2012 (እ.አ.አ)
ወንጌልን ልብ ለልብ መካፈል
ሴፕቴምበር 2012


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ መስከረም 2012 (እ.ኤ.አ)

ወንጌልን ልብ ለልብ መካፈል

ምስል
ፕሬዘደንት ሔንሪ ቢ አይሪንግ

እግዚአብሔር ወንጌሉን ለማካፈል ፈቃደኛ በሆኑ አገልጋዮቹ መንገድ ፊት የተዘጋጁ ሰዎችን ያስቀምጣል። እናንተም ይህ በህይወታችሁ ደርሶባችሗል። ድግግሞሹ እንደ አዕምሮአችሁ እና ልባችሁ መዘጋጀት ይወሰናል።

ወንጌልን ለመቀበል ከተዘጋጀ ሰው ጋር ለመገናኘት ዘወትር የሚጸልይ አንድ ጓደኛ አለኝ። መፅሐፈ ሞርሞንን ሁልጊዜም ይዞ ይሄድ ነበር። አጭር ጉዞ ከማድረጉ በፊት ባለው ምሽት፣ መፅሀፉን ሳይሆን በራሪ ወረቀት ይዞ ለመሄድ ወሰነ። ነገር ግን ለመውጣት ሲዘጋጅ፣ “መፅሐፈ ሞርሞንን ይዘህ ሂድ” የሚል የመንፈስ ሹክሹክቻ መጣለት። በሻንጣው ውስጥ አንድ አስቀመጠ።

በጉዞው ጊዜ የሚያውቃት አንድ ሴት በአጠገቡ ስትቀመጥ፣ “እርሷ ትሆን?” ብሎ አሰበ። ከጉዞ በሚመለስበት ጊዜም አብራው ተጓዘች። “ስለወንጌሉ ለመነጋገር እንዴት መጀመር እችላለሁ?” እያለ አሰበ።

እርሷ ግን “ለቤተክርስትያንህ አስራት ትከፍላለህ፣ አይደለምን?” አለችው። እርሱም እከፍላለሁ አለ። ለቤተክርስቲያኔ አስራት መክፈል ቢኖርብኝም አልከፈልኩም አለች። እናም “ስለመፅሐፈ ሞርሞን ምን ልትነግረኝ ትችላለህ?” ብላ ጠየቀችው።

እርሱም መፅሐፉ ከቅዱሳት መጻህፍት አንዱ፣ ሌላኛው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር፣ እና በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንደተተረጎመ ገለጸላት። ለማወቅ የምትፈልግ ስለመሰለች ወደ ሻንጣው እጁን አስገብቶ “ይህን መፅሐፍ ይጄው እንድመጣ ስሜት ተሰምቶኝ ነበር” አለ። “ይህም ለአንቺ መሆኑን ነው የማስበው።”

እርሷም መጽሀፉን ማንበብ ጀመረች። ሲለያዩም፣ “እኔ እና አንተ ስለእዚህ ተጨማሪ እንነጋገርበታለን” አለችው።

ጓደኛዬ ያላወቀው፣ ነገር ግን እግዚአብሔር አውቆት የነበረው ቢኖር ቤተክርስቲያን እየፈእገች ነበር። እርሷ ጓደኛዬን እንደተመለከተች እና ቤተክርሲያኑ ለምን ደስተኛ እንዳደረገው ትገረም እንደነበር እግዚአብሔር አውቆ ነበር። ስለመፅሐፈ ሞርሞን እንደምትጠይቅ እና በወንጌል መልእክተኞች ለመማር ፈቃደኛ እንደምትሆንም እግዚአብሔር አውቆ ነበር። ተዘጋጅታ ነበር። ጓዳኛዬም ተዘጋጅቶ ነበር። እኔ እና እናንተም ለመዘጋጀት እንችላለን።

ለመዘጋጀት የሚያስፈልገንም በአዕምሮአችን እና በልባችን ውስጥ ነው። ሴቷ ስለመፅሐፈ ሞርሞን፣ በጌታ በዳግም ስለተመለሰው ቤተክርስቲያን፣ እና ለእግዚአብሔር አስራት ስለመክፈል ትእዛዝ ሰምታ እና አስታውሳ ነበር። በልቧም የእውነት ምስክርነት ስሜት መጀመሩን ተሰምትዋታል።

ጌታ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በአዕምሮአችን እና በልባችን እውነትን እንደሚገልጥ ተናግሯል (ት. እና ቃ. 8:2 ተመልከቱ)። የምትገናኟቸው ብዙዎቹ ሰዎች የዚህ ዝግጅት ጅማሬ ነበራቸው። ስለእግዚአብሔር እና ስለቃሉ ሰምተዋል ወይም አንብበዋል። ልባቸው ለስላሳ ከሆነ፣ ግልጽ ባይሆንም ኣንዃ የእውነት ማረጋገጫ ስሜት ነበራቸው።

ያችም ሴት ተዘጋጅታ ነበር። መፅሐፈ ሞርሞኑን ያጠናው ጓደኛዬም ተዘጋጅቶ ነበር። ይህም እውነት እንደሆነ ተሰምቶታል፣ እናም መፅሐፉን ይዞ እንዲሄድ ከመንፈስ ቅዱስ የተሰጠውን መመሪያ ተገንዝቧል። በአዕምሮው እና በልቡ ተዘጋጅቶ ነበር።

እግዚአብሔር ዳግም ስለተመለሰው ወንጌል ያላችሁን ምስክርነት እንዲቀበሉ ሰዎችን እያዘጋጀ ነው። የእናንተን እምነት እናም ከዚያም ለእናንተ እና ለምትወዷቸው ከሁሉም በላይ ውድ የሆነላችሁን ነገር ያለፍርሀት የማካፈልን ተግባር ይጠብቅባችኋል።

በየቀኑ አዕምሮአችሁን በወንጌል እውነት በመሙላት ለማካፈል ተዘጋጁ። ትእዛዛትን ስትጠብቁ እና ቃል ኪዳናችሁን ስታከብሩ፣ የመንፈስ ምስክርነት እና በተጨማሪ ም ለእናንተ እና ለምትገናኟቸው ያለውን የአዳኝ ፍቅር ይሰማችኋል።

ድርሻችሁን ከተወጣችሑ፣ ከእናንተ ወደ እነርሱ የሚቀርበውን የልብ ለልብ ምስክርነታችሁን ለመስማት የተዘጋጁ ሰዎችን የማግኘት አስደሳች አጋጣሚዎችን ይበልጥ ታገኛላችሁ።

ከዚህ መልእክት ማስተማር።

የእራስን ምስክርነት የሚጠናከርበትን መንገድ ፕሬዘደንት አይሪንግ የተናገሩትን ከመጨረሻ አንቀጽ በፊት ያለውን አንቀጽ መልእክቱን ከቤተሰብ ጋር ለማንበብ እና ለመወያየት ተመልከት። ወንጌልን ስታካፍሉ ምስክርነታችሁን የማካፈል አስፈላጊነትን ከቤተሰብ ጋር ተወያዩበት። በቤተሰብ ወስጥ ያሉ ልጆችም ለጓደኞቻቸው እንዴት ምስክርነታቸውን ማካፈል እንደሚችሉ ለማሳየት መለማመድ ይጠቅማቸዋል።

አትም