2010 (እ.አ.አ)
ከከፍተኛ ቦታ የሚታየው እይት
ኦገስት 2010


ወጣቶች

ከከፍተኛ ቦታ የሚታየው እይት

በወጣትነቴ በሳን ዲዬጎ ቤተመቅደስ ለሙታን የመጠመቅ ብዙ እድሎች ነበሩኝ። ምንም እንኳን ሁልጊዜም ጥሩ አጋጣሚዎች ቢኖሩንም፣ የአንድ ጊዜው ጉዞ በልዩ በአዕምሮዬ ይታወሳል።

እኔ 16 አመቴ ነበር እና ትንሿ እህቴ 12 ሆኗት ነበር እና ለሙታን ለመጠመቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ትሄድ ነበር። ይህ የመጀመሪያዋ ጊዜ ስለነበረ፣ ከጨረስን በኋላ በቤተመቅደሱ ውጪ በየዙሪያው ለመሄድ ወሰንን።

የቤተመቅደሱ ምድር በአንድ በኩል እይታ የሚታይበት አንድ ሁለት ቦታዎች ነበሩት፣ ስለዚህ ወደዚያ ሄድን። የሳን ዲዬጎ ቤተመቅደስ የተሰራው በብዙ ጥቅም ላይ በሚውል መንገድ አጠገብ ስለነበረ፣ እይታ በሚደረግበት ቦታ ሲቆም፣ ወደ መንገዱ ነበር መመልከት የሚቻለው።

በእዚያ ቀን በቤተመቅደሱ ከፍተኛ ቦታ ላይ መቆሜ በህይወቴ ላይ አዲስ አስተያየትን ሰጠኝ። መኪናዎቹ በፍጥነት ወደሚያልፉበት፣ ተሞልተው ወደነበሩት የእንግዳ ቦታዎች፣ እና በአስቂኝ ጽሁፎች ወደተሞሉት የመንገድ ምልክቶች አለም ወደታች እየተመለከትኩኝ ነበር።

በእዚያም ጊዜ ነበር ይህ ሀሳብ ወደአዕምሮዬ የመጣው፧ “በዚህ ተሳታፊ ለመሆን አትፈልጊም፤ ይህም የህይወት አላማ አይደለም።” ወደሰማይ አባታችን መመለስ እና እንደ እርሱም መሆን የህይወት አላማ እንደሆነ ሁልጊዜም ተምሬ ነበር። እነዚህን ነገሮች ለማከናወን የአለም ነገሮችን እንደማያስፈልጉኝም አውቄአለሁ።

አስደናቂውን ቤተመቅደስ ለመመከት ዞርኩኝ፣ እና ስለወንጌሉ ላለኝ እውቀት እና ለሰጠኝ አስተያየት ምስጋና ተሰማኝ። በሁከታማ እና በከዳተኛ አለም መካከል፣ የምቆምበትን ከፍተኛ ቦታ እንዳገኘሁም አወቅኩኝ።

በእዚያም ቀን በቤተመቅደስ እያለሁ የሰማይ አባቴን ሁልጊዜም ከአለም ጋር ሳይሆን ከእርሱ ጋር እንደምቆም ቃል ገባሁ። ምንም አለም ቢጥልብንም፣ ቃል ኪዳን የገባነውን በማክበር እና ቅዱስ በሆኑ ቦታዎች በመቆም ልናሸንፋቸው እንችላለን (D&C 87:8 ተመልከቱ)።