2012 (እ.አ.አ)
ሁልጊዜም በመካከል
ጁላይ 2012


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሐምሌ 2012 (እ.አ.አ)

ሁልጊዜም በመካከል

በፕሬዘደንት ዲየትር ኤፍ ኡክዶርፍ

በአብዛኛው የአለም የቀን መቁጠሪያዎች፣ ነሀሴ የአመት መካከልን ያመለክታል። የነገሮች የመጀመሪያ እና መጨረሻ የሚከበሩ እና የሚታወሱ ቢሆኑም፣ በመካከል የሚገኑ ነገሮች በብዙ ጊዜ ሳይስተዋሉ ያልፋሉ።

መጀመሪያዎች ቆራጥ ውሳኔዎች የሚሰሩበት፣ እቅድ የሚሰሩበት፣ ሀይል የሚፈስበት ጊዜዎች ናቸው። መጨረሻዎች ነገሮች የሚዘጉበት እናም የመፈጸም ወይም የመጥፋት ስሜታ የሚገኙበት ነው። ነገር ግንትክክለኛ በሆነ አስተያየት፣እራሳችንን በነገሮች በመካከል እንደሆንን መመልከትህይወትን በትንሽ ለመረዳት ከመቻል በላይ ትርጉም ባለው ሁኔታ ለመኖር እንድንችል ይረዳናል።

የሚስዮን መካከለኛ ስራ

ከወጣቶቹ የወንጌል ሰባኪዎቻችን ጋር ስነጋገር፣ እነርሱን በሚስዮናቸው መካከለኝ ላይ እንዳሉ አብዛኛውን ጊዜ እነግራቸዋለሁ። ከቀን በፊት እዚይ የደረሱ ወይም ወደ ቤት ከአንድ ቀብ በፊት የሚሄዱ ቢሆኑም፣ እራሳቸውን በመካከል እንዳሉ አይነት ሁልጊዜም እንዲመለከቱ እጠይቃቸኋለሁ።

አዲሶቹ የወንጌል ሰባኪዎች በዙ አጋጣሚዎች ስላልነበራቸው ውጤታማ እንዳልሆኑ ይሰማቸው ይሆናል፣እናም ስለዚህ በልበ ሙሉነት መናገርን እና ለመስራትን ያዘገያሉ። ሚስዮናቸውን ለብዙ ጊዜ ያገለገሉ የወንጌል ሰባኪዎች የሚስዮናቸው መፈጸም እየቀረበ ስለሆነ ይከፋቸው ይሆናል፣ ወይም ከሚስዮን በኋል ምን እንድሚያደርጉ በማሰላሰል ስራቸውን ቀስ ያደርጉ ይሆናል።

ጉዳያቸው ምንም ቢሆን እና የትም ቢያገለግሉ፣ የጌታ አገልጋዮች ለመቆጠር የማይቻሉ የምስራች ዘሮችን እየዘሩ ናቸው። በሚስዮናቸው መካከል እንዳሉ እራሳቸውን ሁልጊዜም መመልከት እነዚህን ታማኝ የጌታ ወኪሎችን ያበረታታቸዋል እናም ያጠናክራቸዋል። ለሙሉ ጊዜ ወንጌል ሰባኪዎች እንዲህ እንደሆነም፣ ይህም ለእኛ እንዲህ ነው።

እኛም ሁልጊዜም በመካከል ውስጥ ነን።

ይህ የአስተያየት ቅያሬ አዕምሮ ከማታለል በላይ ነው። ሁልጊዜም በመካከል ውስጥ ነን ከሚለው ከእዚህ ሀሳብ ላይ ፈጽሞ ያልታሰበ እውነት አለ። በካርታ ላይ የት እንዳለን ብንመለከት፣ በመጀመሪያ ላይ ነን እንል ይሆናል። ነገር ግን በቅርብ ብንመለከተው፣ ያለንበት በትልቅ ቦታ መካከልላይ ነው።

በጠፈር እንደሆነ፣ በጊዜም እንዲህ ነው። በህይወታችን መጀመሪያ ወይም መጨረሻ ላይ እንዳለን ይሰማን ይሆናል፣ ነገር ግን በዘለአለም አስተያየት የት እንዳለን ብንመለከት—ነፍሳችን ለመቁጠር ችሎታ ከሌለን ጊዜ በላይ እንደነበረች፣ እና በኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም መስዋዕት እና የኃጢያት ክፍያ ምክንያት ነፍሳችን ለዘለአለም እንደምትኖር ሲገባን—በእውነትም በመካከል እንዳለን እናውቃለን።

