2012 (እ.አ.አ)
ጸሎት እና ሰላም
ኦክተውበር 2012


ወጣቶች

ጸሎት እና ሰላም

አንድ ምሽት ከእናቴ ጋር ተጨቃጨቅኩኝ እና ከፍቶኝ ነበር። ስለዚህ ለመጸለይ ወሰንኩኝ። ምንም እንኳን የከፋኝ ብሆንም እና “መንፈሳዊ” ለመሆን ባልፈልግም፣ መጸለይ ደስተኛ እንድሆን እና ተከራካሪ እንዳልሆን እንደሚረዳኝ አውቅ ነበር። እናቴ ከክፍሌ ከወጣች በኋላ፣ መጸለይ ጀመርኩኝ። “ውድ የሰማይ አባት ሆይ፣ ወደ አንተ በዚህ ምሽት የመጣሁበት ምክንያት …” አይሆንም። አይኖቼንን ከፍቼ እጆቼን ዘረጋሁ፤ ያም የማይመች ይመስል ነበር። እንደገናም ሞከርኩኝ። “የሰማይ አባት ሆይ፣ የምፈልገው …” ያም እንደ እንግዳ አይነት ስሜት ነበረው። ሰይጣን የሰማይ አባትን ለእርዳታ የምጠይቅበትን ጸሎት እንድተው እንደሚገፋፋኝ ስሜታ ተሰማኝ።

በድንገት አመሰግናለሁ እንድል የሚገፋፋኝ ስሜት ተሰማኝ። ስለዚህ እንዲሁም አደረግሁኝ፣ እናም የሰማይ አባቴን የማመሰግንባቸው ብዙ ነገሮች ከአዕምሮዬ መፍሰስ ጀመሩ። እርሱን ማመስገን ስፈጽምም፣ የነበረውን ችግር ካሰብ መወያየት ጀመርኩኝ።

በኋላም በውስጤ አስደናቂ የሆነ ሰላም፣ የሰማይ አባታችን እና ወላጆቼ እንደሚያፈቅሩኝ እና እኔም የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንኩኝ ስሜት የሚሰጠኝ የደመቀ መንፈሳዊ ስሜትተሰማኝ። ከእናቴም ይይቅርታን ለመጠየቅ እና እርሷም ይቅርታ እንዳደርግላት የጠየቀችንኝ ለመቀበል ቻልኩኝ።

አትም