2012 (እ.አ.አ)
ሙሉ በሆነ ህይወት መኖር
ጃንዩወሪ 2012


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ጥር 2012 (እ.አ.አ)

ሙሉ በሆነ ህይወት መኖር

አዲሱ አመት ሲጀምር፣ ሙሉ ህይወት፣ በውጤት፣ መልካምነት፣ እና በረከቶች የተሞላ ህይወት፣ ለማግኘት የግል፣ ትሁት፣ እና ታላቅ ሙከራ እንዲያደርጉ እያንዳንዱን የኋለኛ ቀን ቅዱስን እጠይቃለሁ። በትምህርት ቤት መሰረታዊ ነገሮችን እንደተማርን፣ እኔም ሙላት ያለው ህይወት ለማግኘት የሚረዱንን መሰረታዊ ምርሆች አቀርባለሁ።

መልካም አስተሳሰብ ይኖራችሁ

በመሰረታዊ ምርሆዎቼ የመጀመሪያው አስተሳሰብ ነው። የአሜሪካ ሳይኮሎጂስት እና ተፈላሳፊ፣ ውልያም ጄምስ እንደጻፈው፣ “በትውልዳችን ከነበረው ታላቅ ለውጥ ከሁሉም የሚበልጠው ቢኖር ሰዎች የውስጥ የአዕምሮ አስተሳሰባቸውን በመቀየር የውጪ ህይወታቸውን ጉዳይ ለመቀየር እንደሚችሉ ማግኘት ነው።”1

በህይወት ውስጥ ብዙ ነገሮች በአስተሳሰባችን ላይ ይመካሉ። ነገሮችን ለመመልከት እና ለሌልች መልስ ለመስጠት የምንመርጥበት በህሉም ነገሮች ላይ ልዩነት አላቸው። እንደምንችለው ለማድረግ እና ከእዚያም ስለጉዳዮቻችን፣ ምንም ቢሆኑም፣ ደስተኞች ለመሆን መምረጣችን ሰላም እና እርካታ ሊያመጡልን ይችላሉ።

ጸሀፊ፣ አስተማሪ፣ እና የክርስቲያን ሰባኪ የሆነው ቻርልስ ስዊንዶል እንዳለው፣ “ለእኔ አስተሳሰብ …በፊት ከደረሰው በላይ፣ …ከገንዘብ በላይ፣ ከጉዳዮች በላይ፣ ከውድቀቶች በላይ፣ ከውጤታማነት በላይ፣ ሌሎች ሰዎች ከሚያስቡበት ወይም ከሚሉበት ወይ፣ ከሚያደርጉት በላይ አስፈላጊ ነው። ከመልክ፣ ተስጥኦ ካለው፣ ወይም ከችሎታ በላይ አስፈላጊ ነው። ካምፓኒን፣ ቤተክርስቲያንን፣ ቤትን ሊያቋቁም ወይም ሊያፈርስ ይችላል። የሚያስደንቀው ነገር ቢኖርም፣ በየቀኑ ምን አይነት አስተሳሰብ እንዲንደሚኖረን ለመወሰን እንችላለን።”2

ንፋስን መምራት አንችልም፣ ነገር ግን የመርከብ ሸራን ለማስተካከል እንችላለን። ለሙሉ ደስታ፣ ሰላም፣ እና እርካታ፣ መልካም አስተያየትን እንምረጥ

በእራሳችሁ እመኑ

ሁለተኛም በእራሳችሁ፣ በአካባቢያችሁ ባሉት፣ እና በዘለአለም መሰረታዊ መርሆች ማመን ነው።

በእራሳችሁ፣ በሌሎች፣ እና በሰማይ አባታችሁ ታማኝ ሁኑ። ጊዜው በማለፍ እስከሚያመልጠው ድረስ በእግዚአብሔር ታማኝ ካልነበሩት አንዱ ካርዲናል ዎስሊ ነበር፣ እርሱም ሼክስፒር እንዳለው የህይወት አገልግሎቱን ሶስት ጌታዎች በማገልገል እና ሀብትንና ሀይልን በመደሰት አሳለፈ። በመጨረሻም፣ ሀይሉና ሀብቱ ትዕግስት በሌለው ንጉስ ተወሰደበት። ካርዲናል ዎስሊም እንዲህ በማለት አለቀሰ፥

ንጉሱን ባገለገልኩ አይነት አምላኬን በግማሽ ቅንአት ባገለግል

በእዚህ እድሜዬ

ለጠላቶቼ በእራቁቴ አይተወኝም ነበር።3

በ17ኛው መቶ አመት ይኖር የነበረ የእንግሊዝ ቤተክርስቲያን ሰው እና የታሪክ ምሁር ቶማስ ፉለር ይህን እውነት ጽፏል፥ “በእምነቱ መሰረት የማይኖር አያምንም።”4

እራሳችሁን አታስገድቡ ኣም ሌሎች እናንተ ማድረግ በምትችሉት የተገደባችሁ እንደሆናችሁ እንድታምኑ እንዲያደርጓችሁ አትፍቀዱ። በእራሳችሁ እመኑ እናም የምትችሉትን ለማከናወን ኑሩ።