በቅርብ የወላጆቼን ሀውልት ማሳደስ እንደሚገባኝ ተሰማኝ። ጊዜ ለመቃብር ቦታው ደግ አልንበረለትም፣ እናም መልካም ምሳሌ ለነበረው ህይወታቸው አዲስ ሀውልት አስፈላጊ እንደነበረ ተሰማኝ። የተወለዱበት እና የሞቱበት ቀን በሀውልቱ ላይ በትንሽ ስርዝ እንደተገናኘ ስመለከት፣ ይህ ትንሽ የህይወት መጠን ምልክት አዕምሮዬን እና ልቤን በሚበዙ ትዝታዎች ሞላቸው። እነዚህ ውድ ትዝታዎች በወላጆቼ ህይወት መካከል እና በእኔ ህይወት መካከል ትንሽ ጊዜን ያመለክቱ ነበር።

እድሜአችን ምንም ያህል ቢሆን፣ የትም ብንገኝ፣ ነገሮች በህይወታችን ላይ ሲደርሱ፣ እኛ ሁልጊዜም በመካከል ውስጥ ነን። ተጨማሪ ቢሆንም፣ ለዘለአለም በመካከል እንሆናለን።

በመካከል የመሆን ተስፋ

አዎን፣ በይወታችን ውስጥ የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ጊዜዎች አሉ፣ ነገር ግን እነዚህ በዘለአለማዊ ህይወታችን መካከል ምልክት የሚሆኑ ናቸው። በመጀመሪያም ብንሆን በመጨረሻ፣ ወጣትም ብንሆን ያረጀን፣ ምንም የማገልገል ችሎታችንን የሚያስወቅድ ሀሳባችንን ከተውን እና የእርሱ ፍላጎት ህይወታችንን እንዲያስተካክልልን ከፈቀድን ጌታ ለእርሱ አላማ ሊጠቀመን ይችላል።

ዘማሪው እንዳለው፣ “እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።” (መዝሙር 118፥24)። አሙሌቅ እንድናስታውስ እንደሚያደርገን “ይህ ጊዜ ለሰዎች እግዚአብሔርን ለመገናኘት የዝግጅት ወቅት ነው፤ አዎን፣ እነሆ የዚህ ህይወት ቀናት ሰዎች ስራቸውን የሚ ያከናውኑባቸው ቀናቶች ናቸው” (አልማ 34፥32፤ ትኩረት ተጨምሮበት)። ገጣሚው እንደተደነቀበት፣ “ዘለአለም በአሁን የተሰራ ነው።”1

ሁልጊዜም በመካከል መሆን ማለት ጨዋታው በምንም አያልቅም፣ ተስፋ በምንም አይጠፋም፣ መሸነፍ የመጨረሻ አይደለም ማለት ነው። ይትም ብንሆን ወይም ጉዳያችን ምንም ቢሆን፣ የዘለአለም መጀመሪያዎች እና የዘለአለም መጨረሻዎች በፊታችን የተዘረጉ ናቸው።

ሁልጊዜም በመካከል ነን ያለነው።

ማስታወሻ

  1. ኤምሊ ዲከንሰን “Forever—is composed of Nows,” በ The Complete Poems of Emily Dickinson፣ ed. Thomas H. Johnson (1960)፣ 624 ውስጥ።

ይህን መልእክት ማስተማር

ከቤተሰብ ጋር በአንድ ነገር መጀመሪያ ወይም መጨረሻ ላይ ቢሆኑም፣ “ሁልጊዜም በመካከል” እንደሆኑ ለመወያየት አስቡበት። በፊት ስለነበረው ሳያስቡ ወይም ለሚቀጥለው መሳተፊያ ወይም ስራ ሳይጠብቁ፣ አሁን በሚያደርጉት በሚችሉት ያህል እንዲጥሩበት አበረታቷቸው። ይህን ምክር ለማስተዋል እንደ ቤተሰብ ማድረግ የሚችሉበትን አንድ ነገር እንዲመርጡ እናም ይህን አላማ ለማሟላት ተስፋ የሚያደርጉበትን ቀን እንዲመርጡ ሀሳብ አቅርቡላቸው።