2010 (እ.አ.አ)
እምነትን እና የግል ጻድቅነትን ማሳደግ
ኦገስት 2010


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ነሐሴ 2010

እምነትን እና የግል ጻድቅነትን ማሳደግ

ይህን መልእክት አጥኑ፣ እናም ከምትጎበኟቸው እህቶችም ጋር ተገቢ ሲሆን ተወያዩበት። ጥያቄዎችንም እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና በህይወታችሁ ውስጥም በሴቶች መረዳጃ ማህበርን ተሳታፊነት እንዲገኝ ለማድረግ እንዲረዳችሁ ተጠቀሙበት።

ምስል

እምነት • ቤተሰብ • አገልግሎት

ከቅዱስ መጻህፍት፧

ኢሳይያስ 2፧2–3; D&C 109:22–23; 110:8–10

በቤተመቅደስ ለማምለክ ብቁ ለመሆን ያለን ሀላፊነት

“በቤተመቅደስ ውስጥ ከምንቀበላቸው ስነስርዓቶች ጋር የተያያዙት የምንገባቸው ቃል ኪዳናት ወደእግዚአብሔር ፊት ለመግባት የሚያስችሉን መረጃዎች ይሆናሉ። ቃል ኪዳናቶቹ ከእራሳችን ሀይል እና አስተያየት ገደብ በላይ ከፍ እንድንል ያደርጉናል። መንግስትን ለመገንባት ያላንን ታማኝነት ለማሳየት ቃል ኪዳን እንገባለን። በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስር ስንገባም የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ህዝቦች እንሆናለን። ቃል የተገቡት በረከቶች በሙሉ በእነዚህ ቃል ኪዳናት ታማኝ በመሆን በኩል የእኛ ይሆናሉ። …

“የቤተመቅደስ በረከቶችን ለማግኘት የቤተክርስትያኗ ሴቶች ምን ማድረግ ይችላሉ?

“ጌታ የቤተመቅደስ በረከቶችን ያልተቀበሉት እነዚህን ለመቀበል ብቁ ለመሆን ለማድረግ የሚችሉትን በሙሉ እንዲያደርጉ በነቢያቱ በኩል ይጋብዛቸዋል። እነዚህን በረከቶች የተቀበሉትንም እነዚህን አጋጣሚዎች እንደገና እንዲደሰቱባቸው፣ ስለዘለአለማዊ አላማው አስተያየታቸውን እና የሚረዱበትን ለመጨመር እንዲመለሱ ይጋብዛል።

“የአሁኑ ወደቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ለማግኘትም ብቁ ሁኑ። ቤተሰቦቻችንን በዘለአለማዊነት ለማስተሳሰር ወደቤተመቅደስ እንሂድ። ጉዳዮቻችን እንደሚፈቅዱልን ያህል ወደቤተመቅደስ በመደጋገም እንመለስ። ለሙታኑ ዘመዶቻችንም የዘለአለማዊነት ስነስርዓትን ለመቀበል እድል እንስጣቸው። … ወደቤተክርስትያን በየጊዜው ስንሄድ የምንቀበለውን የመንፈስ ጥንካሬን እና ራዕይን እንደሰትባቸው። የኃጥያት ክፍያን ሙሉ በረከቶች ለመቀበል የቤተመቅደስ ቃል ኪዳናትን ለመግባት እና ለመጠበቅ ታማኝ እንሁን።”1

ስልቪያ ኤች ኦልረድ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ።

ከታሪካችን

ፕሬዘደንት ቢ ሒንክሊ (1910–2008) የሴቶች መረዳጃ ማህበር የመጣው እህቶች በቤተመቅደስ ለማምለክ ባላቸው ፍላጎት እንደሆነ አስተምረዋል፧

“የከርትላንድ ቤተመቅደስ በሚገነባበት ጊዜ ሴቶች በቤተመቅደሱ ግድግዳ ማለስለሻ ውስጥ እንዲደባለቁ፣ በዚህም የጸሀይና የጨረቃ ብርሀን ሲመታቸው በማንጸባረቅ ህንጻውን ወብታዊ መልክ እንዲሰጡት ዘንድ የሸክላ ሠሀኖቻቸውን እንዲሰባብሩ ተጠይቀው ነበር።

“ብዙ ገንዘብ በሌለበት ግን እምነት በተትረፈረፈበት በእነዚያ ጊዜዎች፣ ሰራተኞቹ አቅማቸውን እና ጥሬ እቃዎቻቸውን የጌታን ቤት ለመገንባት ሰጡ። ሴቶቹ ከሚያዘጋጇቸው ሁሉ በላይ የሆኑ ምግቦችንም አቅርበውላቸዋል። ኤድዋርድ ደብሊው ቱሊጅ ሀተታ እንዳቀረቡት ሴቶች የቤተመቅደስን መጋረጃ እየሰፉ እያሉ፣ ጆሴፍ ስሚዝ እነርሱን እየተመለከት እንዲህ አለ፣ ‘እህቶች፣ ሁልጊዜም ለመርዳት የተዘጋጃችሁ ናችሁ።’ እህቶች ሁልጊዜም በመልካም ስራዎች ሁሉ መጀመሪያ እና ከሁሉም በፊት ናቸው። ሜሪ በመጀመሪያም ከሞት መነሳት ጊዜ እዛ ነበረች፤ እናም እህቶችም በቤተመቅደስ ውስጥ ለመስራት የመጀምሪያዎች ነበሩ።’ …

“እንደገናም ቤተመቅደሱ በሚገነባበት ጊዜ በናቩ ውስጥ ለሰራተኞቹ ሸሚዞች ለመስራት አንዳንድ ሴቶች ተሰብስበው ነበር። በዚህም ጉዳይ ነበር በሐሙስ በመጋቢት 17 ቀን 1842 ዓ.ም. (እ.አ.አ) በነቢዩ ግምጃ ቤት ከፍተኛ ክፍል ውስጥ ተሰብስበው የነበሩት።”2 እንደዚህም ነበር የሴቶች መረዳጃ ምህበር የተጀመረው።

እኛ ምን ማድረግ እንችላለን?

  1. እህቶቼ ለቤተመቅደስ ለመዘጋጀት እና ለመሄድ ለመርዳት ምን አይነት ድጋፌ ለማቅረብ እንችላለን?

  2. የቤተመቅደስ በረከቶችን ለመቀበል መስዋዕት ያደረጉትን የጥንት እህቶችን ውርስ ለመምሰል እንዴት እችላለሁ?

  3. የቤተመቅደስ በረከቶችን ለማግኘት እንዴት እችላለሁ?

ማስታወሻዎች

  1. ስልቪያ ኤች ኦልሬድ፣ “Holy Temples, Sacred Covenants,” Liahona, ሕዳር 2008, 113, 114።

  2. ጎርደን ቢ ሒንክሊ፣ “Ambitious to Do Good,” Ensign, መጋቢት 1992, 2።

አትም