2010 (እ.አ.አ)
የቤተመቅደስ በረከቶች
ኦገስት 2010


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ነሐሴ 2010

የቤተመቅደስ በረከቶች

የዘለአለም ቤተሰብ ለመሆን ቤተሰባችንን ወላጆቻችን የአውሮፓ የመጀመሪያው ወደሆነው አዲስ ወደተሰራው ወደ ስዊስ ቤተመቅደስ የወሰዱንን ቀን አሁንም አስታውሳለሁ። በዚያ ጊዜ ከአራት ልጆች ታናሽ ሆኜ 16 አመቴ ነበር። ለዘለአለም ለመተሳሰር እንደምንችል አስደሳች ቃል ኪዳን እየተገባልን፣ በክህነትስልጣን ሀይል መሰረት በምድር ለመተሳሰር በመሰዊያው አጠገብ አብረን ተንበረከክን። ይህን ታላቅ አስደናቂ ጊዜ በምንም አልረሳውም።

በልጅነቴ እንደቤተሰብ ለመተሳሰር የአገር ድንበርን አቋርጠን በመሄዳችን በጣም ተደንቄ ነበር። ለእኔ ይህ የቤተመቅደስ ስራ እንዴት አለማዊ ደንበሮችን በማቋረጥ ዘለአለማዊ በረከቶችን ለአለም ለሚኖሩት በሙሉ እንደሚያመጣ በተምሳሌ የሚያገለግልልኝ ነበር። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ቤተመቅደሳት ዜጋነትን፣ ባህልን፣ ወይም የፖለቲካ አስተያየትን ሳይለያዩ ለአለም ሁሉ ጥቅም የተሰሩ ናቸው።

ቤተመቅደሳት መልካም ፍላጎት እንደሚያሸንፍ የሚያሳዩ የማይበገሩ ምስክሮች ናቸው። የቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ የነበሩት ፕሬዘደንት ጆርጅ ኪው ካነን (1827–1901) አንድ ጊዜ እንዳሉት፣ “ለቤተመቅደስ የተቀመጠው እያንዳንዱ የመሰረት ድንጋይ፣ የተገነባው እያንዳንዱ ቤተመቅደስ…በምድር ላይ ያለውን የሰይጣንን ሀይል ይቀንሳል፣ እናም የእግዚአብሔርን እና የአምላካዊነትን ሀይል ይጨምራል።”1

እያንዳንዱ ቤተመቅደስ በምድር ውስጥ የጻድቅነትን ተፅዕኖ ሲያሳድግ፣ በእርግጥም ከሁሉም በላይ ታላቅ የሆነው በረከት የሚመጣውም ወደቤተመቅደሱ ለሚሄዱት ነው። በእዚያም ተጨማሪ ብርሀን እና እውቀት እንቀበላለን እንዲሁም ከተከተልናቸው በደቀመዝሙርነት መንገድ እንድንጓዝ ወደሚረዱን ክብራዊ ቃል ኪዳናት እንገባለን። በአጭር አስተሳሰብም፣ ቤተመቅደስ ስለህይወት ቅዱስ አላማ ያስተምረናል እናም እውነተኛውን የስጋዊና መንፈሳዊ አቅጣጫችንን እንድናገኝ ይረዳናል።

ወደቤተመቅደስ የምንሄደው ለእራሳችን ብቻ አይደለም። ወደ እነዚህ ቅዱስ ቤቶች በምንገባበት በእያንዳንዱ ጊዜ፣ በአብ በተወለደው አንድያ ልጅ የኃጥያት ክፍያ ምክንያት ለእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ እንዲገኝ በተደረገው በተቀደሰው የደህናነት የቤዛነት ስራ ተሳታፊ እንሆናለን። ይህም ለራስ የማያሳስብ እና ቅዱስ አገልግሎት እና እኛ ሟቾች በፅዮን ተራራ ላይ አዳኞች የመሆንን አስገራሚ ስራን ተሳታፊ እንድንሆን ይፈቅድልናል።

በማንኛውም ምክንያት ወደቤተመቅደስ ለመሄድ ለማይችሉት፣ በሚቻላችሁ ሀይል ሁሉ አሁንም የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ እንዲኖራችሁ አበረታታችኋለሁ። የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ የታማኝነታችን እና ጌታን ለማገልገል ያለን ውሳኔን የሚያሳይ ነው። ይህም ለጌታያለንን ፍቅር የሚያሳይ ነው፣ ጌታ እንዳስተማረውም፣ “ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ” ዮሀንስ 14:21

ለጌታ በተቀደሱት እነዚህ ቅዱስ ህንጻዎች የአለም ገጸ-ምድር ማሳመር ሲቀጥሉ፣ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድን ለማግኘት እና ለመጠቀም ብቁ በመሆን ሰማይን ወደ ምድር ለማቅረብ የምንችለውን እንድናደርግ ጸሎቴ ነው። ይህን ስናደርግ፣ ጻድቅነት በህይወታችን እና በቤቶቻችን ውስጥ ብቻ ሳይሆን በህብረተሰቦቻችን እና በአለም በሙሉ ጻድቅነት በእርግጥም ይጨምራል።

ማስታወሻ

  1. ጆርጅ ኪው ካነን፣ in “The Logan Temple,” Millennial Star, ህዳር 12, 1877, 743።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

ብዙ ሰዎች በመናገር ብቻ በላይ ከሚታዩ ነገሮች እርዳታ ሲማሩ በተሻለ ለመማር እና ለረጅም ጊዜ ለማስታወስ ይችላሉ (Teaching, No Greater Call [1999], 182 ተመልከቱ)። በትምህርቱ ጊዜ፣ የቤተመቅደስን ስዕል ለማሳየት አስቡበት። ይህን አንቀፅ ካነበባችሁ በኋላ፣ ቤተመቅደሱ ለምን ለፕሬዘደንት ኡክዶርፍ አስፈላጊ እንደነበረላቸው ተወያዩ። የቤተሰብን ትትንሽ ልጆች ቤተሰቦቻቸውን በቤተመቅደስ ውስጥ የሚያሳዩ ስእሎች እንዲስሉ ጋብዟቸው።

Teaching, No Greater Call እንደሚለው፣ “ያስተማርካቸውን መሰረታዊ መመሪያ በህይወታቸው የሚጠቀሙባቸው አንድ ወይም ሁለት አላማዎች እንዲኖራቸው የምታስተምራቸውን አበረታታ” (159)። ከቤተሰብ ጋር የፕሬዘደንት ኡክዶርፍን መልእክት ለማንበብ አስቡበት እናም የቤተሰብ አባላት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድን ለማግኘት እና ለመጠቀም ብቁ እንዲሆኑ የሚረዷቸውን የግለሰብ አላማዎች እንዲፅፉ አበረታቷቸው።

አትም