2012 (እ.አ.አ)
የሚናገሩትን ማወቅ
ሴፕቴምበር 2012


ወጣት

የሚናገሩትን ማወቅ

ወንጌልን ከሌሎች ጋር ለማካፈል በቂ እውቀት እንደሌላችሑ ከተሰማችሁ፣ ከቅዱሳት መጻህፍት ባሉት የተስፋ ቃላት ተፅናኑ፥

“ስለዚህ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ወደ እነዚህ ህዝቦች ድምጾቻችሁን ከፍ አድርጉ፤ በልባችሁ የምጨምረውን ሀሳብ ተናገሩ፣ እና በሰዎችም ፊት አታፍሩም፤

የምትናገሩትን በዚያች ሰዓት፣ አዎን፣ በዚያች ጊዜም፣ ምን እንደምትናገሩ ይሰጣችኋልና።” (ት. እና ቃ.100፥5–6)።

“አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።” (ዮሀንስ 14፥26)

እነዚህ ታላቅ የተስፋ ቃላት ናቸው፣ ነገር ግን እነዚህን ለማግኘት የእኛን ፋንታ ማከናወን አለብን። በእዚህ መልእክት ውስጥ ፕሬዘደንት አይሪንግ እንዳስተማሩን፥ “[ወንጌሉን] በየቀኑ አዕምሮአችሁን በወንጌሉ እውነት በመሙላት ለማካፈል ተዘጋጁ።” አዕምሮአችሁን በወንጌል እውነት ለመሙላት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

አትም