የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ጥቅምት 2012 (እ.ኤ.አ)
ለደስተኛ ቤተሰብ አስፈላጊ የሆነው አንዱ ቁልፍ
ታላቁ የራሺያ ጸሀፊ ሊዮ ቶልስቶይ አና ከረኒና የሚባለውን ልበ ወልድ መፅሀፉን ለመጻፍ ሲጀምር እነዚህን ቃላት ተጠቅሟል፥ “ደስተኛ ቤተሰቦች በሙሉ የተመሳሰሉ ናቸው፤ ደስተኛ ያልሆኑ ቤተሰቦችም በሙሉ በእራሳቸው መንገድ ደስተኛ አይደሉም።”1 ምንም እንኳን እኔ እንደ ቶልስቶይ ደስተኛ ቤተሰቦች የተመሳሰሉ እንደሆኑ የማወቅ እርግጠኛነት ባይኖረኝም፣ አብዛኛዎቹ የሚመሳሰሉበትን አንድ ነገር ለማወቅ ችያለሁ፥ ሌሎች ፍጹም ያልሆኑባቸውን ነገሮች ይቅርታ የመስጠት እና የመርሳት እንዲሁም መልካም የሆነውን ለመፈለግ የሚጥሩበት መንገድ አላቸው።
እነዚያ ደስተኛ ያልሆኑ ቤተሰቦች፣ በሌላም በኩል፣ በአብዛኛው ጊዜ ስህተትን ይፈልጋሉ፣ ቂም ይይዛሉ፣ እናም በፊት የተከፉበትን አይረሱም።
ደስተኛ ያልሆኑት “አዎን፣ ነገር ግን …” በማለት ይጀምራሉ። አንዱም “አዎን፣ ግን እንዴት ባስከፊ ሁኔታእንደጎዳችኝ አታውቅም፣” ይላል። ሌላውም “አዎን፣ ግን እንዴት መጥፎ እንደሆነ አታውቅም” ይላል።
ምናልባት ሁለቱም ትክክል ሊሆኑ፣ ወይም ማናቸውም ትክክል ላይሆኑ ይችላሉ።
የማስቀየው ብዙ ደረጃዎች አሉ። የመዳት ብዙ ደረጃዎችም አሉ። ነገር ግን የተመለከትኩት ቢኖር ቁጣችንን ምክንያት የምንሰጠው እና ህሊናችንን የምናረካው የሌሎችን ስራ ይቅርታ ለመስጠት የማይገባው እና ራሳቸውን ወዳጅ እንደሆኑ የሚያሳዩ ታሪኮችን ለእራሳችን በመንገር ሲሆን፣ በእዚያም ጊዜም የእራሳችን ምክንያት ንጹህ እና የዋህ እንደሆነ ከፍ በማድረግ ነው።
የልዑል ውሻ
ወደቤቱ ሲመለስ ውሻው ከፊቱ ላይ ደም እየተንጠበጠበ ስላገኘው ልዑል የሚነግር ከ13ኛው መቶ አመታት አካባቢ ከዌልሽ የመጣ የጥንት ታሪክ ነበር። ሰውየውም ፈጥኖ ወደ ውስጥ ገባ፣ እናም በሚያስደነግጥ ሁኔታም ህጻን ልጁ እንደጠፋ እና የተኛበትም ተገልብጦ እንደነበረ ተመለከት። በንዴትም ልዑሉ ጎራዴውን ሳበ እናም ውሻውን ገደለው። ከአጭር ጊዜ በኋላ፣ ልጁ ሲያለቅስ ሰማ—ህጻኑ በህይወት ነበር! በህጻኑም አጠገብ የሞተ ተኩላ ነበር። ውሻው፣ በእውነቱ፣ የልዑሉን ህጻን ልጅ ከሚገድለው ተኩላ ጠብቆ ነበር።
