2012 (እ.አ.አ)
ችግርን ለመቋቋም ያለ ብርቱንት
ጃንዩወሪ 2012


ወጣቶች

ችግርን ለመቋቋም ያለ ብርቱንት

በወጣት ሴቶች የካስማ ካምፕ ሁለተኛ ምሽት ላይ፣ ታላቅ አውሎ ንፋሰና ዝናብ ነበረ። ከዎርዴ የመጡ በካምፕ የነበሩ 24 ወጣት ሴቶች እና ሁለት መሪዎች ነበሩ፣ እናም ሁላችንም ከዝናቡ ለመሸለል በአንድ ትንሽ ቤት ውስጥ መግባት ነበረብን። በጣም ይዘንብ ነበር፣ እናም ንፋሱም በጣም ሀይለኛ ነበር። የካስማ ፕሬዘደንታችን ያቀረቡትን ጸሎት በተደጋጋሚ እንዳስታውስ አደርግ ነበር። ዎርዳችንም እንደ ቡድን የራሳችንን ጸሎት አደረግን፣ እናም እራሴም ጸለይኩኝ።

ብዙዎቹ ሲቶች ፈርተው ነበር፣ እናም ለምን እንደሚፈሩ ለማየት ቀላል ነበር። የነበርንበር ቤት በጣም ጠንካራ አልነበረም፣ እናም በወንዝ አጠገብ ነበርን። ከ20 ደቂቃ በኋላ፣ ዝናቡ ሀይለኛ ሆኖ የካስማ አባላት በሙሉ የዎርድ አባላት ከነበሩበት ቤቶች ከፍ ማለ ቦታ ወደነበረው ወደ አማካሪዎች ቤት በመሮጥ ሄዱ። የካስማ ፕሪዘደንቴእንደገና ጸለዩ፣ እናም መዝሙር ዘመር፣ የመጀመሪያ ክፍል መዝሙር፣ እና የካምፕ መዝሙሮችን እራሳችንን ለማፅናናት ለመሞከር ዘመርን። ፈርተን ነበር፣ ነገር ግን ሁሉም ነገር መልካም እንደሚሆን ተሰምቶን ነበር። ከግማሽ ሰዓት በኋላ ወደ ዎርድ ቤታችን ለመመለስ ቻልን።

በኋላም በአውሎ ንፋሱ ምን እንደደረሰ አወቅን። እንደ ሁለት ንፋሶች ተከፈለ። አንደኛም እኛ ከነበርንበት ወደ ቀኝ እና ሌላው ወደ ግራ ሄደ። የነበረብን ከሁሉም በላይ መጥፎ አልነበረም።

እግዚአብሔር ጸሎታችንን በእዚያ ምሽት እንደሰማ እና ከአውሎ ንፋሱ እንደጠበቀን አውቃለሁ። እግዚአብሔር እንዲከፈል ካልፈለገው በስተቀር ለምን አውሎ ንፋሱ ይከፈላል። በህይወት አውሎ ንፋስ፣ ወደ ሰማት አባት ለመጸለይ እንደምንችል እና እርሱም እንደሚሰማን እና በደህንነት እንድናልፍበት ብርቱነት እና ጥበቃ በመስጠት መልስ እንደሚሰጠን አውቃለሁ።