ለማከናወን እንደምትችሉ የምታምኑትን ለማከናወን ትችላላችሁ። እመኑ እናም እምነት ይኑራችሁ።

ፈተናዎችን በብርቱነት ተቋቋሙ።

እንደ ወንድ ለመሞት ፈቃደኛ እንደመሆን ሳይሆን በመልካምነት ለመኖር እንዳለ ውሳኔ ከተመለከትነው፣ ብርቱነት ጥቅም ያለው እና ትርጉም ያለው ምግባረ ጥሩነትይሆናል።

የአሜሪካ ገጣሚ እና ጸሀፊ ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን እንዳለው፥ “ምንም ብታደርጉም፣ ብርቱነት ያስፈልጋችኋል። በምንም መንገድ ላይ ብትወስኑም፣ ትክክል እንዳልሆናችሁ የሚነግራችሁ አንድ ሰው ሁልጊዝለም ይገኛል። ሁልጊዜም ተቺዎቻችሁ ትክክል እንደሆኑ እንድታምኑ የሚፈትኗችሁ ችግሮች ይመጣሉ። የምታደርጉበት ለመወሰን እና እስከመጨረሻ ለመከተል ወታደሮች የሚያስፈልጋቸው አይነት ብርቱነት ያስፈልጋል። ሰላም ድሎች አሏት፣ ነገር ግን እነዚህን ለማሸነፍ ጀግና ወንዶች እና ሴቶች ያስፈልጋሉ።”5

የምትፈሩበት እና ተስፋ የምትቆርጡበት ጊዜ ይኖራል። የተሸነፋችሁ እንደሆናችሁ የሚሰማችሁም ጊዜ ይኖራል። ድልን የማግኘት እድል አስቸጋሪ ይመስላል። አንዳንዴም ዳዊት ከጎልያድ ጋር ለመዋጋት እንደሚሞክርበት አይነት ይሰማናል። ነገር ግን ይህን አስታውሱ—ዳዊት አሸንፏል!

ወደሚፈልገው አላማ ወደፊት ለመግፋት ብርቱነት ያስፈልጋል፣ ነገር ግን ሰው ሲደናቀፍ እና ለማከናወን ሁለተኛ ጥረት ሲያስፈልገው ከእዚህም በላይ የሆነ ታላቅ ብርቱነትም ያስፈልገዋል።

ይህን ጥረት ለማድረግ፣ ብቁ ለሆነ አላማ ለመስራት የትኩረት እንዲኖራችሁ ውሳኔ፣ እናም መምጣቱ የማይቀረውን ፈተና ለመቋቋም ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ ከሆነ ሁለተኛ ጥረት ለማድረግ ብርቱነት ይኑራችሁ። “አንዳንድ ጊዜ ብርቱነት በቀን መጨረሻ ላይ፣ ‘ነገ እንደገና እሞክራለሁ’”6 የሚለው ድምጽ ነው።

በአዲስ አመት ጉዞአችንን ስንጀምር፣ መልካም አስተያየትን፣ አላማችንን እና ውሳኔዎቻችንን ለማከናወን እንደምንችል እምነትን፣ እና ወደ እኛ የሚመጣውን ፈተናዎች ለመቋቋም ብርቱነት ስናሳድግ፣ እነዚህን መሰረታዊ መርሆች እናስታውስ። ከእዚያም የህይወት ሙላይ የእኛ ትሆናለች።

ማስታወሻዎች

  1. ውልያም ጄምስ, በሎይድ አልበርት ጆንሰን መፅሐፎች ውስጥ፣ A Toolbox for Humanity: More Than 9000 Years of Thought (2003)፣ 127።

  2. ቻርልስ ስዊንዶል፣ በዳኔል ኤች. ጆንሰን፣ Lessons for Living ውስጥ (2001)፣ 29።

  3. ዊልያም ሼክስፒር፣ King Henry the Eighth, act 3, scene 2, ቁጥሮች 456–58።

  4. ቶማስ ፉለር፣ በኤች. ኤል. መንከን፣ መሁር፣ A New Dictionary of Quotations ውስጥ፣ (1942)፣ 96።

  5. ራልፍ ዋልዶ ኤመርሰን በሮይ ቢ. ዙክ፣ The Speaker’s Quote Book ውስጥ፣ (2009)፣ 113።

  6. Mary Anne Radmacher, Courage Doesn’t Always Roar (2009).

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

የቤተሰብ አባላት መልካም አስተያየት፣ በእራስ ማመን፣ ወይም ብርቱነት እራሳቸውን እንዲት እንደረዳቸው የግል አጋጣሚዎቻቸውን እንዲካፈሉ ለመጋበዝ አስቡበት። ወይም ለእነዚህ ሶስት መሰረታዊ መርሆች ምሳሌ ከቅዱሳት መጻህፍት እንዲያገኙ ጋብዟቸው። በጸሎት እራሳችሁ የነበራችሁን ቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሰት ወይም አጋጣሚዎችን በማሰብ ለማስተማር ተዘጋጁ።

አትም