ምንም እንኳን ይህ ታሪክ ተውኔታዊ ቢሆንም፣ የሚያሳየው ነጥብ አለ። ሌሎች አንድ ነገርን የሚያደርጉበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለእራሳችን የምንነግረው ታሪክ በእርግጥ ከእውነታ ጋር ለመስማማት የማይችልም ይሆናል—አንዳንዴም በእርግጥ እውነታው ምን እንደሆነም ለማወቅ አንፈልግም። ምሬታችንን እና ቅሬታችንን የተሰማብንን አጥብቀን በመያዝ ለቁጣችን ምክንያት ለመስጠትም እንፈልጋለን። አንዳንዴም እነዚህ ቂም የምንይዝባቸው ለብዙ ወራት ወይም አመታት ለመቆየት ይችላሉ። አንዳንዴም እድሜ ልክ ለመቆየት ይችላሉ።
የተከፋፈለ ቤተሰብ
አባት ልጁ ተምሮት ከነበረው መንገድ ወጥቶ ስለሄደ ይቅርታ ለመስጠት አይችልም። ልጁ በአባቱ ተቀባይነት የሌላቸው ጓደኞች ነበሩት፣ እናም አባቱ ማድረግ ይገባዋል ብሎ ከሚያስባቸው ነገሮች የተቃረኑ ብዙ ነገሮች ያደርግ ነበር። ይህም በአባት እና በልጅ መካከል ጠብ አመጣ፣ እናም ልጁ ወዲያው ሲችልም ከቤት ወጣ እና እንደገናም አልተመለሰም። ደግመውም አልተነጋገሩም ማለት ይቻላል።
አባትየው የትክክለኛነት ስሜት ነበረው? ምናልባት።
ልጅስ ትክክል እንደሆነ ስሜት ነበረው? ምናልባት።
የማውቀው ነገር ቢኖር ቤተሰቡ ተከፋፍሎ እና ደስተኛ አልነበሩም ምክንያቱም አባት ወይም ልጅ እርስ በራስ ይቅርታ ለመስጠት አልቻሉምና። ስለእርስ በራ ስላላቸው መራራ ትዝታቸው ለመርሳት አልቻሉም። ልባቸውን በፍቅር እና በይቅርታ ሳይሆን በንዴት ሞሉ። እያንዳንዱም የሌላውን ህይወት በመልካም መነገድ ለመንካት ያላቸውን እድል ሰረቁ። በመካከላቸው ያለው ክፍተት በጣም ጥልቅ እና ሰፊ የሆነ መስሎ እያንዳንዱን ሰው በእራሱ የስሜት ደሴት ላይ በመንፈስ እስረኛ ያደርጋል።
እንደ እድል ሆኖ፣ የሚያፈቅረን እና ጥበበኛው ዘለአለማዊ የሰማይ አባታችን ይህን የኩራት ልዩነትን የምናሸንፍበትን መንገድ ሰጥቶናል። ታላቁ እና መጨረሻ የሌለው የኃጢአት ክፍያ የይቅርታ እና የመታረቅ ታላቅ ስራ ነው። ከፍተኛነቱም ከምረዳው በላይ ነው፣ ነገር ግን ስለእውነትነቱ እና መጨረሻ ስለሌለው ሀይሉ በሙሉ ልቤና ነፍሴ እመሰክራለሁ። አዳኙ ለኃጢአቶቻችን መክፈያ ራሱን አቀረበ። በእርሱም በኩል ይቅርታን አገኘን።
የቱም ቤተሰብ ፍጹም አይደለም።
ማንኛችንም ኃጢአት የሌለን አይደለንም። እያንዳንዳችን፣ በተጨማሪም እኔ እና እናንተ፣ ስህተት እንሰራለን። ሁላችንም ቆስለናል። ሁላችንም ሌሎችን አቁስለናል።
