2012 (እ.አ.አ)
ልዩ ፍላጎቶች እና እርዳታ የተሰጠበት
ሴፕቴምበር 2012


የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ማስተማሪያ መልእክት፣ መስከረም 2012 (እ.ኤ.አ)

ልዩ ፍላጎቶች እና እርዳታ የተሰጠበት

ይህን መልዕክት በጸሎት መንፈስ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ንቁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።

ምስል
የሴቶች መረዳጃ ማህበር ማህተም

እምነት, ቤተሰብ, እርዳታ

ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ ሞንሰን እንዳሉት፣ “እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዘወትር ይገኛሉ እናም እያንዳንዳችን ሰውን ለመርዳት አንድ ነገር ለማድረግ እንችላለን ሌሎችን በማገልገል እራሳችንን ካልረሳን በስተቀር፣ በህይወታችንም ውስጥ ያለው አላማ ያነሰ ይሆናል።”1

የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት አስተማሪዎች እንደመሆናችን መጠን፣ የምንጎበኛትን እያንዳንዷን እህት ማወቅ እና ማፍቀር እንችላለን። ለምንጎበኛቸው ሰዎች የምናደርገው አገልግሎት ለእነርሱ ካለን ፍቅር ይመነጫል (ዮሀንስ 13፥34–35 ተመልከቱ)።

እርዳታ በሚያስፈልግበት ጊዜ ለመስጠት እንችል ዘንድ እንዴት የእህቶቻችንን መንፈሳዊ እና ስጋዊ ፍላጎት ማወቅ እንችላለን? የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት አስተማሪ እንደመሆናችን መጠን፣ ስለምንጎበኛቸው ሰዎች ስንጸልይ፤ መንፈሳዊ ምሪትን የማግኘት መብት አለን።

ከምንጎበኛቸው እህቶች ጋር ቋሚ ግንኙነት ማድረግ አስፈላጊ ነው። የግል ጉብኝቶች፣ የስልክ ጥሪዎች፣ የማበረታቻ ማስታወሻ፣ ኢሜል መላክ፣ ከእርሷ ጋር መቀመጥ፣ ከልብ የመነጨ ሙገሳ መስጠት፣ በቤተክርስቲያንም እርሷን ማነጋገር፣ በበሽታ ወይም በችግር ጊዜም እርሷን መርዳት፣ እና ሌሎች የአገልግሎት ስራዎች በሙሉ እርስ በርስ እንድንጠባበቅ እና እንድንጠነካከር ይረዱናል።2

የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት አስተማሪዎች፤ የእህቶችን ደህንነት፣ ምን እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፣ እና ምን አገልግሎት እንደተሰጣቸው ዘገባ እንዲያቀርቡም ተጠይቀዋል። እንደዚህ አይነት ዘገባዎች እና ለእህቶቻችን የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ደቀ መዛሙርትነታችንን እንድናሳይ ይረዱናል።3

ከቅዱሳት መጻህፍት

ዮሀንስ 10፥14–163 ኔፊ 17፥7፣ 9ሞሮኒ 6፥3–4

ከታሪካችን

እርስ በራስ ማገልገል ሁልጊዜም የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ትምህርት ዋና ክፍል ነው። ቀጣይነት ባለው አገልግሎት፤ በየወር ከመጎብኘት በላይ የሆነ ደግነትን እና ጓደኝነትን እናመጣለን። መቆርቆራችን ነው የሚቆጠረው።

13ኛዋ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት የነበሩት ሜሪ ኤለን ስሙት እንዳሉት፣ “የኔ ፍላጎት የስልክ ጥሪን ወይም በአመት ሶስት ጊዜ ወይም በየወሩ ስለሚደረገው ጉብኝት ማሰብ እንዲያቆሙ ልለምናቸው እፈልጋለሁ።” እንዲህም ጠይቀውናል፣ “በዛ ፋንታ ሩህሩህ የሆኑትን ነፍሳት በመንከባከብ ላይ አተኩሩ።”4

ፕሬዘደንት ስፔንሰር ደብሊው ኪምባል [1895–1985 (እ.ኤ.አ)] እንዳስተማሩት፣ “በእርስቱ ወስጥ እርስ በራስ ማገልገል በጣም አስፈላጊ ነው።” ነገር ግን ሁሉም አገልግሎቶች በጀግንነት የሚደረጉ እንዳልሆኑም አውቀዋል። እንዲህም አሉ፣ “ብዙውን ጊዜ፣ አገልግሎታችን ቀላል በሆነ ማበረታቻ ወይም ስጦታ የሚከናወን ነው… ነገር ግን ትንሽ ቢሆንም በጥንቃቄ በተደረገ ስራ ምክንያት የሚመጣው ውጤት እንዴት አስገራሚ ነው።”5

ማስታወሻዎች

  1. ቶማስ ኤስ. ሞንሰን፣ “What Have I Done for Someone Today?” Liahona፣ ህዳር 2009፣ 85።

  2. Handbook 2: Administering the Church (2010)፣ 9.5.1 ተመልከቱ።

  3. Handbook 2፣ 9.5.4 ተመልከቱ።

  4. ሜሪ ኤለን ስሙት፣ በDaughters in My Kingdom: The History and Work of Relief Society ውስጥ (2011)፣ 117።

  5. Teachings of Presidents of the Church: Spencer W. Kimball (2006)፣ 82።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. እንድጠብቃት ለተመደብኩላት ለእያንዳንዷ እህት፤ መንፈሳዊ እና ስጋዊ ፍላጎት መልስ ለመስጠት እንዴት እንደምችል ለማወቅ የግል ተነሳሽነትን ፈልጌአለሁን?

  2. የምጠብቃቸው እህቶች ስለእነርሱ እና ስለቤተሰቦቻቸው እንደምጨነቅላቸው እንዴት ያውቃሉ?

አትም