2012 (እ.አ.አ)
ይቅርታ ደስታን ያመጣል።
ኦክተውበር 2012


ልጆች

ይቅርታ ደስታን ያመጣል

ፕሬዘደንት ኡክዶርፍ ለቤተሰብ አባላቶቻችን ይቅርታ መስጠት እንደሚገባን አስተምረዋል። የጆሴፍ እና የአና ምርጫዎች ቤተሶቦቻቸውን እንዴት እንደነካ ተመልከቱ።

ጆሴፍ እና ታናሽ እህቱ አና አብረው ይጫወቱ ነበር። አና የጆሴፍን መጫወቻ ነጠቀችበት። ጆሴፍ ምን ማድረግ ይገባዋል?

ጆሴፍ በአና ላይ ተናደደ።አና አለቀሰች። የጆሴፍ እናት ከእህቱ ጋር በመጣላቱ ቀጣችው። ጆሴፍ መልካም ያልሆነ ምርጫ ስላደረገ ቅርታ ተሰማው።

ጆሴፍ እህቱን ይቅርታ አደረገላት እናም ሌላ መጫወት አገኘ።በደስታ አብረው ተጫወቱ። የጆሴፍ ለእህቱ ደግ ስለሆነ እና በቤተሰብ ውስጥ ሰላምን ስለሚጠብቅ እናታቸው ተደሰተች። ጆሴፍ ይቅርታ ለማድረግ ስለመረጠ ደስታ ተሰማው።

በኋላም፣ ጆሴፍ እና አና ምግብ ለማዘጋጀት እናታቸውን ለመርዳት ያስፈልጋቸው ነበር። ጆሴፍ እርዳታ አልሰጠም። አና ምን ታድርግ?

አና ለእናቷ ቅሬታዋን ገለጸች አና ብቻዋን በብቻዋ ስለመስራቷ ተጨቃጨቀች። በእራት ጊዜ በጭቅጭቁ ምክንያት ሁሉም አልተደሰሩም።

አና ጆሴፍን ይቅር አለችው እና በእራት ጊዜ ረዳች። እናታቸው ለአና እርዳታ ምስጋና ተሰማት። ቤተሰቡ አብረው እራትን በመብላት ተደሰቱ። አና ይቅር ለማድረግ በመምረጧ ተደሰተች።

ቅይርታ ምርጫችሁ እንዴት የቤተሰባችሁን ደስታ ይነካል?

አትም