የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክቶት፣ ጥር 2012 (እ.አ.አ)
በሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መንከባከብ እና ማገልገል
ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።
“ልግስና [ማለት] ከቅንነት ስሜታ በላይ ነው” ብለው የቀዳሚ አመራር የመጀመሪያ አማካሪ ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ አይሪንግ አስተምረዋል። “ልግስና በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እምነት የሚመጣ እና የኃጢያት ክፍያው ውጢአት ነው።”1 ለሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች፣ የሴቶች ቤት ለቤት ጉብኝት በአዳኝ ያለንን እምነት የምንጠቀምበት የሚሰራበት ልግስና ለመሆን ይችላል።
በሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት፣ እያንዳንዷን እህት በማነጋገር፣ የወንጌል መልእክትን በመካፈል፣ እና የእርሷን እና የቤተሰቧን ፍላጎት ለማወቅ በመፈለግ እንክብካቤን እንሰጣለን። “ትኩረታችን በቁጥሮች ላይ ሳይሆን በሰዎች ላይ ሲሆን፣ የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት የጌታ ስራ ይሆናል” ብለው የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት ጁሊ ቢ. ቤክ ገልጸዋል። “በእርግጥም፣ የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት በምንም የሚፈጸም አይደለም። የስራ ሀላፊነት ሳይሆን በህይወት የሚኖርበት ነው። እንደ ሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪ በታማኝነት ማገልገል የደቀ መዛሙርትነታችን መረጃ ነው።”2
በመከታተል እና በጸሎት እንክብካቤን ስንሰጥ፣ እንዴት ከሁሉም በላይ ለማገልገል እና የእያንዳንዷን እህት እና ቤተሰቧን ፍላጎት ለማሟላት እንደምንችል እንማራለን። አገልግሎት መስጠት በተለያየ መነገድ መከናወን ይቻላል—አንዳንዶቹ ታላቅ ሲሆኑ ሌሎቹም እስከዚህም ታላቅ አይደሉም። “ብዙ ጊዜ ሌላን ከፍ ለማድረግ እና ለመባረክ የሚያስፈልገው ትትንሽ የአገልግሎት ስራዎች ናቸው፥ እነዚህም ስለቤተሰብ የሚያስብ ጥያቄን መጠየቅ፣ የሚያበረታታ ቃላቶችመናገር፣ ከልብ የሚመጣ ምስጋና ማቅረብ፣ የምስጋና ካርድ መስጠት፣ በስልክ ማነጋገር ናቸው፣” ብለው ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን አስተምረዋል። “የምንመለከት እና የምናውቅ ከሆንን፣ እና በምንነሳሳበት ነገሮች የምንሰራ ከሆንን፣ ብዙ መልካም ነገሮችን ለማከናወን እንችላለን። … በሴቶች መረዳጃ ማህበር የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች የሚያቀርቡት የአገልግሎት ስራ መቆጠር የማይቻል ነው።”3
ከቅዱሳት መጻህፍት
ዮሀንስ 13፥15፣ 34–35፤ 21፥15፤ ሞዛያ 2፥17፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 81፥5፤ ሙሴ 1፥39
ከታሪካችን
በ1843 (እ.አ.አ) ፣ በናቩ ኢለኖይ የነበሩ የቤተክርስቲያኗ አባላት በአራት ዎርዶች ተከፋፈሉ። በእዚያ አመት በሐምሌ ውስጥ፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር መሪዎች በእያንዳንዱ ዎርድ በሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ኮሚቴ ውስጥ አራት እህቶችን መደቡ። የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ኮሚቴ ሀላፊነትም በተጨማሪ የእርዳታ ፍላጎቶችን ለመመልከት እና መፅዋዕትን መሰብሰብ ነበሩ። የሴቶች መረዳጃ ማህበር እነዚህን መፅዋዕቶችን እርዳታ የሚፈልጉትን ለመርዳት ተጠቀሙበት።4
ምንም እንኳን የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች መፅዋዕትን አሁን የማይሰበስቡ ቢሆኑም፣ መንፈሳዊ እና ጊዜአዊ እርዳታ የሚያስፈልገውን የማወቅ እና እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት የመስራት ሀላፊነት አለባቸው። ሁለተኛ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት የነበሩት እላይዛ አር. ስኖው እንደገለጹት፥ “አስተማሪ… ወደ ቤት ውስጥ ስትገባ ምን አይነት መንፈስ እንዳለ ለማወቅ የጌታ መንፈስ በብዛት እንዲኖራት በእርግጥም ያስፈልጋታል። … በቤት ውስጥ የሚገኘውን መንፈስ ለማወቅ… እናየሰላም እና የመፅናኛ ቃላትን ለመናገር፣ በእግዚአብሔር እና በመንፈስ ቅዱስ ፊት [መንፈስን] ለማግኘት ለምኑ፣ እናም የበረዳት እህት ካገኛችሁ፣ በእቅፋችሁ ልጆችን እንደምታደርጉት በልባችሁ አስገቧት እናም ሙቀት ስጧት።”5
© 2012 በIntellectual Reserve, Inc መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩኤስኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፧ 6/11 (እ.አ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፧ 6/11 (እ.አ.አ) Visiting Teaching Message, January 2012 ትርጉም። Ahmaric። 10361 506