ከፍ ከፍ መደረግ እና ዘለአለማዊ ህይወትን የምናገኘው በአዳኙ መስዋዕት መሰረት ነው። የእርሱን መንገድ ስንቀበል እና ልባችንን በማለስለስ ኩራታችንን ስናሸንፍ፣ መታረቅን እና ይቅርታን ወደ ቤተሰቦቻችብ እና ወደ ግል ህይወቶቻችን ለማምጣት እንችላለን። እግዚአብሔር ይቅርታ ለመስጠት፣ ተጨማሪ ጥረት ለማድረግ፣ የእኛ ጥፋት ባይሆንም ይቅርታ በመጠየቅ የመጀመሪያ ለመሆን፣ የድሮ ቂምን ለመተውና እነርሱን ደግመን እንዳንኮተኩታቸው ይረዳናል። አንድያ ልጁን ለሰጠው እግዚአብሔር እና ህይወቱን ለእኛ ለሰጠው ለወልድ ምስጋና ይሁን።
በየቀኑም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር ይሰማናል። “ብዙ ስለተሰጠኝ ምክንያት” በሚለው ተወዳጅ መዝሙር ውስጥ እንደተማርነው ለጓደኞቻችን ከእራሳችን ተጨማሪ ለመስጠት አንችልምን?2 ጌታ ይቅርታን የምናገኝበት በር ከፍቶልናል። የእራሳችንን ስራ ከፍ ማድረግጋችንን እና ኩራታችንን መተዋችን እና ለምንታገላቸው፣ በልዩም ከቤተሰቦቻችን ጋር በሙሉ፣ ያን የተባረከ የይቅርታ በር መክፈታችን ትክክል አይሆንምን?
በመጨረሻም፣ ደስታ የሚመጣው ከፍጹምነት ሳይሁን፣ መለኮታዊ የሆኑትን መሰረታዊ መርሆችን፣ እንዲሁም ትትንሽ እርምጃዎችን፣ በመጠቀም ነው። የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ሸንጎ እንዳወጁት፥ “በቤተሰብ ህይወት ውስጥ ደስታ የሚገኘው ቤተሰብ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት በኩል ሲገነባ ነው። የተሳኩ ጋብቻዎች እና ቤተሰቦች የሚመሰረቱት እና የሚጸኑት በእምነት፣ በጸሎት፣ ንስሀ በመግባት፣ በይቅርታ፣ በክብር፣ በፍቅር፣ በርህራሄ፣ በስራ፣ እና በመልካም መዝናኛ እንቅስቃሴዎች መሰረት በኩል ነው።”3
ይቅርታ በእነዚህ እውነቶች መካከል የተቀመጠ፣ በሰማይ አባታችን የደስታ እቅድ የተመሰረተ ነው። ይቅርታ መሰረታዊ መርሆችን ስለሚያገናኝ፣ ሰዎችንም ያገናኛል። ይህም ቁልፍ ነው፣ የተቆለፉ በሮችን ይከፍታል፣ የቀና መንገድ መጀመሪያ ነው፣ እናም ደስተኛ ቤተሰብ ለማግኘትም ታላቅ ተስፋችንም ነው።
እግዚአብሔር በቤተሰባችን ውስጥ የተሻለ ይቅርታን የምንሰጥ፣ እርስ በራስ የተሻለ ይቅርታን የምንሰጣጥ፣ እና ለእራሳችንም በተጨማሪ ይቅርታ የምንሰጥ እንድንሆን እግዚአብሔር ይርዳን። አብዛኛዎች ደስተኛ ቤተሰቦች የሚመሳሰሉበት አንዱ አስደናቂ መንገድ የሆነውን ይቅርታ እንዲያጋጥመን እጸልያለሁ።
© 2012 በ መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፧ 6/11 (እ.ኤ.አ) ትርጉም የተፈቀደበት፧ 6/11 (እ.ኤ.አ) First Presidency Message, October 2012 (እ.ኤ.አ) ትርጉም። ። 10370 506