2012 (እ.አ.አ)
በፍቅር እና በአገልግሎት ደቀመዛምሩት መሆናችንን ማሳየት
ጁላይ 2012


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሐምሌ 2012 (እ.አ.አ)

በፍቅር እና በአገልግሎት ደቀመዛምሩት መሆናችንን ማሳየት

ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።

እምነት, ቤተሰብ, እርዳታ

በስጋዊ ህይወቱ በሙሉ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሌሎች ያለውን ፍቅር እነርሱን በማገልገል አሳይቷል። እንዲህም ብሏል፣ “እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ” (ዮሀንስ 13፥35)። ምሳሌን አሳይቷል እናም “[የእኛን እርዳታ ፍለጋ የቆሙትን [እንድንረዳ]” ይፈልገናል (ሞዛያ 4፥16)። ሌሎችን ለማገልገል እና እንደ እርሱ ለመሆን እድል እየሰጣቸው፣ በአገልግሎቱ አብረውት እንዲሰሩ ደቀ መዛሙርቶቹን ጠርቷል።1

በቤት ለቤት ለምናስተምራቸው የሚቀጥሉትን በማድረግ ለእነርሱ ያለንን ፍቅራችንን ስናሳያቸው የሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪነት አገልግሎታችን እንደ አዳኝ አገልግሎት እንዲመስል ያደርገዋል፥2

  • ስምቸውንና የቤተሰባቸውን ስም አስታውሱ እናም ስለእነርሱን እወቁ።

  • ሳትፈርዱባቸው አፍቅሯቸው።

  • ጠብቋቸው እናም አዳኝ እንዳደረገው “አንድ በአንድ” እምነታቸውን አጠናክሩ (3 ኔፊ 11፥15)።

  • ከእነርሱም ጋር ልባዊ ጓደኝነት መስርቱ እናም በቤታቸውን እና በሌሎች ቦታዎችም እነርሱን ለመጎብኘት ሂዱ።

  • ስለእያንዳንዷ እህት አስቡ። የልደቅ ቀኖችን፣ መመረቂያቸውን፣ የጋብቻ ቀናትን፣ የጥምቀት ቀናትን፣ ወይም ለእርሷ ትርጉም ያላቸውን ጊዜዎች አስታውሱ።

  • አዲስ እና በብዛት ተሳታፊ ያልሆኑ አባላትንም አስቡባቸው።

  • ብቸኛ እና እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸውንም አስቡባቸው።

ከቅዱሳት መጻህፍት

3 ኔፊ 11ሞሮኒ 6፥4; ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥47

ከታሪካችን

“አዲስ ኪዳን በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ፣ በስም የተጠሩም ቢሆን ያልተጠሩ፣ እምነታቸውን የጣሉ ሴቶች ታሪኮች ይገኛሉ። … እነዚህ ሲቶች የደቀ መዛሙርትነት ምሳሌ ሆነዋል። … [እነርሱም] ከኢየሱስ እና ከአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ጋር ተጓዙ። በአገግሎቱ ለመርዳት ያላችውንም ሰጡ። ከሞቱ እና ትንሳኤው በኋላም፣ ታማኝ ደቀ መዛሙርቶች በመሆን ቀጠሉ።”3

ጳውሎስ ፌቤን ስለምትባል “የቤተክርስቲያን አገልጋይ” ጽፎ ነበር (ሮሜ 16፥1)። ስዎችንም “እርስዋ ለብዙዎች ለእኔም ለራሴ ደጋፊ ነበረችና፥ ከእናንተም በምትፈልገው በማናቸውም ነገር እርዱአት” ብሎ ጠየቀ (ሮሜ 16፥2)። “ፌቤን እና ሌሎች የአዲስ ኪዳን ታላቅ ሴቶች የሰጡት አይነት አገልግሎት አሁንም በሴቶች መረዳጃ ማህበር መሪዎች፣ በሴቶች የቤት ለቤት አስተማሪዎች፣ በእናቶች፣ እና የብዙዎቹ ደጋፊ እና ረጂ በሆኑት ሌሎች ይቀጥላል።”4

ማስታወሻዎች

  1. Daughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society (2011)፣ 105 ተመልከቱ።

  2. See Handbook 2: Administering the Church (2010), 3.2.3።

  3. Daughters in My Kingdom፣ 3።

  4. Daughters in My Kingdom፣ 6።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. ሌሎችን ለመንከባከብ ያለኝን ችሎታ እንዴት ለማሳደግ እችላለሁ?

  2. የምጠብቃቸው ሴቶች እንደምወዳቸው እንዲያውቁ ለማረጋገጥ ምን እያደረኩኝ ነኝ?