2010 (እ.አ.አ)
ታማኝ ጓደኞች
ጁላይ 2010


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሐምሌ 2010 (እ.ዓ.ዓ)

ታማኝ ጓደኞች

አዳኝ ከሚሰጠን ምስጋናዎች አንዱ “ጓደኞች” ብሎ እኛን መጥራቱ ነው። የሰማይ አባቱን ልጆች ሁሉ በፍጹም ፍቅር እንደሚያፈቅር እናውቃለን። ለእርሱ በሚያደርጉት አገልግሎት ታማኝ ለሆኑት ግን ይህን ልዩ ርዕስ ይጠብቃል። ከትምህርት እና ቃል ኪዳን 84 ያሉትን ቃላቶች አስታውሱ፧ “እና ጓደኞቼ፣ ከዚህ ጀምሮ ጓደኞቼ ብዬ እጠራችኋለሁና፣ እንደገናም እላችኋለሁ፣ ከእነርሱ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ወንጌልን ለመስበክ በሀይሌ በሚጓዙበት ቀኖች እንደነበሩት ጓደኞቼ ትሆኑ ዘንድ ይህን ትእዛዝ ለእናንተ መስጠቴ አስፈላጊ ነው” (ትምህርት እና ቃል ኪዳን 84፧77)።

ለእርሱ ሌሎችን ስናገለግል የእርሱ ጓደኞች እንሆናለን። እኛ መሆን የሚገባን አይነት ፍጹም የጓደኝነት ምሳሌ ነው። ለሰማይ አባቱ ልጆች ጥቅም የሚሆነውን ብቻ ነው የሚፈልገው። የእነርሱ ደስታ የእርሱ ደስታ ነው። ለኀጥያታቸው ሁሉ ዋጋን ስለከፈለ፣ የእነርሱን ህመም ሁሉ በእራሱ ላይ ስለወሰደ፣ ችግሮቻቸውን ሁሉ ስለተሸከመ፣ እና ፍላጎታቸውን ሁሉ ስለተሰማው፣ የእነርሱን ሀዘን እንደእራሱ ይሰማዋል። የሚያነሳሳውም ኝጹህ የሆነ ነው። ታዋቂነት የሚፈልገው ለእራሱ ሳይሆን ለሰማይ አባቱ ሁሉ ግርማ ለመስጠት ነው። ፍጹም ጓደኛ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ለሌሎች ደስታን በማቅረብም ስለራሱ በፍሱም አያስብም።

የጥምቀት ቃል ኪዳን የገባነውም የእርሱን ምሳሌ በመከተል እርሱ እንደሚያደርገው የእያንዳንዳችንን ሸከም ለመሸከም ቃል ገብተናል (ሞዛያ 18፧8ን ተመልከቱ)።

በሚቀጥለው ትንሽ ቀናት ለእርሱ ጓደኞች የመሆን ብዙ እድሎች ይኖራችኋል። ይህም በአቧራማ መንገድ ስንጓዙ ይሆን ይሆናል። ይህም በባቡር ውስጥ ስትቀመጡም ይሆን ይሆናል። ይህም በቤተክርስትያን ተሰብሳቢዎች መካከል ለመቀመጫ ቦታ ስትፈልጉም ይሆን ይሆናል። ከተመለከታችሁም፣ ሰው ከባድ ሸከምን ተሸክመው ታያላችሁ። የሀዘን ወይም የብቸኛነት ወይም የንዴታ ሸከም ይሆን ይሆናል። ይህም ለእናንተ የሚታያችሁ መንፈስ ወደልቦች ውስጥ ለመመልከት እንድትችሉ ከጸለያችሁ እና ያዘለሉትን እጆች ከፍ ለማድረግ ቃል ከገባችሁ ይሆን ይሆናል።

ለጸሎታችሁ መልስምለብዙ አመት ያላያችኋቸውም ቢሆን ፍላጎታቸው በድንገት ወደአዕምሮአችሁ የሚመጣና የእናንተ እንደሆነ የሚሰማባችሁ የድሮ ጓደኛችሁ ፊትን መመልከት ይሆን ይሆናል። ይህም ለእኔ ደርሶብኝ ነበር። የድሮ ጓደኞች ከርቀት እና ከብዙ አመቶች ተላልፈው እግዚአብሔር ብቻ ስለሸከሜ በነገራቸው ምክንያት እኔን ለመርዳት መጥተው ነበር።

እንደተቀያሪዎች ወደቤተክርስትያኗ ለሚመጡት ታማኝ ጓደኞች እንድንሆን እና ተሳታፊነትን ያቆሙት እንድናድን ህያው ነብያት ጠይቀውናል። ይህን ለማድረግ እንችላለን፣ እና አዳኝን ሁልጊዜ ካስታወስንም ይህን እናደርጋለን። እርዳታ ለመስጠት እና ሸክርምን ለማስቀለል ስንጥር፣ እርሱም ከእኛ ጋር ይጥራል። እርዳታ ወደሚፈልጉትም ይመራናል። እነርሱ የሚሰማቸውን እንዲሰማንም ይባርከናል። እነርሱን ለማገልገን በምንጥረው ስንጸናም፣ ለእነርሱ የሚሰማውን ፍቅር እንዲሰማን ተጨማሪ ስጦታዎች ይሰጠናል። ያም በታማኝነት ደጋግመን እንድንጥር ማበረታታት እና ጥንካሬ ይሰጠናል።

እና ወደ ታማኝ ጓደኞቹ መካከል በመልካም የምንመጣበትን ደስታን በጊዜና በሰለአለም ይሰማናል። ያንም በረከት ለሁላችንም እና ለምናገለግላቸው ሁሉ እንዲሆን እጸልያለሁ።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

የቤተሰብ አባላት ቅዱስ መጻህፍትን እና የነብያትን ቃላት ሲያጠኑ አንድ ነገርን እንዲፈልጉ ሲጠየቁ ተሳታፊነታቸው ትርጉም ያለው ይሆን ይሆናል (Teaching, No Greater Call[1999], 55 ተመልከቱ)። አንቀጹን ስታነቡ፣ የቤተሰብ አባላት የጌታ ጓደኞች ተብለው ለመጠራት ብቁ እንዲሆኑ የሚረዷቸውን መሰረታዊ መመሪያዎች እንዲጠቁሙ ጠይቋቸው።

Teaching, No Greater Call እንደሚለው፧ “የክርስቶስ አይነት ፍቅር ካላችሁ፣ ወንጌልን ለማስተማር በደንብ ትዘጋጃላችሁ። ሌሎች ጌታን እንዲያውቁትና እንዲከተሉት ለመርዳት ትነሳሳላችሁ” (12)። በአንቀጹ ውስጥ የተሻለ የቤት ለቤት አስተማሪዎች ለመሆን የሚረዷችሁን የመመሪያ መሰረቶችን አግኙ። እነዚህን ከጓደኛችሁ ጋር ተወያዩአቸው፣ እና በጸሎትም ለምታገለግሏቸው እንዴት “ታማኝ ጓደኞች” ለመሆን እንደምትችሉም አስቡበት።

አትም