2012 (እ.አ.አ)
ለሚስዮን በምትዘጋጁበት መካከል
ጁላይ 2012


ወጣት

ለሚስዮን በምትዘጋጁበት መካከል

ፕሬዘደንት ኡክዶርፍ ለወንጌል ሰባኪዎች በሚስዮናቸው መካከል እንደሆኑ እንዲያስቡበት ነግረዋቸዋል። ይህን ሀሳብ ለሚስዮን በምትዘጋጁበት ለመጠቀም ትችላላችሁ፥ 12 ወይም 18 አመታችሁ ቢሆንም፣ በሚስዮን ለማገልገል ትችላላችሁ።

ለሚስዮን በምትዘጋጁበት “ጊዜ” ለማድረግ የምትችሏቸው አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው?

  • በቤተመቅደስ ለመሳተፍ ሁልጊዜም ብቁ ሁኑ።

  • የምትነሳሱበትን በመጻፍ እና በማከናወን የመንፈስ ቅዱስ መነሳሻን ለማወቅ ተለማመዱ።

  • ለወንጌል ሰባኪዎች ጸልዩ።

  • በአካባቢያችሁ ያሉትን የወንጌል ሰባኪዎች በሚስዮን ለማገልገል ለመዘጋጀት ምን ማድረግ እንደሚገባችሁ ሀሳባቸውን ጠይቁ።

  • ጊዜአችሁን፣ በተጨማሪም እንደ አገልግሎት፣ ቅዱሳት መጻህፍት ማጥናት፣ እና ማስታወሻን መጻፍ አይነት አስፈላጊ የምትሳተፉባቸውን ጊዜዎች ለማስተዳደር ተማሩ።

  • ከቤተሰብ አባላት ጋር ስትነጋገሩ፣ በቅርብ ጊዜ ስላነሳሳችሁ ቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሰት ተካፈሉ። ስለቅዱሳት መጻህፍት ያላችሁን ሀሳብ ተካፈሉ።

  • ጓደኞቻችሁን ስለሀይማኖታቸው እና ምን እንደሚያምኑ ጠይቋቸው። ስለእምነታችሁ ለመካፈል ፈቃደኛ ሁኑ። ወደ ቤተክርስቲያን ወይም ወደምትሳተፉበት ጋብዟቸው።

በሚስዮን ለማገልገል ለመዘጋጀት መካከል ላይ እንዳላችሁ ስታውቁ፣ ለጌታ እምነት እና ለመንፈስ ጓደኝነት ብቁ ለመሆን ይህወታችሁን ታስተካክላላችሁ።

አትም