የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት መልእክት፣ ጥቅምት 2012 (እ.ኤ.አ)
ቃል ኪዳኖቻችንን ማክበር
ይህን መዝገብ አጥኑ እና ተገቢ ከሆነ ከምትጎበኟቸው እህቶች ጋር ተወያዩት። እህቶቻችሁን ለማጠናከር እና የሴቶች መረዳጃ ማህበርን የህይወታችሁ ተሳታፊ ክፍል እንዲሆን እንዲረዳችሁ ጥያቄዎቹን ተጠቀሙባቸው።
የሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት ትምህርትየደቀመዝሙርነታችን መገለጫ እና ሌሎችን ስናገለግልና ስናጠናክር ቃልኪዳኖቻችንን ማክበሪያ መንገድ ነው። ቃል ኪዳን የተቀደሰ እና በእግዚአብሔር እና በልጆቹ መካከል ያለ የሚጸና የተስፋ ቃል ነው። የአስራ ሁለቱ ሐዋሪያት ቡድን አባል ሽማግሌ ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳሉት፣ “የቃል ኪዳን ልጆች እንደሆንን ስናውቅ፣ ማን እንደሆንን እና እግዚአብሔር ምን እንደሚጠብቅብን እናውቃለን”። “የእርሱ ህግ የተጻፈው በልባችን ውስጥ ነው። እርሱ አምላካችን ነው እና እኛም ህዝቡ ነን።”1
እንደ ሴቶች የቤት ለቤት ጉብኝት እንደመሆናችን መጠን፣ የምንጎበኛቸው ሴይች የገቡትን ቃል ኪዳን ለመጠበቅ በሚጠሩበት ጊዜ ልናጠናክራቸው እንችላለን። ይህን በማድረግም፣ ለዘለአለም ህይወት በረከቶች እንዲዘጋጁ እንረዳቸዋለን። የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ቡድን አባል ሽማግሌ ኤም. ራስል ባለርድ እንዳሉት፣ “በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከጌታ ጋር ቃል ኪዳን የገባች እያንዳንዷ እህት ነፍሳትን ለማዳን፣ የአለም ሴቶችን ለመርዳት፣ የፅዮን ቤቶችን ለማጠናከር፣ እና የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት መለኮታዊ ሀላፊነት አላት።”2
ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን ስንገባ እና ስንጠብቅ፣ በእግዚአብሔር እጅ መሳሪያዎች ለመሆን እንችላለን። እምነታችንን በግልጽ መናገር እና በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን እምነት እርስ በራስ ለማጠናከር እንችላለን።
ከቅዱሳት መጻህፍት
1 ኔፊ 14፥14፤ ሞዛያ 5፥5–7፤ 18፥8–13፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥78፤ 84፥106
ከታሪካችን
ቤተመቅደስ “ለቅዱሳን በሙሉ ምስጋና የሚሰጥበት ቦታ” ነው ብሎ ጌታ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በ1833 (እ.ኤ.አ) ገለጠለት። ይህም “ለቅዱሳን ሁሉ ሀምስጋናን መስጫ የማቅረቢያ ቦታ፣ እና በአገልግሎቱ ስራ በተለያዩት ጥሪአቸው እና ሀላፊነታቸው የተጠሩት ሁሉ ለየሚማሩበት ቦታ፤ በአገልግሎታቸው፣ በአስተያየታቸው፣ በመሰረታቸው፣ በመሰረታዊ መርህ፣ እና በትምህርታቸው፣ እና የመንግስቱ ሀቁልፍ በላያችሁ የተሰጣችሁ የመንግስቱ ሀቁልፍ፣ በምድር ላይ ያስላለው የእግዚአብሔር ለመንግስትን በሚመለከት ሁሉ፣ በዚህ ሁሉ ፍጹም ሐመረጃቸውዳትን ፍጹም እንዲያደርጉይኖራቸው ዘንድ ነው” (ት. እና ቃ. 97፥13–14)።
በ1840 (እ.ኤ.አ) መጀመሪያ በናቩ፣ ኢለኖይ ውስጥ የነበሩ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች እርስ በራስ ለቤተመቅደስ ስርዓቶች ለመዘጋጀት ተረዳዱ። በናቩ ቤተመቅደስ ውስጥ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ከተቀበሉት የከፍተኛው የክህነት ስርዓቶች ውስጥ፣ “የአምላክነት ሀይል” ታይቷል (D&C 84:20)። “ቅዱሳን ቃል ኪዳኖቻቸውን ሲጠብቁ፣ ይህም ሀይል ተጠናክሯል እናም ወደፊት ቀናት እና አመታት በነበራቸው ፈተናዎች አጠናክረዋቸዋል እናም አጽንቶአቸዋል።”3
ዛሬ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ፣ በአለም በሙሉ ያሉ ታማኝ ሴቶች እና ወንዶች በቤተመቅደስ ውስጥ ያገለግላሉ እናም በቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖች መሰረት ብቻ ለመቀበል በሚችሉት በረከቶች ብቻ ጥንካሬን ያገኛሉ።
© 2012 በIntellectual Reserve, Inc መብቶቹ በህግ የተጠበቁ። በዩ.ኤስ.ኤ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፧ 6/11 (እ.ኤ.አ)። ትርጉም የተፈቀደበት፧ 6/11 (እ.ኤ.አ)። Visiting Teaching Message, October 2012 ትርጉም። Amharic። 10370 506