቁልፎችን የሚጠይቁ ሌሎች ኃላፊነቶችን ማከናወን።
በተለምዶ ቡድኖች የአንድ ክፍል መሠረታዊ ፕሮግራምን ይጠቀማሉ።
የቡድን አባላት የአባልነት መዛግብት ቡድኑን በሚከታተለው አጥቢያ ወይም ቅርንጫፍ ውስጥ ይቀመጣሉ።
የቤተክርስቲያኗ ዋና መሥሪያ ቤት ለቡድኖች የክፍል ቁጥር አይሰጥም።