2010 (እ.አ.አ)
ቤተሰቦችን እና ቤቶችን ማጠናከር
ጁላይ 2010


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሐምሌ 2010 (እ.አ.አ)

ቤተሰቦችን እና ቤቶችን ማጠናከር

ይህን መልእክት አጥኑ፣ እና ትክክል በሆነውም ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩ። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን በህይወታችሁ ውስጥ የሚሳተፍ ክፍል እንዲኖራት ለማድረግ እንዲረዷችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።

ከቅዱስ መጻህፍት፧ ዘፍጥረት 18፧19; ሞዛያ 4፧15; ትምህርት እና ቃል ኪዳን 93፧40; ሙሴ 6፧55–58

በእያንዳንዶቹ እድሎች ማጠናከር

“እያንዳንዳችን የተለያዩ የቤተሰብ ጉዳዮች አሉን። አንዳንድ ቤተሰቦች በቤት ውስጥ እናት እና አባት ከለጆች ጋር ይገኛሉ። አንዳንድ የተጋቡ ሰዎች በቤታቸው ውስጥ ልጆቻቸው የሉም። ብዙ የቤተክርስትያኗ አባላት ያላገቡ ናቸው እና ሌሎችም ያላገቡና ልጆች ያሏቸው ናቸው። ሌሎችም ብቻቸውን የሚኖሩ ባለቤቶቻቸው የሞቱባቸው ናቸው።

“ቤተሰቦቻችን ምንም አይነት ቢሆኑም፣ ቤተሰቦታችንን ለማጠናከር ወይም ሌሎችን ለማጠናከር እያንዳንዳችን ለመስራት እንችላለን።

“[አንድ ጊዜ] ከእህቴ ልጅ እና ከቤተሰቧ ጋር በቤቷ ቆይቼ ነበር። ልጆቹ በእዛ ቀን ማታልጆች ወደ መኝታ ከመሄዳቸው በፊት፣ አጭር የቤተሰብ ምሽት አድርገን እና የቅዱስ መጻህፍት ታሪኮችን አነበብን። አባታቸው ስለሌሂ ቤተሰብ እና የእግዚአብሔር ቃል የሆኑትን የብረት በትሮችን በጽኑነት እንዲይዙ ልጆቹን እንዳስተማራቸው ተናገረ። የብረት በትሩን በፅኑነት መያዛቸው በደህናነት ይጠብቃቸዋል እና ወደ ደስታ ይመራቸዋል። የብረት በትሩን ከለቀቁ፣ በቆሻሻ ውሀ ወንዝ ውስጥ የምስመጥ አደጋም አለ።

“ይህን ለልጆች ለማሳየት፣ እናትየዋ ልጆቹ በጽኑነት የሚይዟት “የብረት በትር” ሆነች፣ እና አባታቸውም ከደህናነት እና ከደስታ ጎትቶ ለመውሰድ እንደሚሞክር ዲያብሎስ ሆነ። ልጆቹ ታሪኩን ወደዱት እና የብረት በትሩን በፅኑነት መያዝ እንዴት አስፈላጊ እንደሆነም ተማሩ። ከቅዱስ መጻህፍት በኋላ፣ የቤተሰብ ጸሎት ጊዜ ነበር። …

“ቅዱስ መጻህፍት፣ የቤተሰብ የቤት ምሽት፣ እና የቤተሰብ ጸሎት ቤተሰቦችን ያጠናክራል። ቤተሰቦችን ለማጠናከር እና በትክክለኛው መንገድ ላይ ለመቆየት እርስ በራስ ለመረዳዳት በእያንዳንዱ እድል መጠቀም ያስፈልገናል።1

የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ሁለተኛ አማካሪ ባርብራ ቶምሰን።

ምን ማድረግ እንችላለን?

  1. የትኛውን የቤተሰቦች እና ቤቶች የማጠናከሪያ ሀሳቦችን ከእህቶቻችሁ ጋር ትካፈላላችሁ? የግለሰቦች ጉዳዮቻቸውን እታሰላስሉአቸው፣ መንፈስ ሀሳቦችን በአዕምሮአችሁ ያመጣላችኋል።

  2. ቤተሰባችሁን እና ቤታችሁን ለማጠናከር በዚህ ወር ምን ነገሮችን ወደፊት በማድረግ ለመቀየር ትችላላችሁ?

ከታሪካችን

ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ቤተሰቦችን እና ቤቶችን የማጠናከር ሃላፊነት ተሰጥቷት ነበር። ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ ለመጀምሪያዎቹ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ሴቶች ይህን አስተምሯቸው ነበር፧ “ወደቤት ስትሄዱ ለባለቤቶቻችሁ በንዴት ወይም ደግ ባልሆነ ንግግር አታነጋግሯቸው፣ ነገር ግን ደግነት፣ ልግስና፣ እና ፍቅር ከዚህ ጀምሮ ስራዎቻችሁን ያድምቁ።”2

በ1914 (እ.አ.አ) ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ ለሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች እንደነገሯቸው፣ “ስለቤተሰብ በምንም ደንቆሮነት ወይም በትንሽም ቢሆን መግባት በማይገኝበት ቦታ … በእዚያም ይህ ድርጅት ይገኛል ወይም ቅርብ ነው፣ እና በዚህ ድርጅት ውስጥ መገኘት በሚገባው ፍጥረታዊ ስጦታ እና መነሳሳትም እነዚህን አስፈላጊ ሀላፊነቶችን በሚመለከት ለማስተማር የተዘጋጁ ናቸው።”3

ማስታወሻዎች

  1. ባርብራ ቶምሰን፣ “His Arm Is Sufficient,” Liahona, ግንቦት 2009, 84።

  2. የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፧ ጆሴፍ ስሚዝ [2007 (እ.አ.አ)]፣ 482።

  3. የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፧ ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ [1998 (እ.አ.አ)]፣ 186።

አትም