2010 (እ.አ.አ)
አዲሱ ሰው
ጁላይ 2010


ወጣቶች

አዲሱ ሰው

ባለሁበት መገኘት እንደሚገባኝ መሰማቱ ያስቸግረኝ ነበር። ቤተሰቤ ከአገሩ አቋርጠው ወደሌላው ቦታ ሄደው ነበር። አሁን የምንኖርበት ዎርድ ትልቅ የወጣቶች ቡድን ነበረው. ነገር ግን ይህም “አዲሱ ሰው” የምሆንበት የመጀመሪያ ጊዜ ነበር። ከዚህም በላይ የሚያከፋውም ወደ አሲስ ትምህርት ቤት መሄድ ነበረብኝ፣ እና “በምሳ ጊዜ ከማን ጋር ነው የምቀመጠው?” የሚለው አስተሳሰብ በአዕምሮዬ ወዳው መጣብኝ። ምናልባት ከቤተክርስትያን አንድ ሰው አያለሁ፣ ነገር ግን እኔ በቡድናቸው ውስጥ እንደሚፈልጉኝ ስላላወቅኩኝ በሌሎች የምሳ ቡድን ውስጥ ገፍቼ ለመግባት አልፈለኩም ነበር።

የትምህርት ቤት የመጀመሪያ ቀኔ ለረጅም ጊዜ የሚሄድ መሰለ። በመጨረሻው የምሳ ደውል ተደወለ። ወደምሳ ክፍል በቀስታ ስገባ፣ የማውቀው ሰው እንዳገኝ የሰማይ አባት እንዲረዳኝ ጸለይኩኝ። የማቀው ሰም ለማየትም ዞር ዞር አልኩኝ። ማንም አልነበረም። ስለዚህ በምሳ ክፍሉ ራቅ ወዳለው ቦታ ላይ ሄጄ በመቀመጥ ምሳዬን በላሁ።

በእዛው ቀን በኋላም በህሳብ ክፍል ውስጥ የማውቀው ሰው አየሁ። በዛ ቀን ጠዋት ዴቪድን በመንፈሳዊ ትምህርት ቤት ውስጥ አይቼው ነበር። የክፍል መመሪያዬን ለመመልከተ ጠየቀኝ እና አንድ አይነት የምሳ ክፍል እንዳለን አወቀ። “በምሳ ጊዜ የት ነበርክ?” አለኝ።

“በክፍሉ ዳርቻ ተቀምጬ በላሁ” ብዬ መለስኩለት።

“ነገ ና እና ከእኔ ጋር ምሳህን ብላ” አለኝ።

የእያንዳንዳችንን ፍላጎት ለሚያውቀው እና የእያንዳንዳችንን ጸሎት ለሚመልሰው ለሚያፈቅረው የሰማይ አባት ምስጋና አለኝ። የጓደኝነትን ክንድ ለመዘርጋት ፈቃደኛ ለሚሆነውም ዳግሞ ምስጋና ይሰማኛል። እንደ ጋብዛ አይነት ቀላል የሆነውም ነገር ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል።